2013-10-02 17:14:12

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! መልካም ቀን ይሁንላችሁ! ጸሎተ ሃይማኖት በምንደግምበት ጊዜ በአንዲት ቤተ ክርስትያን አምናለሁ ካልን በኋላ ቅድስት የሚለውን ቅጽል እንጨምራለን፣ በዚህም ቤተ ክርስትያን ቅድስት መሆንዋን እንመሰክራለን፣ ይህ ቅጽል ቤተ ክርስትያን ስትመሠረት ከጥንት ጀምሮ የተገለጠ የቤተ ክርስትያን ባህርይ ነው፣ በሓዋርያት ሥራ 9፣13.32.41 ላይ እንዲሁም በሮሜ 8.27 እና በአንደኛ ቆሮንጦስ 6.1 ላይ ክርስትያኖች “ቅዱሳን” ተብለው ይጠሩ እንደነበር እናንባለን ምክንያቱም የእግዚአብሔር አብና የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቤተ ክርስትያንን እንደሚቀድስ ይተማመኑ ነበርና፣
ነገር ግን የቤተ ክርስትያን ታሪክን በዘመናት ጉዞ ያየን እንደሆነ ብዙ ችግሮች እንደንበርዋት ጨለማ ግዝያትም እንዳሳለፈች ስንመለከት ቤተ ክርስትያንን ቅድስት የሚያሰኝት ምን ይሆን? በሰዎች የቆመች እንዲያውም በኃጢአቶች የቆመች ቤተ ክርስትያን እንዴት ቅድስት ልትሆን ትችላለች? ሰዎቹ ኃጢአተኞች ሴቶቹ ኃጢአተኞች ቄሶቹ ኃጢአተኞች ደናግሎቹ ኃጢአተኞች ጳጳሳቱ ኃጢአተኞች ካሪዲናሎቹ ኃጢአተኞች ር.ሊ.ጳጳሳቱ ኃጢአተኛ ሁላቸው እንደዛ ኃጢአተኞች ሲሆኑ ቤተክርስትያንዋ እንዴት ቅድስት መሆን ትችላለች?
    ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ቅዱስ ጳውሎስ በኤፈውሶን ወደ ነበሩ ክርስትያኖች ከጻፈው መጥቀስ እወዳለሁ፣ ሓዋርያው በቤተሰቦች መካከለ ያለውን ግኑኝነት እንደምሳሌ በመጠቀም “ክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን ስለወደዳት ቅድስት እንድትሆን ዘንድ ገዛ ራሱን ስለእሷ ሰጠ” (5.25) ይላል፣ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን አፈቀራት ገዛ ራሱም በመስቀል ላይ አሳልፎ ስለሷ ሰጠ፣ ይህ ማለትም ቤተ ክርስትያን ቅድስት ናት ምክንያቱም ቅዱስ ከሆነው እግዚአብሔር ስለምትመነጭ እግዚአብሔርም ለቃሉ ታማኝ ስለሆነ ለሞትና ለክፋት ኃይል አሳልፎ አይሰጣትም (ማቴ 16.18) ቅድስት ናት ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆን (ማር 1.24) ሊወድም በማይችል ትሥስርም ከእርሷ ጋር ተሳስረዋል (ማቴ 28.20)፣ በሚያነጻ በሚለውጥና በሚያድስ መንፈስ ቅዱስ ስለምትመራም ቅድስት ናት፣ ቅድስት የምንላት በሥራዋ ወይንም በችሎታው አይደለም ነገር እግዚአብሔር ቅድስት ስላደረጋት በመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችና ስጦታዎች ቅድስት ናት፣ ቅድስት የምናደርጋት እኛ አይድለንም! ቤተ ክርስትያንን በፍቅሩ ቅድስት የሚያደርጋት እግዚአብሔር ነው! መንፈስ ቅዱስ ነው፣
    ምናልባት እናንተ ነገር ግን በየዕለቱ እንደምንመለከተው ቤተ ክርስትያን በኃጢአተኞች የቆመች ናት ልትሉኝ ትችላላችሁ! አዎ ይህ እውነት ነው፣ የኃጢአተኞች ቤተ ክርስትያን ነን! ነገር ግን ልንለወጥ ልንታደስ ልንቀደስ ፈቃዳችን እንዲሆን በእግዚአብሔር የተጠራል ነን፣ በታሪክ የተመለከትን እንደሆነ አንዳንዴ ቤተ ክርስትያን የንጹሓን ብቻ በሁለመናቸው ፍጹማን የሆኑ ሰዎች ብቻ ናት በሚል እምነት ሌሎችን የማግለል ፈተና አጋጥሞ ነበር፤ ይህ ግን እውነት አይደለም፣ ይህ መናፍቅነት ነው! ቅድስት የሆነች ቤተ ክርስትያን ኃጢአተኞችን አታገልም፣ ሁላችንን አታገለንም! ሁላችንን ስለምትጠራ ማንንም አታገልም፣ ሁላቸውን ትቀበላለች! እጅግ ርቀው ላሉ ሳይቀር ክፍት ናት! በእግዚአብሔር አባታችን ምሕረት ፍቅርና ይቅር ባይነት እንድንለወጥ እና በቅድስና ጐዳና እንድንራመድ ሁላችንን ትጠራለች፣ ምናልባት አንድ ሰው ነገር ግን አባ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ እጅግ ትልቅ ኃጢአት ሰርቼአለሁ እንዴት የዚች ቅድስት ቤተ ክርስትያን አባል እሆናለሁ! ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፣ እኔ ደግሞ ውድ ወንድሜ የተወደድሽው እኅቴ ጌታ ሊሰማ የሚፈልገው ይህን ነው “ጌታየ ሆይ! ከነኃጢአቶቼ እዚህ እገኛለሁ” ልንለው፣ ምናልባት ከእናንተ ጥቂቶች ኃጢአቶቻችሁን ትታችሁ እዚህ ትገኙ ይሆናል ሆኖም ግን እኛ ሁላችን ኃጢአቶቻችንን ተሸክመን ነው የምንጓዘው ነገር ጌታ ልንነግረው የሚፈልገው “ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ! ጉዞየን ለመቀጠል እርዳኝ! ልቤን ለውጠው” ብለን እንድንማጠነው ነው፣ ልባችንን ሊለውጠው የሚቻለው ደግሞ ጌት ነው! በቤተ ክርስትያን የምናግኘው እግዚአብሔር ጨካኝ ዳኛ አይደለም! ነገር ግን ያ በጠፋ ልጅ ምሳሌ በወንጌል የምናነበው መሓሪና ይቅር ባይ አባት ነው፣ ቤቱን ጥሎ የጠፋ ልጅ ከእግዚአብሔር እጅግ የራቅን ልንሆን እንችላለን፣ ወደ አባቴ ቤት ልመለስ እፈልጋለሁ ለማለት ኃይል ባገኘህበት ወቅት ቤቱ ክፍት ሆኖ ይቆያሃል እግዚአብሔር ደግሞ ሁሌ ስለሚጠባበቅ ወዲያውኑ ይቀበለሃል፣ ያቅፈሃል ይስመሃል ታላቅ በዓልም ያደርጋል ይደግሳልም፣ ጌታ እንዲህ ነው! የአባት ፍቅርም እንዲህ ነው፣ ጌታ አንድ የቤተ ክርስትያን ክፍል ሁላቸውን ለመቀበል ክፍት እንዲሆን ይፈልጋል በዚህም ሁላቸው ሊታደሱ ሊለወጡ በፍቅር ሊቀደሱ ይችላሉ፣ ኃይለኞችም ይሁኑ ደካማዎች ኃጢአተኞችም ቸልተኞች ተስፋ የቆረጡም ይሁኑ የጥፉ ሆኖ የሚሰማቸው ሁሉ ይህንን ያገኛሉ፣ ቤተ ክርስትያን ለሁላቸው የቅድስና መንገድን እንዲከተሉ ዕድል ትሰጣለች ይህም የክርስትያን መንገድ ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በምሥጢራት በተለይ ደግሞ በምጢረ ንስሓና ምሥጢረ ጥቀ ቅዱስ ቁርባን እንድናገኘው ታስችለናለች! ቃለ እግዚአብሔርን ታስተላልፈናለች እግዚአብሔር ለሁላችን ባለው ፍቅር ለመኖርም በምግባረ ሠናይ እንድንኖር ታደርገናለች፣ አሁን ወደ ገዛ ራሳቸን መለስ ብለን ልንቀደስ ፈቃደኞች ነን ወይ? ኃጢአተኞችን ለመቀበልና ለማቀፍ ብሎም ብርታትና ተስፋ ለመስጠት የተከፈትን ነን ወይም በገዛ ራሷ የተዘጋች ቤተ ክርስትያን? አንዱ ለሌላ የሚጸለይባት አንዱ ስለሌላው የሚያስባባት የእግዚአብሔር ፍቅር በተግባር የሚታይባት ቤተክርስትያን ነን ወይ ብለን እናሰላስል፣
    የመጨረሻ ጥያቄ! ደካማ ቀሰስተኛ እና ኃጢአተኛ ሆኖ የሚሰማኝ እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ? ብለህ ለመጠየቅ ትችላለህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይለሃል! የቅድስና ፍራቻ አይኑርህ! እግዚአብሔር እንዲያፈቅርህና እንዲያነጻህ ከፍ ወዳለው ነገር ለማለም አትፍራ! መንፈስ ቅዱስ እንዲመራህ ለመፍቀድ አትርፍራ! ማንኛውም ክርስትያን ለቅድስና የተጠራ ነው፣ ቅድስናም አስደናቂ ነገሮች በመፈጸም ሳይሆነ እግዚብሔር በአንተ ላይ እንዲሰራ በመፍቀድ የቆመ ነው፣ በደካማነታችንና በእግዚአብሔር ጸጋ ኃይል መገናኘት የቆመ ነው፣ በፍቅር እንድንኖርና ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብርና ለጓደኛ ፍቅር በደስታና በትሕትና ለመፈጸም በሚአይስችለን የእግዚአብሔር ስራ በመተማመን የቆመ ነው፣ ለዮን ብሏ በሚባ በፈረሳዊው ጸሓፊ በሕይወቱ መጨረሻ ላይ የጻፈው ሓረግ አለ፤ “በሕይወት ውስጥ የሚያሳዝን አንድ ነገር ብቻ አለ እርሱም ቅዱሳን አለመሆን ነው” ይላል፣ በቅድስና ያለንን ተስፋ እንዳናጠፋ ሁላችን ይህንን መንገድ እንከተል፣ ቅዱሳን ለመሆን እንፈልጋለንን? ጌታ ይጠባበቀናል! ሁላችንን እጆቹን ዘርግቶ ይጠባበቀናል፣ በዚሁ የቅድስና ጐዳና እንዲሸኘን ይጠባበቀናል! እምነታችንን በደስታ እንድንኖር ይሁን! ጌታ እንዲያፈቅረን እንፍቀድለት፣ ለገዛ ራሳችንና ለሌሎች ይህንን የጌታ ስጦታ በጸሎት እንጠይቅ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣









All the contents on this site are copyrighted ©.