2013-08-02 15:27:02

ግብጽ፦ የማኅበረ ክርስቲያን ወቅታዊው ሁኔታ


RealAudioMP3 በግብጽ የሚንያ የምስራቅ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቦትሮስ ፋሒም አዋድ ሐና በአሁኑ ወቅት በግብጽ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን የክልሉ የክርስቲያን ማኅበረሰብ ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያውክ ይመስላል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ሲያመለክት፣ በተለያዩ አንዳንድ የእስላማዊ ወድማችነት የፖለቲካ ሰልፍ ደጋፊ በሆኑት የተለያዩ ድረ ገጾች በግብጽ ያለው አለ መረጋጋት ተጠያቂውና ጠንሳሹ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ሁለተኛ ናቸው በማለት ባጠቃላይ መንግሥታዊ ስልጣን የተዋድሮስ የረፓብሊካዊት የመከላከያ ኃይል በሚል ሲያሜ ሲገለጡት ይታያል፣ እንዲህ ባለ መልኩ የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የሞርሲ መንግሥት እንዲወገድ ላደረገው ሴራ ቀዳሜ አስተንፍሶ ናቸው በማለት እስላማዊ ወንድማማችነት ደጋፊው ሕዝብ የዚሁ የፖለቲካ ሰልፍ በብቃት ለማስተዳዳር አለ መቻሉ ያለው ድካምነት ለመሸፈን የሚጠቀምበት ስልት በአገሪቱ መጻኢ ጸረ ክርስቲያን ሽብር ለማነቃቃት ያቀደ መሆኑ ብዙ የአገሪቱ የፖለቲካ ተንታኞች የሚሰጡት መግለጫ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ ብፁዕነታቸው እስላማዊ ወድማማችነት ደጋፊው ሕዝብ ክርስትያናዊ አብዮት በማለት በግብጽ የተቀሰቀሰው ሁኔታ በመግለጥ ተጠያቂው ማኅበረ ክርስቲያ ነው በማለት የሚሰጠው መግለጫ መሠረት የሌለው ነው። ከጠቅላላው 30 ሚሊዮን የግብጽ ሕዝብ ብዛት ውስጥ 10 ሚሊዮን የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ መሆኑ ጠቅሶ ብፁዕ አቡነ ቦትሮስ ፋሒም አዋድ ማኅበረ ክርስቲያን ስለ ግብጽ ሰላም እንዲጸልዩ ጥሪ ማቅረባቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.