2013-12-23 16:07:01

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቃልና በሕይወት ቃለ ወንጌል መስካሪ


RealAudioMP3 በሕፃነ ኢየሱስ ሕክምና ቤት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባካሄዱት ጉብኝት የጽሑፍ ንግግር ያሰማሉ የሚለው እንደ ማንኛውም ዓይነት ጉብኝት ሳይሆን የእሳቸው እዛው መገኘት በአካል የሰጡት ምስክርነት ወንጌል በሕይወት አብሳሪ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ከመሆኑም ባሻገር ከሕፃናቱና ከወላጆቻቸው ጋር ያሳዩት ቅርበት ለሁሉም ያላቸው ጽኑ ቅርበት የሚያረጋግጥ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አልሳንድሮ ጋራሺ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ስለዚህ እውነተኛው የቅዱስ አባታችን ንግግር በወረቀት ተጽፎ የሚነበብ ሳይሆን የተጻፈውን ወርቀት ወደ ጎን በማድረግ በነጻ በአካል መገኘት ጥልቅ ኃያው መልእክት በመሆኑ የሚሰጡት ምዕዳን ማራኪና ልብን የሚነካ ነው። ከግኑኝነት በኋላ፦ አለ ምንም ቃል እጃችንን በመጨበጥ በአይናችንን በመመልከት፣ እራሳችንን በመዳበስ ያሳዩት ቅርበት ከቃል በላይ የሚናገር ጥልቅ የፍቅርና የቅርበት ምስክርነት ነው” በማለት ወላጆች ሲገልጡዋቸው፣ የታማሚ ሕፃናት የማገገሚያ የጽኑ ፍወሳ ክፍል ኃላፊ የሕክምና ሊቅ አንድረያ ዶታ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከሕፃናት ወላጆቻቸው ጋር በመገናኘት በማይድን በሽታ ለታመሙት የምትሰጡት የሕክምና አገልግሎት ብዙውን ጊዜ መድኃኒት ካለ መገኘቱ ምክንያት ውጤት ባያስገኝም። በምንም ዓይነት ተአምር ግዚያችሁን እያባከናቸው እይደላችሁም፣ ለሕፃናቱ ቀርቦ የተስፋ ምልክት መሆን ለገዛ እራሱ አቢይ ፈውስ ነው። ስለዚህ እናንተ መልካም ዘር እየዘራችሁ ናቸሁ፣ መልካም ምርት የምታፍሱበት የጌታ ጊዜ ይደርሳል። ስለዚህ በርቱ በጸሎት እንተሳሰብበማለት የስጡት ቃል ለሁሉም ለሕክምና ቤቱ ሠራተኞችና የሕክምና ባለ ሙያዎች ብርታት ነው በማለት ገልጠዉታል።
የሕፃናት የጽኑ ፍወሳ ክፍል ቤተ ጸሎት መንፈሳዊ ተጠሪ አባ ልዊጂ ዙካሮ በበኩላቸውም፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በመሰናበት ላይ እያሉ ሁሉ በመራወጥ ሰላም ለማለት ያሳየው ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅርበት የሚደነቅ ነው” ሲሉ የሕፃናት ቤተ ሕክምና አስተዳዳሪ ፕሮፈሰር ጁዘፐ ፕሮፊቲ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለሕክምና ቤቱ አቢይ በዓል ነው። ሐዋርያዊው ጉብኝቱ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አገባብ ያንጸባረቀ ትሁትና ቸር ምንም ዓይነት የጉብኝት ደንብ ወይንም ሥርዓት የተንጸባረቀበት ሳይሆን፣ ጥልቅ ቅርበት የጎላበት የአባትና የልጅ ግኑኝነት የተኖርበት ነበር” ብለዋል።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጠና ለታመሙት ሕጻናት በጽኑ የፍወሳ ሕክምና ለሚገኙት ለሁሉም በሕክምና ቤቱ ለሚያገለግሉት ለታመሙት ሕፃናት ወላጆች ጭምር ጥልቅ የሥነ ፈውስ ጸጋ ነበር በማለት ገልጠውታል።
የሕፃነ ኢየሱስ ሕክምና ቤት በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ያለው ከተለያዩ አገሮች ለሚመጡት ታማሚ ሕፃናት የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥበት ነው። ብቃቱም በሥነ ሕክም ሙያ ላይ ብቻ ሳይታጠር የተሟላ ሰበአዊነት ላይ ያተኮረ ነው። ሕክምና ቤቱ ብቁ የሚያስብለውም የሚሰጠው የተሟላ አገልግሎት ነው በማለት ያልካሄዱት ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.