2013-10-11 16:11:15

ኤሺያን ነውስ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወንጌላዊ ልኡክነትና ሱታፌን እንድናበራታ ይጠሩናል


RealAudioMP3 ጳጳሳዊ የውጭ ተልእኮ ተቋም ያቋቋመው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት የተመሠረተበት ዝክረ አሥረኛው ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 09 ቀን 2013 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ኡርባኒያኑም መንበረ ጥበብ ልዩ ዓውደ ጥናትና እንዲሁም የዚህ የዜና አገልግሎት ዓላማና የሚሰጠው አስተዋጽኦ የሚያወሳ ስእላዊ መግለጫ ለትርኢት መቅረብም ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወደዚሁ አውደ ጥናት ባስተላለፉት መልእክት፦ ወንጌላዊ የድህነት መልእክት ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ዓለም ይዳርስ ዘንድ የወንጌላዊ ልኡክነት ተግባር የማነቃቃቱ ኃይል እጅግ ማሳየል” በማለት ለሁሉም ተጋባእያን ጥሪ በማቅረብ ቀጥለውም፦ በአቢያተ ክርስቲያን መካከል ሱታፌና የእርስ በእርስ መደጋገፍን የመተባበር ባህል እንዲጎለብት ጠንክሮ ማገልገል አስፈላጊ ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የተካሄደው ዓውደ፦ “እስያ፦ የጋራው የአገልግሎት ኃላፊነት በሦስተኛው ሚለኑዩም” የሚል የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሃሳብ ማእከል በማድረግ የተመሠረተው ይኽ የዜና አገልግሎት በአሁኑ ወቅት በእንግሊዚኛ ጣሊያንኛ በቻይና ቋንቋ የዜና ምንጭ የሚያቀርብ ሲሆን፣ በእነዚህ ቋንቋዎች ሥር የገዛ እራሱ ድረ ገጽ ያለው መሆኑም የዚሁ የዜና አገልግሎት ዋና ኣስተዳዳሪ ኣባ በርናርዶ ቸርቨለራ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፦ “ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎቶ በእስያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ድምጽ ለመስጠትና ስለ እስያ በተመለከተ ለተቀረው ዓለም ለማሳወቅና የወድማማችነት መንፈስ ለማጠናከር ወንጌላዊ ተልእኮ አስፍሆተ ወንጌል ከፍ ከፍ ለማድረግ ነው” ካሉ በኋላ ከዚሁ ጋር በማያያዝ፦ እስያ በተልእኮ ወንጌል አገልግሎት እያደገች ለተቀረው ዓለም አብነት እየሆነች መጥታለች” ሲሉ ጳጳሳዊ የውጭ ወንጌላዊ ተልእኮ ተቋም ጠቅላይ አለቃ አባ ፈሩቾ ብራምቢላስካ በበኵላቸውም፦ ይኽ ጳጳሳዊ የውጭ ወንጌላዊ ተልእኮ ተቋም በልኡካነ ወንጌል ኣቢያተ ክርስቲያንና በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መካከል ግኑኝነት እንዲኖር የሚያገለግል ድልድይ ነው ለማለት ይቻላል። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስተላለፉት መልእክት አገናኝ ድልድይ እንድንሆን የሚያሳስብ ነው” በማለት የሰጡትን ቃለ መልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.