2013-07-12 16:24:34

የካቶሊካውያን ማኅበራዊ ሳምንት
ብፁዕ አቡነ ሚሊዮ፦ የቤተሰብ ኅልዮት ጭጋጋማ አለ ማድረግ


RealAudioMP3 “ቤተሰብ ለማኅበረሰብ መጻኢና ተስፋ” በሚል ርእስ ሥር የኢጣልያ ካቶሊካውያም ማኅበራዊ ሳምንት፦ “ለመንግሥታዊና ለማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎት መጻኢ” የተሰኘው መነሻ የሚፈልቅበት መድረክ ተብሎ የተገለጠው የኢጣሊያ የካቶሊካውያን ማኅበራዊ ሳምንት ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በቶሪኖ ከተማ መከፈቱ ሲገለጥ፣ ይኽ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ስለ ሚጠቃለለው ጉባኤ በማስመልከት የካሊያሪ ሊቀ ጳጳሳት የኢጣሊያ ካቶሊካውያን ማኅበራዊ ሳምንት የሥነ ምርምርና አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ አሪጎ ሚሊዮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውሰው፣ ቤተሰብ የተሰኘው ርእሰ ጉዳይ የብዙ ሰዎች አእምሮ የሚማርክ ለጥልቅ ውይይት የሚያንቃቃና እውነተኛና ለገዛ እራሱ ተጋርጦ ያለው ጉዳይ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ክርስቲያን ግትር ማለትም የሚያምንበትና የተቀበለው የገዛ እራሱ አምክንዮ ግድ የሚል ሳይሆን፣ ቅድነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እግዚአብሔር ፍቅር ነው በተሰየመው ዓዋዲ መልእክታቸው ዘንድ ቤተሰብ የመንከባከቡና መከላከሉ አስፈላጊነት የሚያረጋግጠው የተቀበልነውና የምናምንበት አመክንዮ ከሌሎች ግንዛቤ እንዲያገኝና ሌሎች እንዲረዱት ለማድረግ የተጠራን ነን ሲሉ ከገለጡት ጥልቅ ሃሳብ ጋር በማጣመር ማስረዳት እንጂ አክራሪነት ወይንም ግትርነት መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል ያሉት ሥልጣናዊ ሃሳብ የሚስተነተንበትና ይኸንን አመክንዮ የሚያስረዳ ጉባኤ መሆኑ አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.