2013-12-03 20:08:00

ዘመነ ምጽአት የተስፋ አድማስ ይከፍትልናል፣ በዓለማችን ሰላም እንዲነግሥ ይሁን በኤች አይ ቪ ኤይድስ ለታመሙ ሰዎች ደግሞ ሕክምና እንዲደረግ ይሁን፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ዘወትር እንደሚያደርጉት የዕለቱ ቃለ ወንጌልና አጋጣሚ በመጠቀም ዘመኑ በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ የዘመነ ምጽአት መጀመርያ እኁድ በመሆኑ “ዘመነ ምጽአት የተስፋ አድማስ ይከፍትልናል፣” ሲሉ ምእመናን ከጌታ ጋር የመገናኘትና ከእርሱ ጋር የመጓዝ ደስታን እንዲያገኙ ከገለጡ በኋላ “በዓለማችን ሰላም እንዲነግሥ ይሁን” ሲሉም ታላቁን የሰላም ስጦታ እድንዲሰጠን ጸልየዋል፣ እንዲሁም በዚሁ ዕለት ዓለም አቀፍ የኤች አይ ቪ አይድስ ቀን በመሆኑም “ሁላቸው በኤች አይ ቪ አይድስ የተለፉ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት እንዲያገኙ ይሁን” ሲሉ ተማጥነዋል፣
“በዚሁ ሕመም ለተጠቁ ወገኖቻችን በተለይ ደግሞ ሕጻናትን ቅርበታችን በተግባር እንድንገልጥላቸው ይሁን፣ ይህ ቅርበት ምንም ቃል ተንፈስ ሳይሉ በጸጥታ ሌት ተቀን የሚአይገለግሉ ምስዮናውያንና የጤና ባለሙያዎች በተጨባጭ ያሳዩናል፣ ስለሁላቸውም እንጸልይ ለጤና ጥበቃ ሠራተኞች ሓኪሞችና ለዚሁ መድኃኒት ለማግኘት ስለሚጥሩ እንጸልይ፣ አለምንም ማግለል እያንዳንዱ ሕመምተኛ የሚያስፈልገውን ሕክምና እንዲያገኝ ይሁን ሲሉ ስለ ኤች አይ ቪ አይድስ ሕመምተኞች ከተናገሩ በኋላ ወደ የዕለቱ ቃለ ወንጌልና ዘምና ምጽ አት መለስ በማለት በዚሁ የዘመነ ምጽ አት ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አዲስ ጉዞ ይጀምራል ይህም እጅግ የሚያስደንቅ ሁኔታ መሆኑን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ሁላችን በጉዞ መሆናችን በማወቅ የሚሰማንን መልካም ነገር እንደገና እንድናገኘው ይሁን፣ ቤተ ክርስትያን በጥሪዋና በተል እኮዋ የመላው ዘመደ አዳም የሁሉ ሕዝብና ሥልጣኔ እንዲሁም የሁሉ ዘመ ባህሎች ከግዜ ህዳሴ ጋር በጉዞ ላይ ናት፣ ሆኖም የዚህ ጉዞ ዓላማ የቱ ይሆን ብለን የጠየቅን እንደሆነ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ የጌታ መቅደስ የተደረገው ዓለም አቀፋዊ ወይንም የሁሉ የሰው ልጅ ዘር ጉዞ ነበር፣
“የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ግን የዚሁ ጉዞ ፍጻሜ ሆነዋል የጌታ ግዜም እርሱ ራሱ በመሆን ቃለ እግዚአብሔር ሥጋ ለበሰ፤ ለእኛ ለአዲስ ኪዳን ሰዎች እርሱ ራሱ ዓላማችን እርሱ ራሱ መሪያችን ሆነ፣ ለዚህም በመንፈሳዊ ንግደት የሚገኘው ሕዝበ እግዚአብሔር በእርሱ ብርሃን እየተመራ በዚሁ ብርሃን ደግሞ ሌሎች ወደ የፍትሕ መንግሥት የሆነው የሰላም መንግሥት ሊጓዙ ይችላሉ፣ በዕለቱ ከተነበቡ ቃለ እግዚአብሔር የነቢዩ ኢሳያስ ትንቢት ሁኔታችንን ይመለከታል፣ ለመላው የዓለም ሕዝቦችም ዛሬ ግዜ ደርሰዋል የጦር መሣርያዎች ተሰባብረው የምርት መሥርያዎች ይሁኑ፣ ይለናል፣
“ነገር ግን ይህ ትንቢት መቼ ይፈጸም ይሆናል! ያኔ እንዴት ያለ መልካም ቀን ይሆን ይሆናል፣ ሁሉ የጦር መሳርያ ተደምስሶ የምርት መሣርያ ሆኖ የምናይበት ጊዜ እንዴት ደስ ያሰኛል፣ ይህ እውን እንዲሆን ይቻላል! በተስፋችን እንተማመናለን! የሰላም ተስፋችን ይህንን ትንቢት እውን ሊያደርገው ነው፣ በእያንዳንዳችን የዕለት ኑሮ እንደሚያጋጥመን ሁሌ እንደአዲስ መጀመር እንደገና መነሣት የዚሁ ዓላማና የሕይወታችን ትርጉም ለማግኘት እንዲሁም የመላው ዘመደ አዳም ቤተሰብ ትርጉም ለመረዳት የኅበረት አድማሳችን የተስፋችን ጉዞን ማሳደስ ያስፈልገናል፣
“የተስፋ አድማስ!ጉዞአችንን የሚያሳምረው ይህ አድማስ ነው፣ ዛሬ የምንጀምረው የምጽአት ዘመን ይህንን የተስፋ አድማስ እንደገና ይሰጠናል፤ ይህም ተስፋ የማያታልልና የማያደናግር ተስፋ ነው ምክንያቱም በእግዚአብሔር ቃል የተመሠረተ በመሆኑ ነው፣ እግዚአብሔር ቃሉንና ኪዳኑን ስለማይክድ ይህ ተስፋ ሊያደናገረን ፈጽሞ አይቻለውም፣ ለዚህ ዓይነት የሕይወት ጉዞ ምሳሌ ልትሆነን የምትችል እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፣ እርሷ የአንድ መንደር ትንሽ ልጅ ሆና መላው የእግዚአብሔር ተስፋን በልቧ ይዛ ትጓዝ ነበርች፣
“የእግዚአብሔር ተስፋ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በማኅጸንዋ ሥጋ ለበሰ፣ ሰው ሆኖም ታሪክ ሰራ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ የእመቤታችን መዝሙር በጉዞ የነበረው የእግዚአብሔር ሕዝብ እና በእግዚአብሔር ተስፋ የሚያደርጉ የሁሉ ዘመናት የሰው ልጆች መዝሙር ሆኖ በእግዚአብሔር ምሕረት በመተማመን ተዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር እያሉ ይዘምራሉ፣ እርሷ እናታችን በመሆንዋ እንዴት አድርጋ እንድምትመራን ስለምታውቅ በዚሁ የመጠባበቅ ዘመን እርሷ እንድትመራን ይሁን ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.