2013-12-18 16:02:01

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ወንጌላዊ አገልግሎት ለግል ዓላማ ሳይሆን፣ ያለንን ለድሆችና ለድሆች በቃልና በተግባር የሚኖር አገልግሎት ነው


RealAudioMP3 የቅድስት ሥላሴ ገዳማውያን ማኅበር መሥራች ቅዱስ ኹዋን ደ ማታ በሰማያዊ ቤተ የተወለደበት 800ኛው ዓመት እንዲሁም የዚህ ገዳማዊ ማኅበር አዳሽ ቅዱስ ዮሐንስ ባቲስታ ደላ ኮንቸዚዮነ በሰማያዊ ቤተ የተወለደበት 400ኛው ዓመት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለማኅበሩ፦ “ወንጌላዊ አገልግሎት ለግል ዓላማ ሳይሆን፣ ያለንን ለድሆችና ለድሆች በቃልና በተግባር የሚኖር አገልግሎት ነው” በሚል ቋሚ ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር ምግለጫ አስታወቀ።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወንጌልን ማገልገል ማለት ገዛ እራስን ዝቅ ማድረግና ከማንኛው ዓይነት ዕለት በዕለት ከሚኖረው ለገዛ እራስ ጥቅም ከሚለው አስተሳሰብ ዕርቃን ወጥቶ ወንጌልን መኖር ማለት ነው። ሁለቱ ቅዱሳን ገና በሕይወታቸው እያሉ ካለሙት ከወጠኑት ዓይነት መጻኢ ሕይወት የተለየ እግዚአብሔር በለገሰላቸው ጥሪ አማካኝነት ተለውጠው ለተናቁትና ለታረዙት አገልግሎት መላ ሕይወት ለዚህ መንፈሳዊ ዓላማ በመኖር ያሳለፉት ቅዱስ ሕይወት ለሁሉም አብነት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት አብራርተው፣ እነዚህን ሁለት ቅዱሳት የቅዱስት ሥላሴ ገዳማውያን ማኅበር መሥራችና የማኅበር አዳሽንም ዛሬ ስናከብር (እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2013 ዓ.ም.) በተለይ ደግሞ የገዳሙ አባላት በትህትናና ተራ በሆነ ሕይወት የክርስቶስ መስቀል በመሸከም ገዛ እራስን ለማዳን ገዛ እራስ ከድቶ አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሕይወትን በጌታ እጅ በማኖር ጌታ ድንቅ ሥራውን ይቀጥል ዘንድ የሚያሳትፍ ጥሪ ያለው ክብር የሚታሰብበት ዕለት ነው ብለው ሁሉ በዚህች እለት እኔነት ግለኝነት እኔ ባይነት ከግል ድሎት ተላቆ ወደ ዓለም ለመሄድ ብርታት ታንግቦ ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ያለው ደስታ የሚመሰከርበት ዕለት ነው። የተገናኘኸውን ኢየሱስ መመስከር አሳማኝ ማራኪ ሕይወት ነው። ቅድስት ሥላሴ የድኻ ማደሪያ በሥጋና መፍነስ የቆሰለው ፈውስ የሚያገኝበት ቅድስተ ቅዱሳት ነው፣ በቅድሚያ በጸሎት ከዛም ቅድመ ሁነትን በማያውቅ ለራስ ጥቅም በማይል በሚሰዋ ፍቅር አማካኝነት የሚመሰከር ፍጹም ፍቅር ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
“በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማንኛውም ዓይነት ኃላፊነት፣ አገልግሎት ማለት ነው። ስለዚህ በአገልግሎት የሚኖር ኃላፊነትን የሚያሰማ ነው። በመሆኑም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንቀበለው የኃላፊነት ጥሪ፣ ሁሉም አይነት ኃላፊነት ገዛ እራስ በመካድ ለራስ ጥቅም ከሚቆም ዓይነት ኃላፊነት በመላቀቅ በሥልጣን ከፍ ክፍ ብሎ ለማደግ ከሚል የሥልጣን ጥማት መንፍስ ገዛ እራስን እራቁት በማድረግ ከእግዚአብሔር የተቀበልከው ጸጋና ስጦታ ለሁሉም በማገልገል ሕይወቱን ላካፈለን ጌታ ተመስሎ ገዛ እራስን በማካፈል የሚኖርበት ድኾችን የተናቁትን የተነጠሉትን የኅብረተሰብ ክፍል በልዩ ማገልገል የሚል ጥሪ ነው” መሆኑ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት በማሳሰብ፦ “ከተሞቻችን አገሮቻችን ዓለማችን በድኾች የተሞላ ነው፣ ቀን በቀን እናያቸዋለንም፣ ራቅ ብሎ እያየናቸው እንዳላየናቸው ከማለፍ ይልቅ ቀርቦ የተስፋ ቃል ማቅረብ፣ ይኽም ክርስቶስ እንዳደረገው ለማድረግ ተጠርተናል ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት መልእክት የገዳሙ አባላት ስለ እሳቸው እንዲጸልዩ አደራ በማለት “በጸሎታችሁ የሮማ ጳጳሳንና ድኾችን በእኩል በማሰብ አለ ምንም ልዩነት እንደምታስቡም እተማመናለሁ፣ ድኾች በኢየሱስ ሕይወት ፊተኞች በሰው ልጅ ሕይወት የመጨረሻ ናቸው እኛ እርሱን የተቀብልንና የተገናኘን ከሆን እርሱ ፊተኞች ያደረጋቸው ፊተኞች ማድረግ ይጠበቅብናል፣ ጌታችን በድኽነቱ ሁላችንን ባለ ጸጎች አድርጎናል” በማለት ሓዋርያዊ ቡራኬ በማስተላለፍ ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.