2013-10-29 11:55:02

በኅብረት የሚጸልዩ ቤተ ሰቦች ለሁሉም የእግዚአብሔር ደስታ ያበርካታሉ፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለቤተ ሰብ ቀን ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባደረጉት ስብከት የሚጸልዩ ቤተ ሰቦች ለሁሉም የእግዚአብሔር ደስታ ያበርካታሉ ብለዋል፣በዚሁ የእምነት ዓመት ከተዘጋጁ የተለያዩ ፕሮግራሞች አንዱ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የተደረገው የቤተ ሰብ ቀን ነበር፣
ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለይ ደግሞ ከጣልያን አገር የተሰበሰቡ ቤተ ሰቦች ከነልጆቻቸው የሚገኙባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይና ባሲሊካ ድረስ ሲመጡ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ ዘጠኝ ሰዓት ደግሞ በአደባባዩ በተለያዩ ቦታዎች መንበረ ኑዛዜዎች ተዘጋጅተው ስለነበር በብዛት ይናዘዙ ነበር፣ ቅዱስነታቸው የመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ አስር ሰዓት ተኩል ተጀመረ፣ በአደባባዩ በነበረው መንበረ ታቦት የነበረው ስ ዕል የቅድስት ቤተሰብና የኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት የሚያመለክቱ ነበር፣ በዕለቱ የተነበቡ የቅዱስ መጽሓፍ ክፍሎች ቅዱስነታቸው ስለቤተሰብ በሶስት ነጥቦች አትኵረው እንዲሰብኩ አደረጋቸው፣ ቅዱስነታቸው የመረጥዋቸው ሶስት ቍልፍ ቃሎች ደግሞ ጸሎት እምነትና ደስታ የሚሉ ነበር፣
አንደኛው ን ኡስ አር እስት የምትጸልይ ቤተ ሰብ የሚል ሆኖ በዕለቱ ቃለ ወንጌል ጸሎት እንዲያሳርጉ ወደ ቤተ መቅደስ ስለሄዱ ስለ አንድ መጸባሓዊና ስለ አንድ ፈሪሳዊ ኢየሱስ ያቀረበው ምሳሌ ነበር፣ ፈሪሳዊው በት ዕቢት ጌታን ሲያመሰግን መጸባሓዊው ግን ገና በቤተ መቅድሱ መግባት ሲጀምር በግንባሩ ተደፍቶ ጌታ ሆይ ኃጢአተኛ ለሆንኩኝ ለኔ ይቅር በለኝ ብሎ በመጸልዩ ከፈረሳዊው ይልቅ መጸበሓዊው ጸጋ አግኝቶ እንደተመለሰ ይናገራል፣
“በዚሁ ቃለ ወንጌል መሠረት እናንተን ውድ ቤተ ሰበቦች ለመጠየቅ እፈልጋለሁ! በቤተ ሰብ አንዳንዴ ትጸልያላችሁ ወይ? አንዳንድ ይገኙ ይሆናል፧ ነገር ግን ብዙ ሰዎች በቤተሰብ እንዴት ይጸለያል? ብለው ይጠይቁኛል፣ መልሱ በዛሬው ወንጌል እንዳገኘነው እንደ መጸበሓዊው በእግዚአብሔር ፊት በትሕትና መቅረብ ነው፣ እያንዳንዳችን በትሕትና ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ ምሕረቱን እንጠይቅ እርሱም ምሕረቱን ይሰጠናል፣ በቤተሰብስ እንዴት ይደረግ ይሆናል? ለምንድር ነው ጸሎት የግል ጉዳይ ብቻ የሚመስለው የባሰውኑ ደግሞ በቤተሰብ ውስጥ ለጸሎት የሚሆን ሰላማዊና ጸጥታ የሰፈነበት ጊዜ የማይገኝ ለምንድር ነው? እውነትም እንደዚህ ነው ነገር ግን የትሕትና ጉዳይ ሳይሆን አይቀርም? እንደመጸባሓዊው ዝቅ ብለን ትሕትና ለብሰን እግዚአብሔር እንደሚያስፈልገን ማወቅ ያስፈልጋል፣ ባጠቅላይ ሁሉም ቤተሰብ እግዚአብሔር ያስፈልገዋል፣ ሁላችን የእግዚአብሔር እርዳታ ኃይሉ ቡራኬውና ምሕረቱ ያስፈልገናል፣ ለዚህ ደግሞ ልበንጹሓን መሆን አለብን! በቤተሰብ አብሮ ለመጸለይ ገርነት ያስፈልጋል አብሮም “በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ” ብለን መጸለይ አለብን፣ የማይሆን ከባድ ነገር አይደለም ቀላል ነገርም አይደለም፣ በቤተሰብ አብሮ ጸሎተ መቍጠርያን መጸለይ እጅግ ጣፋጭ ነው ብዙ ኃይል ከእግዚአብሔር ያስገኛል፣ እንዲሁም አንዱ ለሌላው ሲጸልይ! ማለትም ባል ለሚስቱ ሚስትም ለባለቤቷ እንዲሁም ለልጆቻቸው ልጆችም ለወላጆቻቸው ለአያቶቻቸው ሲጸልዩ እንዴት መልካም ነገር ነው አንዱ ለሌላው ሲጸልይ፣ በቤተሰብ ጸሎት ማሳረግ ማለት ይህ ነው እንዲህ የሚጸልይ ቤተ ሰብ ኃይል ያገኛል፣ ጸሎት ይህ ፍሬውና ትርፉ፣
ሁለተኛው ነጥብ እምነት ሲሆን እምነትን የሚጠብቅ ቤተ ሰብ ነው፣ ዛሬ በተነበበው የጳውሎስ መልእክት ወደ ጢሞቴዎስ በጻፈው “ጉዞየን ፈጽምያለሁ እምነቴን ጠብቅያለሁ” ይላል፣ ነገር ግን በአንድ ሳጽን ውስጥ አላስቀመጠውም ወይንም ቆፍሮ በመሬት ውስጥ አላስቀመጠውም፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት ውግ ያ ና ሩጫ ነው የነበረው ሳይፈራና ሳይጠራጠር ቃለ እግዚአብሔርን እስከ አለም ዳርቻ ለማዳረስ እስከ መጨረሻ ታግለዋል፣ ለዚህም ነው ሩጫየን ፈጽምያለሁ እምነቴን ጠብቅያለሁ ያለውም ለዚህ ነው፣
“እዚህ ላይም ሌላ ጥያቄ ማቅረብ እንችላለን! እምነታችን እንዴት አድርገን ነው የምንጠብቀው? ለገዛ ራሳችን ለቤተሰባችን እንደየግል ጉዳይ ነው የምንይዘው ወይንስ ምስክርነታችን በመስጠት ልባችን በመክፈትና ሌሎችን በመቀበል ከሌሎች ጋር እንከፋለዋለን? የክርስትያን ቤተሰቦች ሰባክ ያነ ወንጌል ናቸው ወይ? በየዕለቱ በሚያካሄዱት የሕይወት ጉዞ ቤተሰቦች ሰባክ ያነ ወንጌል መሆን አለባቸው፧ ለሁሉም የእምነት ጨውና እርሾ መሆን አለባቸው፣ በቤተሰብ እምነትን መጠበቅ ማለት በየዕለቱ በሚያካሄዱት ጉዞ የእምነት ጨውና እርሾን መጨመር ነው፣
በመጨረሻም በደስታ የሚኖር ቤተሰብ እንዴት ያለ ነው፣ እንደምታውቁት ደስታ ስሜታዊና የውጭ ማሸብረቅ አይደለም ነገሮች በመከማቸትም አይገኝም፣
“ዛሬ አንድ ጥያቄ ላቅርብላችሁ እወዳለሁ! እያንዳንዳችሁ እንደየቤት ሥራችሁ በልባችሁ በቤታችሁ ደስታ ይዛችሁ ትጓዛላችሁ ወይ? በየቤታችሁ ደስታ እንዴት አለች? በቤተሰቦቻችሁ ደስታ እንዴት አለች? መልሱ እናንተ ስጡኝ፣ እውነተኛ ደስታ በሰዎች መካከል ባለው ጥልቅ ውህደትና ግኑኝነት ሁላቸው በልባቸው ይህ ሲሰማቸው አብረው በመኖራቸው ደስ የሚላቸው እርስ በእርስ በመደጋገፍ ይገኛል፣
“እንዲህ ሆኖ በሚሰማን ጥልቅ ደስታ እግዚአብሔር በቤተሰብ እንዳለና መሠረት ሆኖ ሁሉን የሚያቅፍ ፍቅር ምሕረትና እርስ በእርስ መከባበር ያስገኛል፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ የትዕግሥት ፍቅር፤ ትዕግሥት እግዚአብሔር የሚሰጠን ኃይል ሆኖ በቤተሰብ አንዱ ከሌላው ይህ ታጋሽ ፍቅር እንዲኖር ያስተምረናል፣ በመካከላችን ትዕግሥት እንዲኖር ያስፈልጋል፣ የእምነት ደስታን እያጣጣመ የሚኖር ቤተሰብ የምድር ጨውና የዓለም ብርሃን በመሆን የኅብረተሰቡ እርሾ ይሆናሉ፣ ሲሉ ከሰበኩ በኋላ ለቅድስት ቤተሰብ ስለመላው የዓለም ቤተሰቦች እንዲህ ሲሉ ጸሎት አሳርገዋል፣
“የናዝሬቲቱ ቅድስት ቤተ ሰብ የቤተሰብ ቅዱስና የማይነካ ባህርይ በመላው ኅብረተሰባችን እንዲታወቅ እንዲሁም እያንዳንዱ ቤተሰብ የበጎ ነገርና የሰላም መኖርያ እንዲሆን ትረዱን ዘንድ እለምናለሁ፣ ሲሉ ጸሎት አሳርገዋል፣


