2013-07-22 16:54:40

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሪዮ ደ ጃነሮ ብራዚል፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ የመጀመርያ ሀገራት አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማሄድ ዛሬ ጥዋት ከሮም ለኦናርዶ ዳ ቺንቺ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስተዋል። የቅድስት መንበር ብጹዓን ካርዲናላት እና የጣልያን መንግስት ጠቃላይ ሚኒስትር ኤንሪኮ ለታ በአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተለቅድስነታቸውአሸናኘትአድርጎውላቸዋልመልካምጉዞተመኝተውላቸዋል።
ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከሮም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሱት ከጥዋቱ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ስምንት ሰዓት ከ85 ደቂቃ ሲሆን ብብራዚል ጀላዮ አንቶንዮ ካርሎስ ጆቦም ደ ሪዮ ሀገራት አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደርሱት በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኃላ 16 ሰዓት ሲሆን በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 21 ሰዓት መሆኑ ነው ።
በጣልያን በሮም እና ብራዚል ሪዮ ደ ጃንየሮ መካከል ያለውን ርቀት 9.201 ኪሎሜትር ሲሆን የበራራው ሰዓት 12 ሰዓት ተሩብ መሆኑ ይታወቃል።
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ወደ ሪዮ ደጃነይሮ የሚያደርስ አውሮፕላን Airbus A 330 Alitalia የጣልያን አየር መንገድ እንደሆነ ታውቆዋል። ቅድስነታቸው ሪዮ ደጃነሮ ሲገቡ የሀገሪቱ ብፁዓን ካርዲናላት ጳጳሳት በርካታ ውሉደ ክህነት የሀገሪቱ መሪ ፕረሲዳንት ዲላም ሩሰፍ የመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣናት አቀባበል እንደሚደርጉላቸው ተገልፀዋል ። የብራዚል መራሂተ መንግስት ፕረሲዳንት ዲልማ ሩሰፍ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሪዮ ሲገቡ የላቲን አመሪካ ሀገራት መንግስታት መሪዎች እንዲገኙ ማሳሰባቸው ከሪዮ የደረሰ ዜና አመልክተዋል።
ቅድስነታቸው ሪዮ እንደገቡ ከአንድ ሰዓት በኃላ የሀገሪቱ መንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣኖች በሚገኙበት የሀገሪቱ መራሂተ መንግስት ፕረሲዳንት ዲላም ዩሰፍ በጓናራ ቤተ መንግስት ፓርክ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር ያደርጋሉ
ቅድስነታቸውም በቤተ መንግስቱ የክብር ጉብኝት እንደሚያካሄዱ ተገልጠዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ፡ በብራዚል ሪዮ ደጃነይሮ ላይ ዓለም አቀፍ 28ኛ የወጣቶች ቀን እንደሚከናውን እና ቅድስነታቸው በዚሁ የዓለም ካቶሊካውያን ስብስብ ለመሳተፍ እንደሆነም አይዘነጋም። ቅድነታቸው በዚሁ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ሪዮ የገቡ ወጣቶች በይፋ የሚገኛኑት ፊታችን ሐሙስ copacabana በተባለ ቦታ እንደሆነ ተገልጸዋል።በዚሁ በብራዚል ሪዮ ላይ ነገ የሚጀምረው እና ለአምስት ቀናት የሚዘልቀው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ከዓለም ዙርያ ወጣቶች ሪዮ መግባታቸው እና እየገቡ መሆናቸው ይታወቃል።የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አዘጋጅ ኮሚቴ እንዳመለከተው በዚሁ ሪዮ ላይ የሚካሄደው የወጣቶች ቀን በሁለት ሚልዮን የሚገመቱ ወጣቶች ይገኛሉ። የዚሁ 28ኛ ሀገራት አቀፍ የወጣቶች ቀን ርእሰ ሂዱ እና የዓለም ህዝቦችን ሐዋርያት አድርጉ የተሰየመ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የአፓረሲዳ ገዳም በመጐብኘት እና በመጸለይ ፋቨላስ የተባሉ በሚልዮን የሚቆጠሩ በደሳሳ ቤቶች ከሚኖሩ እና እስር ቤት ውስጥ የሚጐኙ በመጐብኘት የወጣቶች ቀኑን መንፈሳዊ እምርታ እንደሚሰጡት የቫቲካን መገለጫ ገልጠዋል። ይሁን እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በብራዚል ቆይታቸው ፊታችን ሮቡዕ ወደ አፓረሲዳ ገዳም ዘልቀው በቅድስት ድንግል ማርያም ወላዴተ አምላክ ፊት ተንበርክከው ርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው የወጣቶች ቀን ስኬታምነት በአልኮሆል እና ዕጸ ፋርስ ሱስነት ለሚሰቃዩ ለዓለም ሰላም እንደሚጸልዩ ተዘግበዋል።