2014-02-26 20:24:26

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ዛሬ ይዘንማል ተብሎ ነበር! ያም ሆነ ይህ እናንተ ግን እዚህ ትገኛላችሁ! ባሳያችሁት ብርታት ላመግናችሁ እወዳለሁ፣ በዚሁ ትምህርታችን ስለ ምሥጢረ ቀንዲል የሕሙማን ምሥጢር እንመለከታለን፣ ይህ ምሥጢር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ርኅራኄ በእጆቻችን እንድንነካ ያስችለናል፣ ባለፉት ዘመናት የመጨረሻ መቀባት ይባል ነበር ምክንያቱም በመጨረሻዎቹ የሞት መጋፈጥ ግዝያት መንፈሳዊ መጽ ጽናት እንደሚሰጥ ይታመን ነበርና፣ ስለ ቅብ ዓ ሕሙማን ስንናገር ግን በሕመምና በሥቃይ ያለውን አመለካከታችን እንድናሰፋና በእግዚአብሔር ምሕረት ዓይን እንድንመለከተው ያስችለናል፣
    በቅዱስ መጽሓፍ የዚህ ምሥጢር ጥልቅ ትርጉምን የሚገልጥ በቅብ ዓ ሕሙማን ተደብቆ ያለውን የሚያበራ በሉቃስ ወንጌል 10፡30-35 የመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ እናገኛለን፣ ይህንን ምሥጢር በምንካናወንበት ማንኛው ግዜ ጌታ ኢየሱስ በእርሱ እንደራሴ ካህን አማካኝነት በጸና ለታመመውና ለሚሰቃየው ሰው ወይንም ሽማገሌ ቅርብ ሆነ ይፈውሰዋል፣ የመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ የወንበዴዎች ሰለባ ሆነ በቆሰለው ሰው ቍስሎች ላይ ዘይትና ወይን እንዳፈሰሰ ይናገራል፣ ይህ ዘይት ያ በያዓመቱ በጳጳስ በበዓለ ጸሎተ ሓሙስ በዘይት ቡራኬ መሥዋዕተ ቅዳሴ ላይ ሕሙማን እንዲቀቡበት የሚባረከው ቅዱስ ዘይትን ያመልክታል፣ ወይኑ ደግሞ ያ ጌታ ኢየሱስ ሕይወቱን መሥዋዕት በማድረግ የገለጠልን ፍቅርና የሰጠን ጸጋን በማመለከት በመላው የቤተ ክርስትያን ምሥጢራት ላይ ያለውን ሃብትን ያመለክታል፣ በመጨረሻ ያ ቍስለኛ ለአንድ እንግዶች አስተናጋጅ በአደራ ሲሰጥና እስከሚድን ድረስም እንዲከባከበውና ለዚህ ተግባር የሚደረገው ወጪም በመልካሙ ሳምራዊ እንደሚሸፈን ይገልጣል፣ ይህ እንግዳ ተቀባይ ማን ይሆን? ቤተ ክርስትያን ናት! የክርስትያኖች ማኅበር የሆንን እኛ ነን፣ በየዕለቱ ጌታ ኢየሱስ በመፈስና በስጋ ለሚሰቃዩት አደራ ይሰጠናል፣ አለምንም መንፈግና መቆጠብ መላውን የእርሱ ምሕረትና ደህንነት እንድንሰጣቸውም አደራ ይለናል፣
    የዚህ ምሥጢር ተልእኮ ጥርት ባለ መንገድ በቅዱስ ያዕቆብ መልእክት 5፡14-15 “ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል።” በማለት ተገልጦ እናገኘዋለን፣ ከመጀመርያዎቹ የሓዋርያት ዘመን ይደረግ የነበረ ተል እኮ መሆኑን እንገነዘባለን፣ ይህም ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ሕመምተኞችና የሚሰቃዩን በሚመለከት የእርሱ ዓይነት ርኅራኄና እንክብካቤ እንዲያደርጉ እንዳስተማራቸው በስሙና እንደየልቡ የሰላምና የመዳን ፍላጎት ተል እኮውን እንዲቀጥሉ በዚሁ ምሥጢር ስልጣን ሰጣቸው፣ ይህ ማለት ግን ሁሌ ተአምር ለመሻትና ወዲያውኑ ከሕመሙ የመዳን ጸጋ የማኘት ፈተና ውስጥ እንዳያገባን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፣ ነገር ግን በዚሁ ምሥጢር ኢየሱስ ሕመምተኛውን እንደሚሸኝ ከ65 ዓመት ወዲህ ይህንን ምሥጢር ለመቀበል ስለሚቻልም ሽማግሌውን እንደሚሸኝና እንደሚረዳው መገንዘብ ያስፈልጋል፣ የሚቀርበን ኢየሱስ ራሱ ነውና፣ ነገር ግን አንዳንድ እምነተቢሶች ሕመምተኛው ቄስ እንጥራ ወይ ብሎ ሲጠይቅ ይቆይ መጥፎ ዕድል ይዞልን ይመጣል ወይም ሕመምተኛ ይደነግጣል የሚል አስተሳሰብ ያላቸው እንዲሁም ቄሱ ከመጣ ወዲህ እማ ስለመቃብር ማሰብ ነው የሚል የተሳስተ አስተባብም አይጠፋም፣ ይህ ግን እውነት አይደለም፣ ቄሱ ሕመምተኛው ወይንም ሽማግሌውን ለመርዳት ነው የሚመጣው ስለዚህ ቄሶች ሕመምተኞችን ሲጐበኙ እጅግ አስፈላጊ ተግባር መሆንን መገንዘብ አለባቸው፣ ሕመምተኞችን ደግሞ ቄስ መጥቶ እንዲጸልያላቸው እንዲባርክዋቸውና እንዲቀብዋቸው መበረታት ያስፈልጋል ምክንያቱም ራሱ ኢየሱስ ነው በካህኑ አማካኝነት ጽናትና ብርታት እንዲሰጠው ተስፋ ሰጥቶ እንዲረዳው የሚመጣው ራሱ ኢየሱስ ነውና፣ ኃጢአቱንም ይቅር ይልለታል! ይህ ደግሞ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ስለሆነ ሌላ ሓሳብን እንድታወግዱ ይሁን፣
    ለምን ነው ይህንን ምሥጢር ብዙ ጊዜ የማንጠይቀው ያልን እንደሆነ ዋነኛው ምክንቱም በዘመናችን በብዙ ሰዎችና ቤተሰቦች አስተሳሰብ ውስጥ ስቃይን እንዲያው ሞትን ሳይቀር እንደመጥፎ ነገር በማሰብ የተቻላቸውን ያህል ሊደብቁት ስለሚታገሉ ነው፣ ለብዝዎቻችን ስቃይ ሕመምና ሞት ምሥጢራዊ ሆነው ለኣእምሮአችን እንደሚያስቸግሩን እና እፊታችን በሚደቀኑበት ጊዜ ምንም ቃል ለማስተንፈስ እንደማንችል እውነት ነው፣ እንዲህ በመሆኑም አንድ ካህን ለታመሙት ምሥጢረ ቀንዲል ወይንም ቅብ ዓ ሕሙማን በሚያደርግበት ጊዜ እጆቹን በሕመምተኛው ላይ በማኖር ጸጥ የሚልበት ጊዜ አለ፣

