2013-08-01 08:59:38

ናይጀሪያ፦ የቦምብ ፍንዳታና የሞት አደጋ በክርስቲያኖች መኖሪያ ክልል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ሌሊት በሰሜናዊ የናይጀሪያ ካኖ ክልል የቦምብ ፍንዳታ አደጋ መጣሉና 12 የክልሉ ነዋሪዎች ለሞት አደጋ መጋለጣቸው ሲነገር፣ ይኽ በብዛት በክልሉ የሚኖረው ውሁድ ማኅበረ ክርስቲያን በሚኖርበት ሳቦን ጋሪ በመባል በሚጠራው ሠፈር የተጣለው የቦምብ ፍንዳታ ጥቃት መሆኑ ሲገለጥ፣ ከዚህ ቀደምም ይኽ ሠፈር ቦኮ ሃራም የአገሪቱ የምስልምና ሃይማኖት አክራርያን ታጣቂ ኃይሎች በተለያየ ወቅት ጥቃት የሰነዘረበት መሆኑም ይነገራል።
የአቡጃ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆን ኦናየካን ስለ ጉዳዩ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በእውነቱ በተለያየ ክልል በተለያየ ወቅትና ሰዓት የሚጣለው የቦምብ አደጋ ምንም’ኳ የጸጥታና የደህንነት ኃይሎች የተለያዩ እርምጃዎችና የጸጥታ ጥበቃ ለማረጋገጥ በተለያየ ክልል የተሰማሩ ቢሆንም አሁንም ማለቂያ የሌለው ነው የሚመስለው፣ ይህ ጉዳይም መፍትሄው በተለያዩ የናይጀሪያ የጎሳ መሪዎች የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች መካከል ግኑኝነት ያለው አስፈላጊነት ያረጋግጥልናል። የጸጥታና ደህንነት ጥበቃ አስፈላጊ ነው ሆኖም በሕዝብ መካከል ውይይትና መቀራረብ ለማረጋግጥ የሚያስችለው መርሃ ግብር ሊተገበር ካልተቻለ ሰላም ለማረጋገጥ አዳጋች ይሆናል ብለዋል።
በናይጀሪያ ሰሜናዊ ክልል የጸጥታ ደህንነት ጥበቃ ተልእኮ የአገሪቱ የመከላከያ ኃይሎች በሥፋት የተሰማራ ነው። ሆኖም ጸጥታና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚከናወነው ተግባር የክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ዕለታዊ ኑሮ ከበድ እያደረገው ነው። በመከላከያ ኃይል አማካኝነት የሚፈጸመው የጸጥታና ደህንነት ጥበቃ መርሃ ግብር ለብቻው በቂ አይደለም እንዲሁም በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል ውይይት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ሰልፎች መካከል ጭምር የጋራው ውይይይ እጅግ ወሳኝ ነው በማለት መፍትሔው ማኅበራዊ ሕዝባዊ ሃይማኖታዊ ፖለቲካዊ ውይይት ነው በማለት የሰጡንት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.