ይህ በእንዲህ ሳለ ቅዳሜ ማታ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የቤተሰብ ቀንን ለማክበርና ጸሎተ ዋዜማ ለማሳረግ ከ70 አገሮች በላይ ለመጡ በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምእመናን ቅዱስነታቸው ባደረጉት አስተምህሮ “ከክርስቶስ ጋር አንድ ሁኑ ምክንያቱም ፍቅር ከሌለ ደስታም የለም፤ ወላጆች አብረው እንዲጸልዩ ይሁን እንዲሁም በማኅበረክርስትያንም ይጸልዩ ምክንያቱም የኢየሱስ እርዳታ ከማንኛው ጊዜ አሁን ስለሚያስፈልጋቸው እንዲህ በማድረጋቸውም በየዕለቱ አንዱ ሌልውን ሊቀበል ይቅር ማለትም ይችላሉና” ሲሉ አስተምረዋል፣
በአደባባዩ ተሰብስበው ለነበሩት ብዙ ሕጻናትና ወላጆች “ይህ አደባባይ እጁን ዘርግቶ ይቀበላችኋል! የሚያፈቅረንና የሚደግፈን እግዚአብሔር የሰበስበን፤ አንድ ነፍስ ብቻ ያለችን አንድ ሕዝብ ነን” ሲሉ ከተቀበልዋቸው በኋላ የንግደቱ ርእስ የነበረው ሓረግ “ቤተሰብ የእምነት ደስታን ትኑር” መነሻ በማድረግ እውነት ነው ዛሬ ኑሮ ከባድ ነው፣ ሥራ መሥራት ያደክማል ሆኖም ግን ከሁሉ የከበደውኑ የከፋው በቤተሰብ ፍቅር ሲጐድል ነው፣ አንዳንዴ በቤተሰብ ውስጥ ባልና ሚስት ልጆችና ወላጆች ምንም የማይነጋገሩበት ጸጥታ የሰፈነበት ሁኔታ ያጋጥማል፣ የባሰውኑ ደግሞ ሽማግሌዎች አያቶች ብቻቸውን ማንም የሚያነጋግራቸው የሚረዳቸው የሌለበት አጋጣሚም ሞልተዋል፣ ግን ለደከሙ ለተቸገሩ እርዳታውን ለመስጠት የሚጠባበቀን ጌታ አለ እርሱም “እናንተ የደከማችሁና ሸክም የከበዳችሁ ወደኔ ኑ እኔ አሳርፋችኋለሁ” ስላለን ወድ ኢየሱስ እንሂድ፣
“ኢየሱስ በወንጌል ደስታችሁ የተትረፈረፍ እንዲሆን ብለዋል፣ ስለዚህ ኢየሱስ ደስታችን የተትረፈረፈ እንዲሆን ነው የሚፈልገው፣ ለሓዋርያት እንደዛ ብሎ ነገራቸው ዛሬም ለእኛ ይደግመዋል፣ ስለዚህ ዛሬ ማታ ማድረግ ያለብን የመጀመርያው ነገር ይህ ነው በሌላ አነጋገር ኢየሱስ ለቤተሰቦች እንዲህ ይላል “እናንተ የመላው ዓለም ቤተሰቦች ደስታችሁ የተትረፈረፈ እስኪሆን ድረስ ወደኔ ኑ፣ ይለናል ይህችን ቃል እያንዳዳችሁ ወደ ቤታችሁ ይዛችሁ ሂዱ እንዲሁም ብልቦቻችሁ ያዟት በቤተ ሰብም ተካፈልዋት፣ ደስታ እንዲሰጣችሁ እንዲሰጠን ጥሪ ያቀርብልናል፣ ካሉ በኋላ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በሰርግ ጊዜ የገባውን ቃለ መሃላ እንዲያስታውስ በደስታም ይሁን በሥቃይ አብሮ ለመጓዝ እንደ የእምነት አባታችን አብርሃም እጅ ለእጅ ተያይዞ በእምነት መጓዝ ነው፣
“እጅ ለእጅ ተያይዞ ለዘላለም ለመላው የኑሮ ዘመን መጓዝ ነው! ባለነው ዘመን የሚታየውን የግዝያውነት ባህልን ጣሉት! በዚሁ እምነትን በእግዚአብሔር በመተማመን ሁሉን አለፍርሃትና በኃላፊነት መጋፈጥ ይቻላል፣ የክርስትያን ቤተሰቦች በሕይወት ያሉ ውጣ ውረዶችን ያውቃሉ ሆኖም ግን በእግዚአብሔርና በማኅበረሰብ ፊት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ፍርሃት የላቸው! አይሸሹም አይርቁም ሲሉ ቤተሰቦች በምሥጢረ ተክሊል ጸጋና አብሮ በመጸለይ ያ የተትረፈረፈ ደስታን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.