2013-08-07 15:36:11

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ለንባብ የበቃበት ዝክረ 20ኛው ዓመት ምክንያት የቫቲካን ረዲዮ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳርዩዝ ኮዋልዝዪክ አማካኝነት የጀመረው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ እ.ኤ.አ. ነሓሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. “ሱታፌ ቅዱሳን” በሚል ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ሁሉ ሱታፌና በምእመናን መካከል ያለው ሱታፌ የምትሰጠው ሥልጣናዊ አስተምህሮና የተአምኖተ እምነት ክፍል ጸሎት ማእክል በማድረግ 38ኛው ክፍለ አስተምህሮ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ በተአምኖተ እምነት “…የቅዱሳን ሱታፌ የሚለው ቃል በቅዱሳን ነገሮች እና በቅዱሳን ሰዎች መካከል ያለው ሱታፌ በቍ. 948 ተመልክቶ ይገኛል” ካሉ በኋላ ከሐዋርያት በተላለፈው እምነት ሱታፌ የእምነት ዕቃቤና የማስተላለፉ ተግባር ይመለከታል። የሰባቱ ቅዱሳት ምሥጢራት ሱታፌ እንኖራለ። በተለይ ደግሞ የቅዱስ ቁርባን ሱታፌ ያስተባብረናል ያወኅደናል፣ የእምነት የፍቅርና የተስፋ ሱታፌ እንኖራለን። ስለዚህ እምነት ቅዱሳት ምሥጢራትና ፍቅር ከእግዚአብሔር የሚፈልቅ ነውና ቅዱሳን ናቸው ብለዋል።
በሰዎች መካከል ሱታፌ፦ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በዚህ በምድር ነጋዲያን በሆኑት ምእመናን ዘንድ በንስሓ ሥፍራ የሚገኙትን በሙላት በመንግሥተ ሰማያት ከእግዚአብሔር ጋር ውህደት ያላቸው ዘንድ የሚኖር ሱታፌ ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት በሶስት ደረጃ በመከፋፈል ያብራራዋል (ቍ. 954 ተመልክተ)። ስለዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ጸጋ በተለያየ ደረጃ ሱታፌውን ይኖራል በማለት ካብራሩ በኋላ፣ እኛ በዚህ ምድር የምንኖረው በጸሎትና በፍቅር ሱታፌውን እኖራለን፣ ቤተ ክርስቲያንም ከዚህ ዓለም በሞት ስለ ተለዩት እንድንጸልይ፦ “ከሙታን ጋር የሚሆን ሱታፌ፦ ቤተ ክርስቲያን በተጓዥ አባላቷ የመላው የክርስቶስ ምሥጢራዊ አካል ሱታፌን በማወቅ ከመጀመሪያ የክርስትና ዘመን ጀምራ ሳታቋርጥ የሙታንን መታሰቢያ በታላቅ ከበሬታ ትዘክራለች፣ ሙታን ከኃጢአታቸው እንዲነጹ መጸለይ የተቀደሰና የተገባ ስለሆነ ስለ እነርሱ ያላት ድጋፍ ትገልጻለች። ለእነርሱ የምናደርሰው ጸሎት እነርሱን ብቻ የሚረዳ ሳይሆን ለእኛም የሚያደርጉልንን ምልጃ ይሠምርልናል” (ቍ. 958) በማለት ታስተምረናለች። ስለዚህ እግዚአብሔር መላ የሰውን ዘር ለማዳን ያለው የመሃሪነት ፈቃዱ የሰዎች ትብብር የሚጠይቅ መሆኑ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች።
ቤተ ክርስቲያን “…አታልቅሱ ከሞትኩ በኋላ ይበልጥ አጥቅማችኋለሁና። እኔም በሕይወት ዘመኔ ካደረግሁላችሁ በበለጠ እረዳችኋለሁ…የመንግሥተ ሰማይ ሕይወቴን በምድር ላይ ጥሩ ተግባር በመፈጸም ላሳልፈው እወዳለሁ…(ቍ. 956)” በሚለው ሃሳብ አማካኝነት የቅዱሳን እንዲሁም የብፁዓን ሱታፌ አምልኮ ትገልጥልናለች በማለት ያቀረቡትን አስተምህሮ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.