2014-02-19 18:20:57

ር.ሊ.ጳሓዋርያዊ ጉብኝት በቅዱስ ቶማስ ሓዋርያ ቍምስና ሮም;


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እሁድ በሮም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ቶማስ ሓዋርያ ቍምስና ላይ ሓዋርያዊ ጉብኝት አድርገዋል፣ የቍምስናዋ አባሎች በሙሉ በታላቅ ደስታ ያስተናገዱት ይህ ሓዋርያዊ ጉብኝት በቅዳሴና በተለያዩ ግንኝቶችና ውይይቶች ተፈጽመዋል፣
በቍስናው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ቅዱስነታቸው “የጐረቤት የጓደኛንና የወንድማሞች ፍቅርን በእውነትና በንጽሕና መኖርን እንቀስቅስ” ሲሉ በዕለቱ ወንጌል የተመለከተውን የፍቅር ጐዳና እንድንከተል አሳስበዋል፣
ቅዱስነታቸው በቍምስናው ሲደርሱ በተደረገው ታላቅ አቀባበል በሮም ሃገረ ስብከት የእርሳቸው እንደራሴ የሆኑ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ እንዲሁም የዞኑ ረዳት ጳጳስ ብፁ ዕ አቡነ ፓውሊኖ ስⷋቮን እና የቤተ ክርስትያኑ ቆሞስ ጥቀ ክቡን አባ አንቶንዮ ደኤሪኮ ተገኝተዋል፣ በቦታው ሲደርሱ ቅዱስነታቸው ለመጀመርያ ሰላም ያልዋቸው ሕጻናትን ነበር፣
“ኢየሱስን ለመውደድ የሚያስችል አንድ ምስጢር እነግራችዋለሁ፣ ተጠንቅቃችሁ ስሙኝ! ኢየሱስን ለማፍቀር መጀመርያ እርሱ እንዲያፈቅረን መፍቀድ አለብን፣ ገባችሁ ወይ! ስራውን የሚያከናውነው እርሱ ነውና! እኛ አይደለንም! በመጀመርያ የሚያፈቅረን እርሱ ነው፣ ካሉ በኋላ ሕጻናቱም መልሰው ጓደኛችንና ወገናችን ነህ ጨብጥ ሲሉ እጆቻቸውን ዘረጉላቸው፣ ከዚህ በኋላ እያንዳንዳቸው በልባቸው ውስጥ ያለውን እውነት ለመፈለግ እንዲህ ሲሉ አሳስበዋል፣
“ዛሬ ነፍሴ ንጽህት ናት ወይስ ቆሻሻ ብለን ከመጠየቅ ይልቅ በልቤ ውስጥ ምን አለ በማለት እውነቱን ጥርት አድርገን ለገዛ ራሳቸን ማሳውቅ አለብን ይህንን ደግሞ እንደ የጋራ ነገር አድርጎ ከመመልከት ይልቅ ወደየልቦቻችን ተመልሰን እንዲህ ብለን እንጠይቅ፣
“በልቤ ውስጥ ፍቅር ነው ያለው ወይስ ጥላቻ? ለበደሉኝ ሰዎች ይቅር የማለትና የምሕረት ስሜት ነው ያለኝ ወይስ የቂመ በቀልና መልሶ የመበቀል ስሜት ነው ያለኛ? በማለት ውስጣችንን እንፈትሽ፣ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ጸሎት ያስፈልገናል እግዚአብሔር ይርዳን ሲሉ አሳስበዋል፣
ከቅዳሴው በኋላ የቆመሱ ምስጋና ከቀረበና ሰላምታ ከተልዋወጡ በኋላ ከተለያዩ የቁምስናው አባላትና ምክር ቤቶች ተገናኝተውና ተወያይተው ወደ መንበራቸው እንደተመለሱ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.