2014-03-26 16:06:07

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በጋራ ለጋራ ጥቅምና ለሰላም


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መጋቢት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. በሊባኖስ በጃምሁር ክልል ወደ ተካሄደው ስምንተኛው የክርስቲያን ምእመናንና የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የጋራ የጸሎት ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይኽ የጋራው የጸሎት ጉባኤ በክልሉ የቀድሞ የቅዱስ ዮሴፍ መንበረ ጥበብና የጃምሁር ተቋም ነበር ተማሪዎች ሰላምዊ የጋራ ኑሮ ለማረጋገጥ በሚል ዓላማ በማነቃቃት ያስጀመሩት መሆኑም ሲታወቅ፣ ቅዱስ አባታችን የሁለቱ ሃይማኖቶች ምእመናን ለጋራ ጥቅምና ለሰላም በመተባበር በጋራ እንዲተጉ ማሳሰባቸውና የጸሎቱ ጉባኤ በሊባኖስ ይኸው ብሔራዊ በዓል እንዲሆን ከተወሰነ ዓራተኛ ዓመቱን ባስቆጠረው እ.ኤ.አ. መጋቢት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. በተከበረው የብስራተ ገብርኤል ዓመታዊ ከማርያም በዓል ጋር ተያይዞ የሚካሄድ ሲሆን፣ ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ለተሟላ ሰብአዊ እድገትና ሕብረተሰብ ለመገንባት በጋራ ለጋራ ጥቅም የሚሰጡት አስተዋጽኦ ያለው አስፈላጊነት የላቀ መሆኑ ገልጠው የተለያዩ ሃይማኖት አባላት በጋራ ለጋራ ጥቅም በሚያደርጉት ትብብር እንዲበረቱና በዚሁ የትብብርና የመቀራረብ ባህል የሚፈጽሙት መልካም ተግባር እንዲቀጥሉበት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
በተካሄደው የጋራው የጸሎት መርሃ ግብር የተሳተፉት የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ክቡር አባ ሚገል አንገል አዩሶ ጉይክሶት ባሰሙት ንግግር፣ ግኑኝነት መናገርና ማዳመጥ ያካተተ መሆኑና አንዱ ሲናገር አንዱ ያዳምጣል ያዳመጠው በተራው ይናገራል ቀድሞ የተናገረው በተራውም በማዳመጥ ተግባር ይተጋል፣ ውይይት እንዲህ ሲሆን መግባባት ያስገኛል፣ አንዱ ሲናገር ሌላው ሳያዳምጥ የገዛ እራሱን ሃሳብና ውሳኔ ለማረጋገጥ ሲል በገዛ እራሱን ሃሳብ ላይ ተዘግቶ በማሰላሰል ሲገታ ግኑኝነት የውይይት ግኑኝነት እንዳይሆን ያግዳል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት እያንዳንዱ በቃልና በሕይወት ምስክርነት በሚሰጥበት እምነቱ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ስለዚህ በዚህ ዓይነት ተጨባጭ እምነት ላይ የሚገነባው የጋራው ውይይት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል መከባበር መቀባበል አንዱ ለሌላው ክፍት እንዲሆን የማድረግ ኃይል እንደምኖረው ገልጠው፣ አያይዘው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት ሙስሊሞችና ክርቲያኖች ለቅድስት ድንግል ማርያም ያላቸው አክብሮት እንዲሁም በቁራን ቅድስት ማርያም ብዙ ግዜ እንደምትጠቀስ አስታውሰው ያሰመሩበት ሃሳብ ኣባ አዩሶ ባስደመጡት መልእክት ጠቅሰው፣ ማርያም የውይይት አብነትና አርአያ ነች፣ እያንዳንዱ በገዛ እራስ እምነት ላይ ባለው እማኔዎች ላይ ግትር ብሎ ገዛ እራሱ ከመዝጋት ይልቅ ሌላውን ለመቀበል ለመገንዘብ ገዛ እራሱ ክፍት በማድረግ ለወንድማማችናን ለወዳጅነት ባህል መረጋገጥ የሚያግዝ መሣሪያ ሆኖ መገኘት አለበት ብለው በሁለቱ ሃይማኖቶች መካከል ያለው ለቅድስት ማርያም የአክብሮት ተግባር የጋራው ሰላማዊ ማህበራዊ ኑሮ ግንባታ መሠረት ነው በማለት ያስደመጡት ንግግር እንዳጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.