2013-10-17 09:30:50

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እግዚአብሔርን እናመልካለን ጣዖት አምላኪያንና አስመሳዮችም እንዳንሆን ጎረቤታችንን እናፍቅር


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ተለመደው ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማራታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የዕለቱ የቅዱስ መጽሓፍ ንባባት ላይ ተንተርሰው ባስደመጡት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “ጣዖት ማምልክ ኃጢኣት ነው፣ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ‘እግዚአብሔርን አውቀዉት እያሉ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔርነቱ ምስጋናም ሆኖ አክብሮት አላቀረቡለትም’ ይላል፣ ፈጣሪን ከማምለክ ይልቅ ፍጡራንን ማምለክ ይመርጣሉ፣ ይኽ ዓይነቱ ጣዖታዊው አምልኮም እግዚአብሔር ፍትሃዊነቱን የሚገልጥበት እውነተኛውን እምነት ያፍናል፣ የእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ በውስጣችን ታትሟል ስለዚህ እርሱን ማምለክ ይገባናል፣ ያስፈልገናልም፣ እግዚአብሔርን ሳናመልክ ስንቀር ፍጡራንን እናመልካለን። ጣዖት አምላክያን እግዚአብሔርን ያወቁ ሆነው እያሉ እርሱን እንደ እግዚአብሔርነቱ አላከበሩትም አልወደሱትም የጣዖት አምላኪነት መንገድ የትኛው ነው? በብኩን አስተሳሰባቸውና ምክንያታቸው ተውጠው ቀሩ፣ ያገደደውና የጨለምተኛው አእምሮ የጣዖት አምላኪነት መንገዶች ናቸው። ወደ አምልኮ ጣዖት የሚመሩ ናቸው። የገዛ እራስ አስተሳስብ ልቅ ወዳድነት የዚህ የእኔው አስተሳሰብ ከሃሌ ኩሉ ነው። የእኔ አመለካከት ብቻ ነው እውነት፣ እኔ እውነት አሳቢ ነኝ፣ እኔ እውነትን በገዛ እራሴ አስተሳሰብ የምፈጥር ነኝ። የተሰኙት መንገዶች የጣዖት አምላኪነት መንገዶች ናቸው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።
“ዛሬም ቢሆን ብዙ ጣዖቶችና ብዙ ጣዖት አምላኪያን አለን። ጥበበኞች ነን ባዮች፣ ገዛ እራሳቸው ጥበብ አድርገው የሚገምቱ፣ ከእኛ መካከልም ይኖራሉ፣ በክርስቲያኖች መካከልም ይኖራሉ፣ እኔ እነዚያ ክርስቲያን ስላልሆኑ አይደለም እምናገረው ያለሁት አከብራቸዋለሁ፣ በእኛ መካከል ስላሉት ነው እምናገረው ያለሁት፣ በእኛ መካከል ያሉት ገዛ እራሳቸውን ጥበብ አድርገው ስለ ሚያስቡት ነው እምናገረው ያለሁት፣ ያንን የማይለወጠውን የእግዚአብሔርን ክብር በገዛ እራሳቸው እኔነትና በገዛ እራሳቸው አስተሳሰብ ይተኩታል፣ ለገዛ እራሳቸው እንዲመቻቸውና፣ ጣዖት አምላክያን ጉዳይ ያለፈ ታሪክ አይደለም፣ ዛሬም በመንገዶቻችን ጣዖቶች አሉ፣ ሁላችን በልባችን የደበቅናቸው ተናንሽ ጣዖቶች ይኖሩን ይሆናል፣ በእግዚአብሔር ፊት የተደበቀው ጣዖቴ የተኛው ነው ማን ነው፣ ብለን በፊቱ ሆነን እንጠይቀው፣ የጌታን ቦታ የተካው ጣዖታችን ማን መሆኑ በጌታ ፊት ሆነን እንጠይቅ” ካሉ በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ጣዖት አምላክያንን ሞኞች በማለት እንደሚጠራቸውና ኢየሱስ በፈርሳውያን እነዚያ መምህር በማእድ ከመቀመጡ በፊት እጆቹን ባለ መተጣቡ ምክንያት ለሚሰናከሉት እንቅፋት ለሚሆንባቸው አካል ስለ ለበሰው አስመሳይና ፈሪሳዊ በሆኑት ፊት ኢየሱስ ውጫዊውን የሚያጥቡ ውስጣችው ግን ተንኮልና ስግብግብነት የተሞላው ነው በማለት ስለሚገለጣቸው ይኸንን በውስጣቸው ያለው ምጽዋት አድርገው ቢሰጡ ኖሮ…የሚል ጥልቅ ሃሳብ የተሞላው እስተንትኖ በማስከተል፦ “ኢየሱስ ውጫዊው ነገር አለ መመልከት እንደሚገባን ምዕዳን ያቀርብልናል፣ እጅግ የበለጠው ውጫዊው የምግብ ሳህን ሳይሆን በውስጡ የያዘው ነው። ከንቱነት ወዳጅ ስልጣን ፈላጊ የማይረካ ብዙ የሚጠብቅ በገዛ እራሱ መሆን የመተማመን ከንቱነት ራስ ወዳድ ትምክህተኛነት፣ ፍጹም ባይነት፣ አለፎ አልፎ መጽዋች እርሱም ህሊናውን ለማሳረፍ፣ የጌታችን መንገድ ግን አምልኮ ለእግዚአብሔር ፍቅር ለእግዚአብሔር ከሁሉም በላይ ባለ እንጀራህን ማፍቀር የሚል ይኽ ደግሞ በጣም ቀላል ነገር ግን ከባድ ፍቅር ነው። ይኽ ለመፈጸም የሚቻለው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ስለዚህ ጸጋን እንለምን” ብለው ያሰሙትን ስብከት እንዳጠቃለሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.