2014-04-04 16:14:32

የስምምነት ሰነድ በቅድስት መንበርና በከፕ ቨርድ መካከል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ ሕንጻ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካን ለጉብኝት የገቡት የረፓብሊካዊት ከፕ ቨርድ መራሔ መንግሥት ኾሰ ማሪያ ፐረይራን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።
ርእሰ ብሔር ኾሰ ማሪያ ፐረይራ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተሰናብተው እንዳበቁም በሐዋርያዊ ሕንጻ በሚገኘው አቢያተ ፍርድ ተብሎ በሚጠራው የጉባኤ አዳራሽ በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ በብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርት ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፅዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘቸው የጠቆመው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ በሁለቱ አገርች የጸናው ወዳጅነት ትብብር የሚያጎለብት በሰላሳ አንቀጽ የጸናው በሕግና ደንብ የተደገፈው ስምምነት እርሱም ዕለተ ሰንበት ዓበይት መንፈሳዊ በዓላት ማክበር የጋራ ጥቅም የሚቆጣጠር ቅዱሳት የአምልኮ ሥፍራ አክብሮት የቤተ ክርስቲያን ንብረት እውቅና መሰጠት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የተካተተ መንፈሳዊ ሕንጸት ለመከላከያ ኃይል አባላት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሕንጸት መርሃ ግብር ማክበር በትምህርት ቤቶች የትምህርተ ሃይማኖት አቅርቦት የቤተ ክርስቲያን የግብረ ሠናይ አገልግሎት በህክምና መስጫ ጣቢያዎችና በማከሚያ ቤቶች የቤተ ክርስቲያን ተሳትፎ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ንብረትና ቁጠባ አክብሮት የተሰኙት ነጥቦች ያካተተ መሆኑ ገልጦ ይኽ አዲሱ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ ከፕ ቨርድ ፕራያ ሰነ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በረፓብሊካዊት ከፕ ቨርድና በቅድስት መንበር መካከል የተደረሰው ስምምነት በሙላት ጸድቆ እግብር ላይ እንዲውል የሚያደርግ የስምምነት ፊርማ ለማኖር የተካሄደ ግኑኝነት መሆኑ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.