2013-11-06 16:01:28

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤና ገዳማዊ ሕይወት


RealAudioMP3 በኢጣሊያ የተለያዩ መንፈሳዊና ገዳማዊ ማኅበራት ጠቅላይ አለቆች ማኅበር ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤና ገዳማዊ ሕይወት” በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምረው በፓዶቫ ከተማ እያካሄዱ መሆናቸው ሲገለጥ፣ በኢጣሊያ የመላ ገዳማዊና መንፈሳዊ ማኅበራት ጠቅላይ አለቆች ማኅበር ሊቀ መንበር አባ ልዊጂ ጋይታኒ በመካሄድ ላይ ስላለው ዓውደ ጥናት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመደጋገም እንዳሉት ከ 50 ዓመት ዝክረ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በኋላ በርግጥ መንፈስ ቅዱስ በጉባኤው የተናገረውን ፈጽመናል እየፈጸምን ነን ወይ” የሚለው ጥያቄ ቤተ ክርስቲያን በተለያየ ዘርፎችዋ አማካኝነት የምታቀርበው ጥያቄ ነው። ገዳማት ማኅበራት ልኡካነ ወንጌል ጭምር የሚኖሩት ጥሪ ከቫቲካን ጉባኤ በተዛመደ መልኩ በመመልከት፣ መንፈስ ቅዱስ የተናገረውን ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያን በመግባት ለየት ባለ መልኩ የተናገረውን ሁሉ በማጤን ቤተ ክርስቲያን በውስጥዋ ያሉት የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራትና ገዳማት ህዳሴና በአዲስ መልክ የተቀበሉት የማኅበራዊ መንፈሳዊ ሃብት መሠረት ቀጣይነቱ በማረጋገጥ በበለጠ በምንኖርበተ ዓለም እንዲጎላ ለማድረግ መሆኑ ገልጠዋል።
መለኮታዊውና ሰብአዊ የሚያገናኘው የዚያ እጽብ ድንቅ እግዚአብሔር ትስብእት የድህነት ምንጭና መሠረት የሆነውን እውነት ሃሳብ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር በዕለታዊ ሕይወት እንዴት መኖር እንደሚገባው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የሚያንጸባርቅ እየሰጡት ያለው ሥልጣናዊ አስተምህሮ ምዕዳን ለገዳማት መንፈሳዊ ማኅበራት ህዳሴ መሠረት የሆነውን ለይቶ የሚወያይ ዓውደ ጥናት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.