2013-12-04 16:00:45

ሶሪያ፦ ብፁዕ አቡነ አውዶ ለታገቱት ደናግሎች ለፈጣን ነጻ መለቀቅ ሁሉም እንዲጸልይ


RealAudioMP3 በሶሪያ ለክርስትና እምነት አርማ ተብሎ በሚነገርለት ከዳማስቆ ጥቂት ኪሎ ሜርት ርቆ በሚገኘው ማአሉላ መንደር የአልቃይዳ ተከታይ ነው ተብሎ በሚነገርለት በአል ኑስራ ግንባር አባላት 12 ደናግሎች መታገታቸው የተሰጠው ዜና በሶሪያ የአለፖ የከለዳውያን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በካሪታስ ለሚጠራው የተራድኦ ማኅበር ለሶሪያ ቅርንጫፍ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አንቶይነ ውዶ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የታገቱት አምስት ደናግሎች መሆናቸውና ታጋቾች ደናግል በጣም ሩቅ ወዳልሆነችው ያብሩድ ከተማ ተወስደዋል የሚባለው የተለያዩ የዜና አውታሮውች የሰጡት መግለጫ ጠቅሰው ለደናግሎቹ ፈጣን ነጻ መለቀቅ ሁሉም በጸሎት እንዲተጋ አደራ ብለዋል።
ማአሉላ ከተማ ለክርስትናው አምነት ብቻ ሳይሆን ለሶሪያ ምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በጠቅላላ ለመካከለኛው ምስራቅ አቢይ ታሪካዊ ሥፍራ መሆኑና በዚያ ክልል አሁንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይጠቀምበት የነበረው የአራማይስጥ ቋንቋ ተጠቃሚ ማኅበርሰብ የሚኖርበት በመሆኑ ከዚህ አንጻር ሲታይ ያለው ታሪካዊና ባህላዊ ሃብት ምንኛ አቢይና የመላ ዓለም ቅርስ ነው ብለው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 14 በሚከበረው በበዓለ መስቀል ምክንያት ወደ ማአሉላና ሳይድንያ ክልል የማይጎርፍ ዜጋ አለ ለማለት በጣም ያዳግታል ብለው፣ በሶሪያ ተከስቶ ያለው ግጭት ጸረ ክርስቲያን ዓመጽ ያስከተለ ነው ብሎ ለመናገር በሶሪያ የምትገኘው ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ማኅበረ ክርስቲያ ፍላጎት የለውም፣ ምክንያቱ የቤተ ክርስቲያንና የማኅበረ ክርስቲያን ኅላዌ ለእርቅና ለመቀራረብ መገልገያ መሣሪያ በመሆኑም ነው። እርቅና ሰላም የማኅበረ ክርስቲያ ጥሪ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የመልኪታና አንጽዮኪያ የመላ ምስራቅ የእስክንድሪያና ኢየሩሳሌም መልኪታ መንፈሳዊ መሪ በደማስቆ ዋና መንበራቸው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ግረጎሪዮ ሶስተኛ ላሃም ምንም’ኳ በሶሪያ ያለው ሁኔታ ለሰማዕትነት የሚዳርግ ቢሆንም ቅሉ ማኅበረ ክርስቲያን በገዛ አገሩ ለመኖር የመረጠ ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
በማአሉላ የደም ሰማዕትነት የከፈሉት ሶስት የማኅበረ ክርስቲያን አባላት ሚካኤል ታአላብ አንቶኒዮ ታአላብ እንዲሁም ሳርኪስ ዛክሔምን በማስታወስ የእምነት ሰማእታት ናቸው ብለው፣ በቅርቡ የታገቱት አምስት የኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ተክላ ገዳም መነኮሳት ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ በማስተላለፍ ጥላቻና ቂም በቀል በማንም ማኅበረ ክርስቲያን አባል ዘንድ አለ መኖሩ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው። ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ያካሄዱት ግኑኝነትም አስታውሰው፣ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ነቢያዊ ራእይ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲረጋገጥ የሚያስተላልፉት ጥሪና የሚወስኑት የጸሎት መርሃ ግብሮች አመስግነው፣ ማኅበረ ክርስቲያን የምስልምና ሃይማኖት ተክታይም ሁሉም በገዛ አገሩ በሰላም ለመኖር የሚፈልግ ነው ብለው ከሶሪያ 42 ሺሕ ክርስቲያኖች የሚገኙባቸው 1.2 ሚሊዮን ዜጎች ለስደት መዳረጋቸውና በአገሪቱ ግጭቱ ከተቀጣጠለበት ዕለት ጀምሮ ተራ ምእመናን ክርስቲያን የመከላከያ ኃይል አባላት ካህናትና ደናግል የሚገኙባቸው በጠቅላላ 1,200 ክርስቲያኖች መገደላቸውና ከ 60 በላይ የሚገመቱ አቢያተ ክርስቲያን ውድመዋል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.