የተወደዳችሁ ጓደኞቼ| ሁሌ በስቃይና በሕመም በምንቸገርበት ጊዜ ብቻችን አለመሆናችንን ማወቅ ጥሩ ነገር ነው፣ በሥር ዓቱ ግዜ ካህኑና አብረውን ያሉ ሰዎች መላዋን ቤተ ክርስትያን ይወክላሉ ይህችም ከከርስቶስ ጋር አንድ አካል የሆነችው ቤተ ክርስትያን ከሕመምተኛውና ቤተሰቦቹ ጋር በመሆን እምነታቸውንና ተስፋቸውን እየመገበች በጸሎትና ወንድማዊ ፍቅር ትደግፋቸዋለች፣ ነገር ታላቁ መጽናናት በምሥጢሩ ራሱ ጌታ ኢየሱስ መኖሩና በእጃችን ይዞ ልክ በምድራዊ ሕይወቱ ከሕመምተኞች ጋር ያደርገው እንደነበር ይደግፈናል ከእርሱ ማንም ሊለየን እንደማይችል ማለትም ሕመም ይሁን ስቃይ ከእርሱ ሊለየን እንደማይችል ያረጋግጥልናል፣ አደራ የምላችሁ ለሕመምተኞች ቄስ የመጥራት ልማድ ይኑረን ሕመም ስል ደግሞ የሁለት ሶስት የጉንፋን ሕመም ወይም ሌላ ቀለል ያለ ሕመም ሳይሆን ሰዎች በጽኑ በሚታመሙበት ጊዜ እንዲሁም ለሽማግሌዎቻችን ይህ ምሥጢር እንዲታደላቸው ይሁን፣ መጽናናት ብርታትና ኃይል ከኢየሱስ በማግኘት ወደ ፊት እንዲገስግሱ እናድርግ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፥








All the contents on this site are copyrighted ©.