2014-01-15 16:10:18

አገረ ቫቲካን፦ የአልኮል መጠን ሱሰኝነት አደጋ ርእስ ያደረገ ዓውደ ጉባኤ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ጳጳሳዊ የሥነ ምርምር ተቋም ያነቃቃው የአልኮል መጠን ሱሰኝነት፣ ሰበቡና የዚህ ሱስ ተጠቂው የሚያስፈልገው ድጋፍ” በሚል ርእስ ሥር በአገረ ቫቲካን መካሄዱ ጉባኤውን የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኰ ገለጡ።
ቅጥ አልቦ የአልኮል መጠት አዘውታሪ መሆንና የአልኮል መጠን ጥገኛ ወይንም ሱሰኛ መሆን ለገዛ እራስ ለማኅበርሰብ ለቤተሰብ አቢይ ችግር መሆኑ የተካሄደው አውደ ጥናት በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሳንቸስ ሶሮንዶ እንዳመለከቱ ሲገለጥ፣ በስብሰባው የተሳተፉ የኢጣሊያ የሥነ አልኮል ሱሰኛነት በሽታ የሚከታተለው ማኅበር ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር ኤማኑኤል ስካፋቶ ካቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የአልኮል ሱሰኝነት በሽታ እጅግ የተስፋፋ አስቸኳይ ክትትል የሚያሻው አንገብጋቢ ሰብአዊና ማህበራዊ ሰባአዊ ችግር ነው። ስለዚህ የአልኮል መጠጥ ሱሰኛነት በሽታ ነው። በሽታ ከሆነ ደግሞ በሽታው ለመፈወስ የሚደግፍ የሥነ ሕክምና ምርምር በተለያየ መልኩ በማራመድ በሽታው ለመፈወስ የሚደረገው ጥረት ማፋጠን ያስፈልጋል። የአልኮል መጠጥ ሱሰኝነት ብዙውን ጊዜ መለየቱ ያዳግታል፣ ቀን በቀን የአልኮል መጠጥ ማዘውተር ለዚህ አደጋ እንደሚያጋልጥ መሆኑ በተለያየ መልኩ ዘመቻ ማካሄድ አስፈላጊ ነው። ቀን በቀን ካለ ማቋረጥ የአልኮል መጠጥ መውሰድ አንዱ የመጀመሪያ የዚህ ለሽታ የሚያጋልጥ ምልክት ነው ብለዋል።
በተካሄደው ዓውደ ጥናት የኢጣሊያ የጤና ጥበቃ ሚኒ. ቤአትሪቸ ሎረንዚኒ መሳተፋቸውም ሲገለጥ፣ ባሰሙት ንግግር የኢጣሊያ መንግሥት በዚህ በሽታ የተጠቁት መደገፍ ብቻ ሳይሆን ወደ የአልኮም መጠጥ ጥገኝነት ለሚያዘነብሉት ከወዲሁ በተለያየ መንገድ ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት ዘርዝረው፣ የተካሄደው ዓውደ ጥናት ያለው አስፍላጊነት ጠቅሰው በኢጣሊያ በትምህርት ቤቶች በተለያዩ የሕንጸት ተቋሞች ሁሉ በጠቅላላ ሱሰኝነት የሚያስከትለው ጉዳት ተገቢ ሕንጸት ማቅረብ የሱሰኝነት ችግር ቀድሞ ለመከላከል ድጋፍ መሆኑ እንዳመለከቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናንኮ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.