Home Archivio
2013-08-07 15:32:59
ዝክረ 20ኛው ዓመት “Veritatis Splendor-የእውነት ውበት(ግርማ)”
እ.ኤ.አ. ነሓሴ 6 ቀን 1993 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “Veritatis Splendor-የእውነት ውበት(ግርማ)” በሚል ርእስ ሥር በሰው ልጅና በመለኮታዊ ሕግ መካከል ያለው ግኑኝነት፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት የኅሊና ክብር እውነታዊው ለተዛማጅነት ግብረ ገባዊ ባህል መልስ የሰጡበት ዓዋዲ መልእክት ትላትና ለንባብ የበቃበት 20ኛ ዓመቱ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ዓዋዲ መልእክቱን ማእከል ባደረጉ በተለያዩ ዓውደ ጥናቶችና የጸሎትና የአስተትኖ መርህ ግብሮች መሠርት መከበሩ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር መማክርት አባል የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ኒኮላ ቡክስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ጋር
“
Veritatis Splendor-የእውነት ውበት(ግርማ)”
በማስድገፍ ባካሄዱት ቃል ምልልስ፦
“Veritatis Splendor-የእውነት ውበት(ግርማ)”
በቲዮሎጊያ ግብረ ገብ ዘርፍ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና እንዲሁም ካቶሊካውያን ባልሆኑት አቢያተ ክርስቲያን ጭምር ሊባል ይቻላል መሠረት ነው። የእውነት ውበትና ግርማ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር መልክ መለወጥ ማለትም ከተገለጠው የሚያስደንቅ ውበት ጋር የተጣመረ ዓዋዲ መልእክት ነው። ስለዚህ እውነት ረቂቅ ሥነ ሃሳብ ሳይሆን አንድ አካል፣ አንድ የሚያንጸባርቅ ግርማዊ ውበት አካል እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ ዓዋዲው መልእክት ከግብረ ገባዊነት ወደ ግብረ ገብነት የሚያሸጋግር ነው። ግብረ ገባዊነት በገዛ እራሳን ኃይል ላይ የሚደገፍ ነው። ግብረ ገብነት ግን በገዛ እራስ ላይ ሳይሆን የግብረ ገብ ምንጭ በሆነው ላይ መደገፍ ማለት መሆኑ ካብራሩ በኋላ፣ ግብረ ገባዊነት ለአንድ ክርስቲያን አቢይ ፈተና ነው፣ ይኽም ገዛ እራስ ግብረ ገብ ማድረግ የሚል ሲሆን፣ የክርስትናው ግብረ ገብ ሰውን በሚለውጥ የሕይወት ምንጭ ውሃ በሆኑት ቅዱሳት ምሥጢራት ላይ የሚደገፍ እንጂ በገዛ እራስ ኃይል የማይደገፍ ወይም የማይተማመን ነው ብለዋል።
“Veritatis Splendor-የእውነት ውበት(ግርማ)”
ልክ እንደ ሁሉም የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ዓዋዲ መልእክቶች ነቢያዊ ባህርይ ያለው የሚተነብይ ቀድሞ የሚያሳስብ ነው። በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እየተኖረ ያለው ሥነ ሰብአዊ አደጋና ሥጋት እያስከተለው ያለው ጉዳት ቀድሞ በማንበብ ምን መደረግ አለበት ለሚለው ሥነ ሰብአዊ ጥያቄ ቀድሞ መልስ የሰጠ ኵላዊ መልእክት ነው። በዚህ ብቻ ሳይታጠር በአሁኑ ወቅት ኅሊና ማለት
“ያሻኝን (መስሎ የታየኝን) ማድረግ”
በሚለው ትርጉም የሚገለጥ እየሆነ በምንም ተአመር እግዚአብሔርን ዋቢ የማድረጉ ሰብአዊ ተኩኖ በገዛ እራስ ዳኝነት (ገዛ ፈቃድ) ተክቶ የሚኖርበት ወቅት ነው። የሰው ልጅ ህሊና ታፍኖና ደብዝዞ በሚታይበት ወቅት ቤተ ክርስቲያንና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮ ይኸንን ሁሉ በማጤን የሆነውና የሚሆነውን በማጤን የሰው ልጅ ህሊና በማነቃቃት ተዛማጅ ባህል እንዲያገል ታሳስባለች፣ መንገዱንም ታመላክታለች፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በመደጋገም እቃቤና መከላከል በሚሉት ቃላት አማካኝነት የሚሰጡት ትምህርት የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቀጣይነቱ የሚያረጋግጥ ነው።
ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የግብረ ገብ የቲዮሎጊያ የፍልስፍና የነበራቸው ሊቅነትና ተመክሮ መሠረት
“Veritatis Splendor-የእውነት ውበት(ግርማ)”
በሚል ርእስ ሥር ያስተላለፉት ስልጣናዊ አስተምህሮ የሚመሰከር ነው፣ ከዚህ ሰብአዊ አገላለጥ ባሻገር የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ጥሪያቸው የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ላይ የጸና ሆኖ የሰው ልጅ በክርስቶስ ብርሃን አማካኝነት የሚያጤን መንፈሳዊነት የተካኑ መሆናቸው ይመሰከራል፣ ስለዚህ በዚህ ረገድ የሚታይ ጉዳይም ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.