2014-03-17 19:38:26

“ኢየሱስን አዳምጡ ቃሉንም ከሌሎች ጋር ተካፈሉት፣ ሁሌ ወንጌል ይዛችሁ ተጓዙ”


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በብዙ ለሚቆጠሩ ም እመናን የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመኰዝ “ኢየሱስን አዳምጡ ቃሉንም ከሌሎች ጋር ተካፈሉት፣ ሁሌ ወንጌል ይዛችሁ ተጓዙ” ሲሉ ካስተማሩ በኋላ ከም እመናኑና ነጋድያኑ ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ትናንትና የተነበበው ወንጌል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጴጥሮስ ዮሓንስንና ያዕቆብን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር የሄደበትና ታላቅነቱና ክብሩ የገለጠበትና ከሙሴና ከኤልያስ ጋር ስለሕማማቱ የተወያየበት ይህ በእርሱ ደስ ያለኝ ልጄ ነው የሚል ቃል ከሰማይ የተሰማበት ክፍልን የሚገልጥ ነበር፣
የደብረ ታቦር ፍጻሜ በዚህ አላበቃም፤ ጴጥሮስ ጌና ይህንን እየተናገረ ሳለ “እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።” ይህ እርሱን ስሙት የሚል የእግዚአብሔር አብ ጥሪ ሁላችንን እንደሚመለከትም እንዲህ ሱሉ ግለጠውታል፣
“ይህ የእግዚአብሔር አብ ጥሪ እጅግ አስፋላጊ ነው፣ የኢየሱስ ተከታዮች የሆንን እኛ ቃላቱን ለመስማትና ተጠንቅቀን እተግባር ላይ ለማዋል የተጠራን፣ ኢየሱስን ሰምቶ ለመቻል በወንጌል እንደምንነበር ሕዝብ እርሱን ለመስማት በፍልስጥኤም ጐዳናዎች ይከተሉትን ያዳምጡት እንደነበር እኛ በአጠገቡ መገኘትና እርሱን መከተል ያስፈልገናል፣ ጌታ ኢየሱስ አንድ ካተድራል ወይም መስበክ ያ መድረክ አልነበረውም ሆኖም ግን መምህር ነበር ተንቀሻቃሽ መምህር ሆኖ አባቱ የሰጠውን ትምህርት በየጐደናዎቹ ያስተምር ነበር፣ እነኚህ ትምህርቶች እንደ ጉዞው ነበር የተከናወኑት ምክንያትም የተወሰነ ቦታ ስላልነበረው ነው፣ አሁን እኛ ኢየሱስን ለማዳመጥ እንድንከተለው ያስፈልጋል የምንከተለውም በወንጌል የተጻፈው ቃሉን በማንበብና በማስተንተን ነው፣ ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ በአደባባዩ ወደ ነበሩ ሰዎች ያቀና ኃይለኛ ጥያቄ አንዲህ ሲሉ አቅርበዋል፣
“እናንተ ወንጌልን ታነባላችሁ ወይ? ወንጌልን ማንበብ መልካም ስራ ነው እንዲያው አንድ ትንሽ ወንጌል በኪስ ወይንም በሻንጣ ይዞ መጓዝና በየዕለቱ ዕድል በምናገኝበት ወንጌሉን ማንበብ ጥሩ ነው፣ ወንጌልን ስናነብ ኢየሱስ ነው የሚናገረን፣ ይህንን ነገር እሰቡበት፣ ከባድም አይደለም አራት የወንጌል መጻሕፍት እንዲሆኑም አስፈላጊ አይደለም ከወንጌላቱ አንዱም ያስኬዳል፣ ሁሌ ወንጌል ከእኛ ጋር ይዘን መጓዝ አለብን ምክንያቱም የኢየሱስ ቃል ስለሆነ እንድናዳምጠው ነው፣ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ይህንን