2014-03-12 16:14:56

ክራኮቪያ ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን 2016 ዓ.ም.


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. የ 2016 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በክራኮቪያ እንዲከናወን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መወሰናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የሚከናወንባቸው ቀናቶችም እ.ኤ.አ. ከ ሐምሌ 26 ቀን እስከ ሐምሌ 31 ቀን ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 20 ቀን እስከ ሐምሌ 25 ቀን የሰበካዎች የወጣቶች ቀን ቀደም ብሎ እንደሚከናወን የ2016 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን www.krakow2016.com የተሰየመው ይፋዊ ድረ ገጽ ያሰራጨው መግለጫ የጠቀሰው ሲር የዜና አገልግሎት ሲያመልክት፣ የዜናው አገልግሎት አክሎ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 26 ቀን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የመክፈቻ በዓል፣ ከረቡዕ ሐምሌ 27 ቀን እስከ ዓርብ ሐምሌ 29 ቀን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መርሃ ግብሮች የሚከናወንባቸው ቀናቶች መሆናቸውና፣ ሐሙስ ሐምሌ 28 ቀን ወጣቶች ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ልዩ የአቀባበል ሥነ ስርዓት እንደሚያከናውኑ አስታውቀዋል።
ዓርብ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የመስቀል መንገድ እንደሚካሄድ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ እ.ኤ.አ. ቅዳሜ ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የዋዜማ ጸሎት አስተንትኖ ምስክርነት መንፈሳዊ መዝሙር የሚቀርብበት ዕለት ሲሆን ጧት እሁድ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መዝጊያ ዕለት ምክንያት መስዋዕተ ቅዳሴ መርተው ሥልጣናዊ ስብከት እንደሚያስደምጡና በዚያኑ የመዝጊያ ዕለት ቅዱስነታቸው ቀጣዩ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ያስተናጋጅ አገር ስም በይፋ እንደሚገልጡ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.