2013-07-10 15:17:54

ዓለም አቀፍ የስደተኞችና ተፈናቃዮች የበላይ ድርገት አስተያየት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢጣሊያ የላምፐዱዛ ደሴት የፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት ለተባበሩት መንግሥታት የስደተኞችና ተፈናቃዮች የበላይ ድርገት ለሜዲትራኒያን ክልል ተጠሪ ላኡረንስ ጆለስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በላፐዱዛ የፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ እዛው ያሰሙት ምዕዳን በጠቅላላ የእሳቸው በዚያች ደሴት መገኘት ከጦርነት ከእርሃብ ክተለያዩ ማኅበራዊ ሰብአዊ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ችግር ምክንያት ለሚሰደዱት ዜጎች ሰበአዊ መብትና ክብር ዳግም የሚያጎናጽፍ ብቻ ሳይሆን ዓለም ስለ እነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል እንዲያተኩር ያለባቸው ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ የሚደረገው ጥረት ከማንኛውም ዓይነት ለስደተኛው የማይበጅ በጥቅማ ጥቅም ላይ ካተኮረ ጥረት ነጻ እንዲሆን የሚያነቃቃ ነው” ብለዋል።
ስለ ዓለም አቀፍ ስደተኞችና ተፈናቃዮች ጉዳይ እንዲተኮር ያነቃቃ ስደተኞችን ተቀብሎ የማስተንገዱ ኃላፊነት ግዴታ ሳይሆን ሰብአዊ ዝንባሌ በእያንዳንዱ ሰው ዘንድ ያለ ባህርይ መሆኑ ያስገነዘበ ሐዋርያዊ ጉብኝት ከመሆኑ ባሻገር፣ ቅዱስነታቸው ከሮውማ ውጭ ማንኛውም ብሔራዊም ይሁን ዓለም አቀፋዊ ጉብኝት አልፈጸሙም ስለዚህ ላምፐዱዛ የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ጉብኝት የፈጸሙባት ከተማ ነች ይኽ ደግሞ ዓቢይ መልእክት አዘል ተግባር ነው። ሰብአዊነት ማእከል ያደረገና በሁሉም ዘርፍ ሰብአዊነት ማእከል እንዲሆን የሚያሳስብ ሁነት መሆኑ ገልጠው፣ የተናቁት የመጨረሻ የሆኑትን ታናናሽ የኅብረተሰብ ክፍል ቅድሚያ መስጠት የሚል ተግባር ነው ብለዋል።
ስደተኛው የሚስተናግበት አገር ስደተኛው የሚነሳበት አገር የዓለም ማኅበረሰብ መንግሥታት ስለ ስደተኞች ጉዳይ እንዲያተኩሩ የሚያነቃቃ ሆኖ፣ በሌላው ረገድ ለስደት የሚዳርጉት ተግባሮች የማስወገዱ ጥረት የሁሉም ኃላፊነት በተለይ ደግሞ የመንግሥታት ነው የሚል ብቻ ሳይሆን ሁሉም በገዛ አገሩ ሰብአዊ መብቱና ክብሩ ተጠብቆለት የመኖር ዋስትናው ማረጋገጥ ግዴታ መሆኑ ያስገነዘበ ሰብአዊነት የተሞላው ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ገልጠው የሰጡት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.