የወንጌል ክፍል በተለይ አሁን ባለንበት ዘመነ ጾም ጋር በመዛመድ በሁለት ቃላት ማለትም ወደ ተራራ መወጣትና ከዛም መውረድ በሚሉ ቃላት አጠቃለዋል፣ ወደ ተራራ መውጣት በእምነት ዓይን ስንመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት መወያትንና ድምጹን የመስማት የጸሎት ቦታ መሆኑን ከተራራ መውረድ ደግሞ ያገኘነውን ጸጋ ከሌሎች ጋር ለመካፈልና በተግባር ብምግባረ ሠናይ ወንድሞቻችን መርዳት መሆኑን ገልጠዋል፣ ሆኖም ግን በወንጌሉ እንደተመለከተው ቅዱስ ጴጥሮስ የኢየሱስ ክብርን ባየና የእግዚአብሔር እዛ መኖር ካጣጠመ በኋላ ሳይታወቀው ገዛ ራሱንና ሌሎቹን ሓዋርያት በመርሳት “ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ” ሲል ተናገረ፣ ይህ ዓይነት ፈተናን እኛን ሁሌ ያጋጥመናል፣ ባለህበት የመቆም ፍላጎት ነገር ግን መንቀሳቀስ ያስፈልጋል የግድ ከተራራው መውረድ አለብን፣ ስለዚህ የደብረ ታቦር ፍጻሜ መውጣትና መውረድ እንዳለብን ያስተምረናል፣
“እርግጥ ነው እኛ ለየት ያለ ቦታ ወደ ጸጥ ያለ ተራራ መውጣት ያስፈልገናል ይህም ገዛ ራሳችንን ለማግኘትና የጌታን ድምጽ ለይቶ ለማወቅ ለመቻል ነው፣ ይህንን ጸሎት በምናሳርግበት ጊዜ እናደርገዋለን፣ ሆኖም ግን እዛ ብቻ መቅረት የለብንም! ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት መገናኘት እንደገና ከተራራው ለመውረድና ወደ ታች ተመልሶ በሚዳው የሚረኙትን ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን በተለይ ደግሞ በድካም በሕመም ፍትሕ በማጣት በድንቁርና በመንፈሳዊና ቍሳዊ ድኅነት የተጨነቁና ሁሉ የተጫጫነባቸውን ማግነትና መጽናንት ያስፈልጋል፣ “የኢየሱስ ቃላትን ስንሰማ የኢየሱስ ቃላትን ስናዳምጥና በልባችን ስንይዘይ ያ ቃል ያድጋል፣ እንዴት እንደሚያድግ ታውቃላችሁን፣ ለሌሎች በመስጠት ያድጋል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በእኛ የሚያድገው ስንሰብከው ለሎኤሎች ስንሰጠው ነው ይህም ነው እውነተኛ የክርስትያን ሕይወት የሚባለው፣ ይህ የመላው ቤተ ክርስትያን የስብከተ ወንጌል ተል እኮ ነው፤ ለማንኛው የተጠመቀ ለእኛ ለሁላችን የተሰጠ ተል እኮ ነው፣ አትርሱት ኢየሱስን ሰምቶ ለሌሎች መስጠት፣ በዚሁ ሳምንት ይህንን ለማድረግ ወስኑ ታደርጉታላችሁን፣ እፊታችን እሁድ እጠይቃችኋለሁ እውነት ያደረጋችሁት እንደሆነ ደግሞ ትነግሩኛላችሁ፣ ሌላው አንድ ትንሽ ወንጌል በኪስ ወይንም በሻንጣ ይዞ መጓዝና ትንሽ ጊዜ ባገኙበት ጊዜ በየዕለቱ ማንበብ፣ ይህንን አድርጉ ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከም እመናኑና ነጋድያኑ አሳርገው በተለያዩ ቋንቋዎች አመስግነው መልካም ቀንና መልካም ምሳ በመመኘት ሸኝዋቸው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.