2013-12-20 15:54:16

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ትህትና ፍርያማ ትዕቢት መካን ያደርጋል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ተለመደው ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ፦ “ትሕትና ፍርያማ ትዕቢት መካን ያደርጋል” በሚል ማእከላዊ ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ እርሱም የእግዚአብሔር በሕይወታችን መገኘት መካን የሆነውን ሕይወታችን ወደ ፍሪያማነት እንደሚለውጠው የሚያረጋግጥ ስብከት ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብዙውን ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ጌታ የሕይወት ጸጋ የሚያድላቸው ብዙ በመካንነት የተጠቁ ሴቶች ታሪክ እናገኛለን በማለት፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዕለቱ ምንባብ ላይ ተንተርሰው በተለይ ደግሞ ወንጌል መካንዋ ኤልሳቤጥ ዮሐንስን ለመገላገል እንደበቃች የሚተርከውን የዕለቱ ምንባበ ወንጌል ላይ በማተኮር ሕይወት ለማፍራት ከማይቻለው ሁኔት ሕይወት እንዲገኝ የሚያደርግ ጌታ፣ መካን በሆኑት ሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ የሕይወት ተስፋ ላልነበራቸውም ጭምር ሁሉ የሕይወት ተስፋ እንዳደላቸው ከመጽሐፈ ሩት የኑሃሚን ታሪክ ጠቅሰው በማብራራት፦ “ጌታ በእነዚያ ሴቶች ሕይወት ውስጥ በመግባት ለእኛ የሚያስተምረን፦ ‘እኔ ሕይወት ለመስጠት የምችል ነኝ’ በነቢያቶች ዘንድም ምንም አይነት ሕይወት የማይበቅልበት ፍሬ የማያፈራ የምድረ በዳነትና የደረቅ መሬት አብነት እናገኛለን፣ ጌታ በዚህ ሁነት በመግባት በመለወጥም ሕይወት እንዲሰጥ ያደርገዋል። ምድረ በዳነት ደናማ ያደርገዋል፣ ምድረ በዳ ሊያብብ ይችላልን? መኻን ሴት ሕይወት ልትሰጥ ትችላለችን? አዎ! የጌታ ቃል አይለወጥም፣ ቃል ገብቶልናል፣ ጌታ ይቻለዋል፣ እንዲቻል አደርገዋል፣ ከእናንተ መኻንነት ሕይወት እንዲፈራ አደርጋለሁ’ ይለናል ድህነት ማለት ይኽ ነው” እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ “… ሁሉ ጸጋ ነው፣ የእግዚአብሔር ሥራ ብቻ ነው ድህነት የሚያሰጠው፣ ድህነት ከእግዚአብሔር ነው። ስለዚህ እኛ ምን ማድረግ ይገባናል፣ ምን ይጠበቅብናል? በቅድሚያ ምድረ በዳነታችንን ማወቅ፣ ሕይወት ለመስጠት የተሳነን ለመሆናችን እውቅና መስጠት፣ ከዚህ በመንደርደር፥ ‘ጌታ ሆይ እኔ ፍሪያማ ለመሆን እሻለሁ፣ ሕይወትን የሚሰጥ ሕይወትን እሻለሁ፣ እምነቴ ፍርያማ እንዲሆን እሻለሁ፣… ጌታ ሆይ እኔ መካን ነኝ የሚቻለኝ ምንም ነገር የለም አንተ ግን ሁሉ ቻይ ነህ፣ እኔ ምድረ በዳ ነኝና አይቻለኝም…ላንተ የሚሳንህ ምንም ነገር የለም’ ማለት ይጠበቅብናል” በዓለ ልደት ከማክበራችን በፊት በእነዚህ በቀሩት ቀናት ውስጥ ይኸንን እንድናስብም አሳስበው በመቀጠልም ትዕቢተኞች እነዚያ ሁሉ ቻይነት የሚሰማቸው በማስታወስና መኻን ያለነበረች ነገር ግን ትዕቢት ተሞልታ የነበረችውን እግዚአብሔር ማወደስ ምንም ማለት መሆኑ ብቻ ሳይሆን በሚያወድሱት ታፌዝ ታላገጥ የነበረቸውን የሳኡል ልጅ ሚልኮል ዘክረው፦ “ትህትና ለፍርያማነት አስፈላጊ ነው፣ ስንቶች ናቸው ቅን ነኝ ባዮች፣ ነበሩ ዛሬም አሉ፣ ለጌታ ‘መካን ነኝ ምድረ በዳ ነኝ ለማለት የሚያበቃ ትህትና ይኑረን’ በዚህ ለበዓለ ልደት በምንዘጋጅበት ወቅት ይኸንን ጸሎታችን እናድርግ፣ ‘የዳዊት ልጅ ሆይ አዶናይ ጥበብ የእሰይ ዘር አማኑኤል ሆይ ና ትህትናን ስጠን የምድረ በዳነት ትህትና የመካን ልብ ትህትና መንፈስ፣ ጸጋን ለመቀበል የሚችል የፍሪያማነት ጸጋ ለመቀበል የሚችል ፍሬና ሕይወት የሚሰጥ አድርግ’ በማለት እንጸልይ” ብለው ያሰሙትን ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.