2013-08-05 16:05:30

እንዴት የኢየሱስ ወዳጅ ለመሆን በቃልና በሕይወት ያስተማረው ካህን ቅዱስ ኩራቶ ዳርስ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ነሐሴ 4 ቀን የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቆሞሶች ጠባቂ ካህን ቅዱስ ኩራቶ ዳርስ በሚል ኵላዊ መጠሪያ የሚታወቀው ቅዱስ ዮሓንስ ማሪያ ቪያነይ ማክበርዋ ሲገለጥ፣ ቅዱስ ኮራቶ ዳርስ እ.ኤ.አ. ከ 1786 እስከ 1859 ዓ.ም. የኖረ ለአርባ ዓመት በፈረንሳይ በሚገኘው ብዙ በማይታወቀው አርስ ተብሎ በሚጠራው መንደር ቆመስ በመሆን ያገለገለና የተከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለሁሉም አብነት ብቻ ሳይሆን ለካህናት ቅድስና አርአያ ተብሎ በቤተ ክርስቲያን የሚነገርለት ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያወጁት የክህነት ዓመት ለእርሱ ጥበቃ በማስረከብ፣ ስለዚሁ ቅዱስ ካህን ጥልቅ አስተምህሮ አቅርበው እንደነበርም የሚታወስ ነው።
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ትልቅ ቅዱስ ተብሎ የሚነገርለት በሕንጸት በአለቆቹና በአስተማሪዎቹ የትምህርትና የጥናት ብቃት የሌለው ተብሎ ሲገለጥ፣ ሆኖም በእርሱ ዘንድ እግዚአብሔር ሊገልጠው የሚፈልገውን የቅዱስ ካህን ቃልና ተግባር በጠቅላላ ምስል ለማወጅም፣ ዮሐንስ ማርያ ቪያነይ በ 29 ዓመት ዕድሜው የክህነት ማዕርግ ለመቀበል በቅቶ ገና ከሕፃንነት በእረኝነት ሕይወቱን ይመራ የነበረ በዚህ የእረኝነት ሙያ ሊቅ በትምህርት ገበታ ያልተቀመጠ ቢሆንም ቅሉ ካህን ለመሆን ተመኝቶ ይኸንን ጥሪ በመከተል ለክህነት ሲዘጋጅ፣ የላቲን ቋንቋ ለማጥናት ጠንቅቆ ለማወቅ እንቅፋት ሆኖበት፣ ይኸንን ቋንቋ ለማወቅ የፈጀበት ጊዜ የክህነት ማዕርግ ዘግይቶ እንዲቀበል እንዳደረገና፣ ገና ክህፃንነቱ አማኝ የዋህ ተብሎ የሚነገርለት የመጻኢው ቅዱስ ካህና፣ ዘረአ ክህነት ለመግባትና ለመማር በቂ ገንዘብ ያልነበረው ሆኖም አንድ የዋህ ካህን ይኸንን የዮሓንስ ማርያ ቪያነይ ካህን የመሆን ጉጉት በመገንዘብ ለትምህርት የሚሆነው ወጪ በመሸፈን እንዲማር ቢደግፈውም በትምህርት ገበታ ተቀምጦ የማያውቅ በመሆን ሰነፍ ተማሪ እየተባለ ጓደኞቹ ሲያፈዙበትና ሲቀልዱበት ለግብርና እንጂ ለትምህርት የማይበቃ እያሉ መቀለጃ ሲያደርጉት ሆኖም የጠራው እግዚአብሔር በእርሱ አማካኝነት ሊያስተምረው የፈለገውን በማስተላለፍ ለማዕርገ ክህነት እንዲበቃ በማድረግ፣ በዓለም መልክአ ምድር ተለይቶ በማይታወቀው በአንድ ሁለት መቶ ሰዎች በሚኖርበት የፈረንሳይ መንደር ቆሞስ እንዲሆን ተልኮ በሰው በማይታወቀው ነገር ግን እግዚአብሔር ለገዛ እራሱ መኖሪያ ባደረገበት መንደር አገልጋይ ቅዱስ ካህን ለመሆን መብቃቱ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፦ “ኩራቶ ዳርስ ትሁት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ነገር ግን ፍርያማነቱ የላቀ ሆኖለት በእርሱ ዘንድ እግዚአብሔር ገዛ እራሱ በመግለጥ በክህነት ሕይወቱ ክርስቶስን በመምሰል የደጉ እረኛ ክርስቶሳዊ ምስል የኖረና ያመለከተ ስለ በጎቹ ገዛ እራሱ አሳልፎ የሚሰጥ ክርስቶስን በክህነት አፈገልግሎቱ የኖረ” በማለት እንደ ገለጡት የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
መላ ሕይወቱ ይላሉ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፦ “ህያው ትምህርተ ክርስቶስ በመሆን መሥዋዕተ ቅዳሴ ሲያቅርብና በቅዱስ ቁርባን ፊት ሲያስተነትን ለረዥን ሰዓታት በማናዘዣ ሥፍራ ተቀምጦ ወደ ጌታ የሚመለሱት ሲጠባበቅ ያሳየው አገልግሎት ይመሰክረዋል” እንዳሉ ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ “ዮሐንስ ማሪያ ቪያነይ በክርስቶስ ፍቅር የተቃጠለ እርሱ የተከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልው ውጤታማነቱ ለሚያበሥረውና ለሚቀድሰው ምስጢረ ቅዱስ ቍርባን የነበረው ፍቅር መግለጫ ነው። ይኽ ያከበረው የቀደሰውና የኖረው ምሥጢረ ቅዱስ ቍርባን ለክርስቶስ መንጋ ፍቅር ለክርስቲያኖች ፍቅር ለሁሉም እግዚአብሔርን ለሚፈልጉ ሁሉ ፍቅር በማድረግ የኖረ ነው” በማለት እንደገለጡት ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.