2014-02-24 20:12:47

ሁላችን የክርስቶስ ስለሆንን በማኅበሮቻችን በድርጅቶቻችንና በእንቅስቃሴዎቻችን መከፋፈል መኖር የለበትም፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እሁድ ከአዳዲስ ብፁዓን ካርዲናሎች ጋር ቅዳሴ ካስረጉ በኋላ እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ም እመናንና ነጋድያ እንዲሁም የአዳዲስ ካርዲናሎች ቤተሰቦች በተገኙበት የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል የአዳዲስ ካርዲናሎች ሲመት በማመልከት “ሁላችን የክርስቶስ ስለሆንን በማኅበሮቻችን በድርጅቶቻችንና በእንቅስቃሴዎቻችን መከፋፈል መኖር የለበትም፣” ሲሉ አንድነትና ውህደት መለያችን መሆኑን ገልጠው ሁላችን መለያየትንና መከፋፈልን ማስገድ እንዳለብን ምክንያቱም ቤተ ክርስትያን የአንድ ሰባኪ አይደለችም፤ የክርስቶስ ናትና ብለዋል፣
መላያየት የዛሬ ሳይሆን በእነ ቅዱስ ጳውሎስ ሓዋርያ ጊዜ በመጀመርያዎቹ ሳይቀር መካፋፈል በቆሮንጦስ ቤተ ክርስትያን ሳይቀር እንደነበርና ሓዋርያዋው ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻፈው አንደኛ መልእክት 1፤12 “እያንዳንዳችሁ። እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ። ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?” በማለት ይህ ዓይነት አስተሳሰብ በአ እምሮ አችን ውስጥ እንዳይኖር ምክንያቱም ቤተ ክርስትያን የሓዋርያት ሳይሆን የክርስቶስ ስለሆነች ይህ ዓይነት አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑን ይገልጣል፣
“ከዚህ አባልነት በክርስትያናዊ ማኅበር ሃገርስብከት ይሁን ቍምስና ማኅበር ይሁን እንቅስቃሴ ሁላችን በክርስቶስ ስም የተጠመቅንና የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን ያሉን ልዩነቶም ወደ ግጭትና መለያየት የሚመሩ መሆን የለባቸውም፣ ማንነታችንና ክብረታችን ይህ ነው፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ በማኅበሮቻችን የመምራት ተል እኮ የተሰጣቸው እንዲሁም የስብከትና የቅዱሳት ምሥጢራት መስተዳደር ሥልጣን የተሰጣቸው ልዩ ሥልጣን እንደተቀበሉና የማኅበሮቻችን ጌቶች እንዳይመስላቸው ይልቁንም ማኅበራችንን ማገልግለና የቅድስና ጐዳናን በደስታ እንዲፈጽሙ ሊረድዋቸው ያስፈልጋል፣ ቤተ ክርስያንን ይህንን ዓይነት አገልግሎት የኑሮ ዘዴ ለአዳዲስ ካርዲናሎች ትመኛለች፣
“የትናንትና የካርዲናሎች ጉባኤ የዛሬው መሥዋዕተ ቅዳሴ የቤተ ክርስትያን አንድነትን ማለትም ካቶሊካዊትነት እንድናጣጥም ዕድል ሰጥቶናል፣ የቤተ ክርስትያን ካቶሊካዊትነት ዓለም አቀፋዊነት ከካርዲናሎች ጉባኤ ይወለዳል እነኚህ ካርዲናሎች ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታታይ ጋር በፍጹም አንድነት የተሳሰሩ ናቸውና፣ ጌታም ለቤተ ክርስትያን አንድነት እንድንሠራና ይህንን አንድነት እንድንገነባ ጸጋውን ይስጠን፣ የቤተ ክርስትያን አንድነት በክርስቶስና ከክርስቶስ ሲሆን መለያየቶችና ግጭቶች ግን ከክርስቶስ አይደሉም ከእነዚህም አንድነት እጅግ እንደሚያፈልገን መረዳት ያስፈልጋል፣ ስለዚህም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስትያን ያለንን እምነትና ፍቅር በማሳደስ ትናንትና የተሰየሙት እረኞች አደራ ለተሰጣቸው ሕዝበ እግዚአብሔር ፍቅርንና ርኅራኄን በማስየት እንዲመርዋቸው እግዚአብሔር ጸጋውን እንዲሰጣቸው መደገፍና በጸሎት መርዳት እንዳለብን አሳስበዋል፣
“ለመሆኑ አንድ ጳጳስ አንድ ካርዲናል ወይንም አቡን ምን ያህል ጸሎት ያስፈልገዋልን ያልን እንደሆነ የእግዚአብሔር ሕዝብን ወደፊት ማራመድ እስከሚችል ድረስ ነው መልሱ! እንዲረዳ ስንል ሕዝበ እግዚአብሔር ማገልገል ማለታችን ነው ምክንያቱም የጳጳስ የካርዲናል የአቡን ጥሪ ሕዝበ እግዚአብሔር በክርስቶስ ስም ማገልገል ስለሆነ ነው፣ በክርስቶስ ስም አገልጋይ መሆን ነው፣ መልካም አገልጋዮች እንጂ መልካም ጌቶች እንዳንሆን ጸልዩልን፣ ጳጳሳት ካህናት ቤተ ክህነትና ምእመናን በክርስቶስ ታማኝ የሆነች ቤተ ክርስትያንና ለወንድሞች ለማገልገል የሚያቃጥል ፍላጎት ያለን እንዲሁም ለዘመናችን ወንዶችና ሴቶች መንፈሳዊ ትንቢታዊ መጠባበቆችና ፍላጎቶች ምስክርነት መስጠት አለብን፣ እመቤታችን ድንግል ማርያምም ለዚህ ታብቃን እንዲሁም በሁሉ ጉዞ አች ሸኝታ ትጠብቀን ሲሉ ካስተማሩ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.