2013-07-17 15:57:48

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 23 ቀን እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ሕዝብን ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው (ማቴ. 28.19)” በሚል ወንጌላዊ ቃል ተመርቶ በብራዚል ሪዮ ደጃነይሮ ከተማ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ገጠመኝ ሁሉ የሚያወሳ በስዕልና በጽሑፍ የተደገፈ የእምነት ገጠመኝ Pope2you በተሰየመው የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሚተዳደረው ድረ ገጽ አማካኝነት እንደሚቀርብና የዚያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መላ ሂደቱና ወጣት ተሳታፊው የሚኖረው ገጠመኝ ለመከታተል እንደሚቻል ምክር ቤቱ ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ በብራዚል በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በተለያየ ምክንያት ለመሳተፍ ለሚሳነው ወጣት ሁሉ በመንፈስ የሚያሳትፍ ሲሆን፣ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በመላ ዓለም በሚገኙት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሰበካዎች ወደ ብራዚል ለመሄድ ለማይችሉ ወጣቶች ከዚያኑ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጋር በተያያዘ መልኩ የዚያ ዓለም አቀፍ ሁነትና መርሃ ግብር በተጓዳኝነት የሚከናወን ሰበካዊ የወጣቶች ቀን ለማክበር በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ተገልጠዋ።
በኢጣሊያ የጀኖቫ ሰበካ የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጠሪ አባ ኒኮሎ አንሰልሚ ከቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዚጠኛ ኢሳበላ ፒሮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በተላያየ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፣ በቅዱስ ቁርባን ፊት አስተንትኖና ጸሎት፣ የመቁጸሪያ ጸሎት፣ በተለያዩ የመንፈሳዊ መዝሙር ትርኢት አማካኝነት ተሸኝቶ ለሁሉም በንስሐ ምሥጢር ላይ የተመረኮዘ ጥልቅ ትምህርት በመስጠት ወጣት ትውልድ በቅዱስ ቁርባን የመሳተፍ ጥሪው ለማነቃቃት የሚል መርሃ ግብር ያጠቃለለ መሆኑ አብራርተዋል።
በተለይ ደግሞ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 27 እና ሐምሌ 28 ቀን 2013 ቀን በኢጣሊያ ሊጉሪያ አስፍሆተ ወንጌል ያነቃቁ የክፍለ ሃገሯ ጠባቂ ቅዱሳን ናዛሮና ቸልሶ በዓል የሚከበርበት በመሆኑም የሰበካው የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ተጓዳኝነት ብሔራዊው የወጣቶች ቀን ለየት የሚያደርገው መሆኑ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸክሶ በመደጋገም እንደሚሉትም ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት እንዲችል የሚደገፍበት በኢየሱስ ፈቃድና ውሳኔ የጸናች ነች በማለት የገለጡት ሐሳብ ጠቅሰው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.