2013-11-08 14:38:54

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ ጳጳሳዊ የሥነ ግኑኝነት ስልት በዓለም አቀፋዊነት ትሥሥር


RealAudioMP3 “ጳጳሳዊ የሥነ ግኑኝነት መላ ዓለም አቀዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት ዓለም” በሚል ርእስ ሥር ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የደረሱት በቫቲካን ማተሚያ ቤት የታተመው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የመቅድም ጽሑፍ የተኖርበት መጽሐፍ እ.ኤ.አ. ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን የሲኖዶስ አዳራሽ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ 5 ሰዓት በይፋ ለንባብ እንደሚቀርብ ሲገለጥ፣ ይኽ መጽሐፍ የብፁዕነታቸው ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ሆነው ያገለገሉበት ዓመታት ክንዋኔዎች ያስተላለፉት መልእክት ያስደመጡት ንግግር እንዲሁም በተለያዩ ዓለም አቀፍ ነክ ርእሰ ጉዳዮች ለምሳሌ ስለ ዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ሰብአዊ ቤተሰብ በጥልቀት የነኩት ጉዳዮች ስለ ሰላም ጉዳይ፣ ልማት የሰብአዊ መብትና ክብር የሃይማኖት ነጻነት፣ ከሉኣላዊነት ባሻገር የሚረጋገጠው ውህደት በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ሥር ሰፊና ጥልቅ አስተንትኖ ያካተተ በሰው ልጅ አናሥር ማለትም በኑባሬ ያለው የቤተሰብአዊነት ባህርይ የሁሉም እጦቢያዊ መልካም በሚል አገላለጥ ወድማማችነት በማስቀደምና በመኖር በዚህ ባህል መመራት የሚሰጠው ውጤት በስፋት የሚያብራራ መጽሓፍ መሆኑ ከወዲሁ የቅድስት መንበር መግልጫ ይጠቁማል።
መጽሐፉ በይፋ ለንባብ ለማቅረብ የሚከናወነው አጭር ዓውደ ጥናት በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚመራና የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ የኮናርድ አደናወር ማኅበር ሊቀ መንበር የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ነበር ሃንስ ገርት ፖይተሪንግ በጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበር ጥበብ ዓለም አቀፍ የሥነ ደንብና ሥርዓት መምህር የሕግ ሊቅ ቪቸንዞ ቦኖሞ መጽሐፉ በማስደገፍ አጭር አስተምህሮ እንደሚያቀርቡ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ግኑኝነት የመጽሐፉ ደራሲ ብፁዕ ካዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በሚያሰሙት የሰላምታ ቃል እንደሚጠናቀቅም አስታውቀዋል።
መጽሐፉ ቅድስት መንበር በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ (በተባበሩት መንሥታት ድርጅት) የአገሮች የሥነ ግኑኝነት መላና የጳጳጳሳዊ የሥነ ግኑኝነት መላ ልኡካን (የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን)፣ ለሰላም ቅድመ ሁኔት መገንባት (ግንባታ)፣ የመብትና ግዴታ ደንብ መሠረት የሰው ሰብአዊ መብትና ፈቃድ፣ ዓለም አቀፍ ዋስትና ለሃይማኖት ነጻነት፣ ለህዝቦች እድገት ያቀና አሳቢ የጋራ መከፋፋል ተግባር፣ ኤውሮጳ በውህደት ጎዳና በተሰኙት 7 አንቀጾች የተከፋፍፍለ መህኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.