2013-11-22 14:40:02

የማእከላይ አፍሪካ ብፁዓን ጳጳሳት፦ በኅብረተሰብ የቤተሰብ ማእከልነት


RealAudioMP3 በጋቦን ሊብረቪለ ከተማ “በማንኛውም ቤተሰብአዊ ጅማሬዎች ማእከል የእግዚአብሔር ፈቃድ ማኖር” የሚል ጥሪ ያስተላለፈው የአፍሪካ መካከለኛው ክልል አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጉባኤ መጠናቀቁ አፒክ የተሰየመው የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
በተካሄደው ጉባኤ የመካከለኛ አፍሪካ ክልል አገሮች ማለትም ከካሜሩን ኮንጎ ከጋቦን ከኤኳቶሪያል ጊኒ ከማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪካ ከቻድ የተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ልኡካን ካህናት ገዳማውያን ደናግል መሳተፋቸው የገለጠው አፒክ የዜና አገልግሎት አክሎ፣ ጉባኤው ቤተሰብ በአፍሪካ የተደቀነበት ተጋርጦና ሥጋት እርሱም የተፋች ብዛት ማደግ፣ ግብረ ሶዶማዊ ስሜት ምርጫ፣ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሴቶች እርግዝና፣ አደንዛዥ እጽዋት መስፋፋት፣ ወላጆች በወላጅ ኃላፊነታቸው መዛል፣ የምሥጢረ ተክሊል ሕንጸት መስጫ ተቋሞች እጥረት፣ የጥሪ ሕንጸት መስጫ ተቋሞች እጥረት ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንዳካሄደ ገልጦ ቤተሰብ በመጽሐፍ ቅዱስ ሥር ሰፊ ትንተና የተሰጠበት፣ ቤተሰብ የሱታፌ ምርጥ ስፍራ መሆኑ የሚሰዋ እወተኛው ፍቅር መግለጫ ሥፍራ መሆኑ የተሰመረበት እንደነበርም ገልጦ በመጨረሻም ጉባኤው ቤተሰብ ለመበታተን ለመለያየት አደጋ የሚያጋልጡ ችግሮች በመለየት በጥልቀት በመወያየት ለዚህ መፍትሔ ይሆናል የሚለውን በመካከለኛው የአፍሪካ ክልል አገሮች በሐዋርያዊ ግርበ ኖልዎ አማካኝነት በማቅረብ ቤተሰብ የኅብረሰብ ማእከል መሆኑ ማረጋገጥ የሚል ውሳኔ ማስተላለፉ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.