2014-01-13 16:40:01

ር. ሊ .ጳ . ፍራንሲስ 19 አዲስ ካርዲናሎች መሰየማቸው አስታወቁ ፡


ሥርዓተ ላቲን ትናትና የመድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ተከብሮ ውለዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅዱስ ጵጥሮስ አደባባይ ከትገኙ ምእመናን እሁዳዊ መልእከ እግዚአብሕር ደግማዋል ። ቅድስነታቸው ከምእምናን ጋር መልእከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ ፊታችን ወርሀ የካቲት 22 ቀን የካርዲናሎች ጉባኤ በሚካሄድበት ግዜ 19 አዲስ ካርዲናሎች እንደሚሰየሙ ገልጠዋል።ከ19ኙ አዲስ ካርዲናሎች 16 የመምረጥ መብት ያላቸው ሶስት የመምረጥ መብት የሌላቸው ማለት ከ80 ዓመት በላይ የሆኑ መሆናቸው ተገልጠዋል። አዲስ የሚሰየሙ ካርዲናሎቹ ከ15 ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው ተመልክተዋል።አዲስ ካርዲናሎቹ ሮማዊት ቤተ ክርስትያን እና በዓለም ዙርያ የሚገኙ አብያተ ክርስትያኖች የሚወክሉ መሆናቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውቀዋል።አዲስ ካርዲናሎቹ የሮማ ጳጳስ ለዓለም አቀፍ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የሚሰጠውን አገልግሎት በበለጠ እንዲተባበሩ ምእመናን እንዲጸልዩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አሳስበዋል።ለካርዲናልነት ከተጠሩ 19 ጳጳሳት እና ሊቀ ጳጳሳት ሁለት ከአፍሪቃ ክፍለ ዓለም በአይቨሪኮስት የአቢጃን ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ጂን ፒየር ኩትዋ እና በቡርኪና ፋሶ የዋጉዱጉ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍሊፕ ወድራጎ ይገኙባቸዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዚች ምድር ላይ ዓቢይ ምሕረት መውረዱ መልእከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜአስታውሰዋል። ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በዮርዳኖስ ወንዝ ኢየሱስ ክርስቶስብ እንዳጠመቀሰማየ ሰማያት መከፈቱ መጽሐፍ ቅዱስ ይመግረናል ያሉት ፓፓ ፍርንሲስ ሚስጢረ ጥመቀት መሰረተ እምነት መሆኑ ገልጠዋል።ሰማየ ሰማያት ባከፈቱ ኖሮ ምድራዊ ሕይወታችን ጨለማ እና ተስፋ አልባ ትቀር ነበር ብለዋል ።ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከምእመናን ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በደገሙበት ግዜ በማያያዝ እንዳሉት ግልጸተ እግዚአብሔር በምድር ዓቢይ የምሕረት የተስፋ እና ብፍርሃን ተጀምረዋል።ከመድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰማየ ሰማያት ተከፈቱ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በክርስቶስ በኩል የማይጠፋ ፍቅር ሰጠ ብለዋል መጽሐፍ ቅዱስን በመጥቀስ ።
ሰማያዊ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሸጋገር እና ከሐጢአቱ ለማገላገል ልጁን ማለት ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር ላከ እሱም አምላክ እያለ ሰውን መሰለ ብለዋል ቅድስነታቸው።ኢየሱስ ክርስቶስ ህዝበ እግዚአብሔር እንድንሆን አደረገ ስለሆነም ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል አለብን አለ ሱ ሕይወታችን ትርጉም አልባ ሆኖ ይቀራል ብለዋል ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ።በመጨረሻም በቅዱስ ጰጥሮስ ለተገኙ ምእመናን ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ተሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.