2013-12-11 16:30:00

ሶሪያ፦ የታገቱት ነጻ እንዲለቀቁ የሚቀርበው ጥሪ አሁንም እየቀጠለ ነው


RealAudioMP3 የሊባኖስ ብሔራዊ የደህንነት ጥበቃ ጉዳይ አስተዳዳሪ አባስ ኢብራሂም በማአሉላ ከተማ በሊባኖስ እስላዊ አማጽያን ኃይል እጅ የታገቱት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መነኮሳት ነጻ እንዲለቀቁ የቃታር መንግሥት ሸምጋይነት ለመጠየቅ በዶሓ እንደሚገኙ የገለጠው ኤሺያን ነውስ የዜና አገልግሎት አክሎ፣ ኢብራሂም ስለ ታገቱት መነኮሳት እስከ አሁን ድረስ ምንም የታወቀ ነገር አለ መኖሩ መግለጣቸውና፣ ከዚህ ቀድም በሊባኖስ አዛዝ ክልል ተጠልፈው የነበሩት ሺዓውያን መንፈሳዊ ነጋድያን ነጻ እንዲለቀቁ የቃጣርና የቱርክ መንግሥታት ሸምጋይነት ውጤት እንዳሰገኘ ሁሉ መነኮሳቱ ነጻ ለማስለቀቅ ያለው አስተዋጽኦ ተስፋ ያለው መሆኑ አስታውቀዋል።
ጀነራል ኢብራሂም ዶሃ የገበቱ የሊባኖስ ርእሰ ብሔር ሚሸል ስለይማን ለቃጣር መንግሥት ያስተላለፉት መልእክት በመያዝም ሲሆን ይህ በእንዲህ እንዳለም ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዩሃና አስረኛ የታገቱት ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ ባለፈው እሁድ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ጥሪ ማስተላለፋቸውና ሁሉም የውይይትና የሰላም አመክንዮ በማስቀደም ማንኛውም ዓይነት አለ መግባባት አለ አመጽና አለ ጦር መሣሪያ ለመፍታት እንዲቆም አደራ እንዳሉ ያስታወሰው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት፣ በፓትሪያርኩ ጥሪ የማኖናዊ ሥርዓት የምትከተለው በክልሉ የምትገኘው ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ማበራቸውና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የታገቱት መነኮሳት ነጻ እንዲለቀቁ ያላሰለሰ ጥረት ያደርግም ዘንድ ከሊባኖስ የኃይል ምንጭና ውኃ ሃብት ሚኒ. ገብራን ባሲሊ ጥሪ መተላለፉ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.