ፊታችን ዓርብ ዕለተ ንስሐ ተሰይሞ ዳ ቦአ በተባለ ሰፊ ፓርክ ለተወሰኑ ወጣቶች እንደሚያናዝዙ እና እኩለ ቀን ላይ ከወጣቶች ጋር መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት እንደሚደግሙ ተወስተዋል።
ከመልአከ እግዚአብሔር ፋጽሜ በኃላ ከአምስት ክፍላተ ዓለም ከመጡ 12 ወጥቶች ጋር ለምሳ እንደሚቀመጡ ተነግረዋል። ፊታችን ዓርብ ቅድስነታቸው ከየዓለም ወጣቶች ጋር አብረው ኮፓ ካባና በተባለ ቦታ ሥርዓተ ፍኖተ መስቀል እንደሚፈጽሙ ተገልጠዋል።
ፊታችን ቅዳሜ ጥዋት በሪዮ ደ ጃነሮ ካተደራል ከሀገሪቱ ጳጳሳት ካህናት ጋር በሁባሬ እንደሚቀድሱ እና ከሥርዓተ ቅዳሴ በኃላ ከየብራዚል የፖሊቲካ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ጋር እንደሚገናኙ መርሀ ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ያምለክታል።በሐዋርያዊ መርሀ ዕደቱ መሰረት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቅዳሜ ማታ ጓራቲባ በተባለ የእምነት አደባባይ በተሰየው ትልቅ አደባባይ ከዓለም ወጣቶች ጋር ከይእሁድ ሥርዓተ ቅዳሴ ዋዜማ የሥርዓተ ጸሎት ይመራሉ ።ወጣቶቹ ለሊቱ በሙሉ በጸሎት ተጠምደው እንዳሚያድሩ ተገልጠዋል።
ፊታችን እሁድ 28 ቀን እኤአ በብራዚል እና ላቲን አመሪካ ብጹዓን ካርዲናላት እና ጳጳሳት ተሸንተው 28ኛ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ፍጻሜ ሥርዓተ ቅዳሴ ይመሩ እና እኩለ ቀን ላይ በዚሁ ሥርዓተ ቅዳሴ ከተሳተፉ ወጣቶች ምእማናት እና ምእመናን ጋር አብረው መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት እንደሚደግሙ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሐዋርያዊ መርሀ ግብር ዘግበዋል። ይህ በዚህ እብዳለ ሆኖ ከሶስት ቀናት በፊት ወደ ሪዮ ከተማ የተላኩ የስራ ባልደረባችን ሮበርቶ ፒየርማሪኒ የሪዮ ሁኔታ ምን እንደሚመስል የላኩት ዘገባ በሪዮ ከተማ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ መድረስ እና ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጅማሬ በግሩም ሁኔታ መጠናቀቁ አውስተው በዚሁ ክንውን ለመሳተፍ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ሪዩ የገቡ ወጣቶች በየአከባቢው እንደሚታዩ እና ደስተኞች መሆናቸው በቀላሉ ለማስተዋል ይቻላል ነበር ያሉት ።በማያይዝም የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ብራዚል ጉብኝት እና 28ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ትኩረት ሰጥተው መጻፋቸው አመልክተዋል።
አንዳንድ ጋዜጦች ለዚሁ ለወጣቶች ቀን የሚወጣው ገንዘብ ብዛት በመማረር ትችት መሰንዘራቸው እና የሀገሪቱ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትችቱ ውድቅ በማደረግ ወጪው ራስዋ እንደሸፈነችው ቅጽበታዊ መልስ መስጠትዋ ገልጠዋል። የሪዮ መንገዶች እና አደባባዮች የፓፓ ፍራንሲስ ሐዋርያዊ ጉብኝት እና የወጣቶች ዕለት የሚያንጸባርቁ ጽሁፎች ተለጥፈው እንደሚታዩ የራድዮ ቫቲካን የዜና መልእተኛ ይናገራሉ ። በታሪክ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የመጀመርያ የላቲን አመሪካ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተሰየሙ ፓፓ ፍራንሲስ ብራዚል ሲጐበኙ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመጅመርያ ግዜ ሀገሪቱ ውስጥ መካሄዱ ደስታ እና ኩራት ለብራዚል ህዝብ በማለት በርካታ ጋዜጦች ለንባብ ማብቃታቸው አያይዘው አመልክተዋል። የብራዚል ማሕበራዊ ኤኮኖሚ መዳከም ምክንያት በማደረግ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠረጠር እና 20 ሺ ጸጥታ አስከባሪዎች በሪዮ ደ ጃነሮ ከተማ መሰማራታቸው ገልጠዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ወደ ሪዮ ብራዚል ከመብረራቸው በፊት ከትናትና ወድያ እዚህ ሮም ውስጥ በሚገኘው የታላቅዋ ቅድስት ደንግል ማርያም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳዊ ካተድራል ተጉዘው ወላዲተ አምላክ በሐዋርያዊ ጉዞአቸው እንድትሸኛቸው አደራ በማለት መጸለያቸው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ካተድራል የበላይ ሐላፊ ብጹዕ ካርዲናል ሳንቶስ አብሪል ኢ ካስተዮ አስታውቅዋል። ብጹዕ ካርዲናል ሳንቶስ አብሪል ኢ ካስተዮ እንድገለጹት ፡ ቅድስነታቸው ወደ ሪዮ ደ ጃነይሮ ከመነሳታቸው በፊት በድንገት ወደ ካተድራሉ መጥተው በብራዚል ሪዮ ላይ የሚያካያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት እና ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የተሰካ እንዲሆን ጸልየዋል ቅድስት ድንግለ ማርያምን ተማጽነዋል።ባለፈው ወርሀ መጋቢት በኮንክላቨ በካርዲናላት ጉባኤ ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙም ወድታውኑ ወደ ካተድራሉ መጥተው ርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው የተስካ እንዲሆን መጸለያቸው የታላቅዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ካተድራል ጠባቂ እና የበላይ ሐላፊ አስታውሰዋል።ቅድስት ድንግል ማርያም የመድኅን ዓለም እና የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እናት በእምነታችን ጸንተን ልጅዋን እናገለግል እና የሱ ፍላጎት ገቢራዊ እናደርግ ዘንድ እንድትረዳን እስዋን መለመን እና መማጸን እንደሚገባን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በመደጋገም ማሳሰባቸውም ብጹዕ ካርዲናል ሳንቶስ አብሪል ኢ ካስተዮ ገልጠዋል።ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመርያ ክርስትያን እና ልጅዋን በእምነት እና ቆራጥነት የተከተለች ሐዋርያትን ያበረታታች ፍጹም ቅድስት ስለሆነች የእምነታችን አለት መሆንዋ ዘወትር ማስታወስ እንደሚገባንም ብጹዕ ካርዲናሉ ገልጠዋል። ይሁን እና ቅድስነታቸው ካተድራሉ በጐበኙበት ግዜ የዚሁ ካተድራል ምእመናት እና ምእመናን እንዲጸልዩላቸው አደራ ማለታቸው ብጹዕ ካርዲናል ሳንቶስ አብሪል ኢ ካስተዮ ተናግረዋል።ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ ሪዮ ከማቅናታቸው በፊት ከቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት 16ኛ ጋር መገናኘታቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል ።በዚሁ መግለጫ መሠረት የቀድሞው እና የወቅቱ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት በንዲክት እና ፍራንሲስ በግል ሐኣብ ለሐሳብ ተለዋውጠዋል ። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በብራዚል ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በመንፈስ አጠገባቸው በመሆን እንዲጸልዩላቸው በነዲክት 16ኛን ጠይቀዋል። በብራዚል ሪዮ ላይ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በቀድሞ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲት የታቀደ እና የታወጀ መኖሩ መግለጫው አስታውሰዋል።በነዲክት 16ኛ በጀርመን ኮልን በአውስትራልያ ሲድኒ እና በስፓኛ ማድሪድ ላይ የተካሄዱ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መምራታቸው እና መሳተፋቸው አይዘነጋም።








All the contents on this site are copyrighted ©.