2013-07-08 16:09:22

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ
“እግዚአብሔርን የሚኖር ሕይወት ያለው ደስታ ሊያስፈራ አይገባም”


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ እየተኖረ ባለው የእምነት ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የዘርአ ክህነት፣ የመንፈሳዊ ማህበራት፣ የደናግል ማኅበራት ተማሪዎች እንዲሁም ተመካሪያን የተሳተፉበት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ካሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በኋላ፣ እኩለ ቀን ከሐዋርያዊ መንበራቸው ከሚገኘው መስኮት ሆነው እነዚህ ወጣቶችና ሌሎች ከውጭና ከውስጥ የመጡ መንፈሳውያን ነጋድያን ጭምር በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በተሳተፉበት ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረገ ስልጣናዊ ስብከት ማሰማታቸ ጉባኤውን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገልጠው፣ ባለፈው ሳምንት ለንባብ የበቃው ስለ እምነት እንዲያስተነተንና ከወቅታዊው ዘረፈ ብዙ ቀውስ ጋር ገዛ እራሳችንን በማነጻጸር ወቅታዊው ሁነት በእምነት ዓይን ለመገምገም የሚያንጸው የእምነት ብርሃን የተሰየመው የደረሱት ቀዳሚው አዋዲ መልእክት በዚህ የእምነት ዓመት የታደልን በመሆናችን አቢይ ጸጋ መሆኑ ሲገለጥ፦ “ኢየሱስ ወደ ዓለም የእግዚአብሔር ፍቅር ለማወጅና ለማስፋፋት በአንድ ልዩ የሕይወት አግባብና በሱታፌ በወንድማማችነት መንፈስ በመኖር እንጂ ለብቻው ሊፈጽመው አልፈለገም። ፍቅር የማወጁ የመኖሩ የማስፋፋት ተልእኮ ኢየሱስ እንዳመለከው ተሳታፊነትንና አንድ ዓይነት የሕይወት አግባብ የሚጠይቅ ነው” እንዳሉ አስታውቀዋል።
“ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀጥታ ደቀ መዛሙርቱን በማነቃቃት ለተልእኮ ያሰማራል፣ የዚህ ተልእኮ ጥሪ በአንድ ላይ ተኩኖ ግዜን ለማሳለፍና በማኅበራዊነት ለመኖር ሳይሆን፣ ዓላማው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማወጅ ነው። ይኽ እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ዛሬም አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ጊዜ የሚባከንበት ወይንም የሁሉም ከሁሉም ተቀባይነት ለማግኘት በመጠበቅ ያስመሳይነት ሕይወት የሚኖርበት ሳይሆን መሄድና ማወጅ የሚል ነው፣ ለሁሉ የክርስቶስ ሰላም ማቅረብ፣ ሳይቀበሉት የቀሩ እንደሆነም አለ ምንም ማመንታት በተልእኮው ጎዳና መቀጠልና ወደ ፊት ማለት ነው” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ ጠቅሰው፦ “ለገዛ እራስ ስለ ገዛ እራስ አለ መኖር እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነው። ለገዛ እራስ መኖር ሳይሆን በተልእኮ ለመጓዝና መልካም ለማድረግ መኖር ነው ደስታው” በማለት እንዳሳሰቡም ገልጠዋል።
ቅዱስ አባታችን በዚያ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ጉባኤ አስተምህሮ ለተሳተፉት ወጣቶች፦ “በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተልእኮ ለመሳተፍ እንዴት ደስ ያሰኛል፣ የኢየሱስን ድምጽ ለይታችሁ እነሆኝ በማለት እርሱን ለማወጅ ልኡካን ለመሆን በመዘጋጀት ላይ ናችሁ፣ ኢየሱስን ማዳመጥ እንዴት ደስ የሚያሰኝ ነው፣ በርቱ። የዚህ ተልእኮ ዋነኛ ተወናያን እኛ አይደለም፣ ከዚህ ገዛ እራስ ቀንደኛ ተወናያን አድርጎ የማሰቡ ፈተና እንጠንቀቅ የጌታችን የጌታችን ጸጋ ነው ዋነኛው ተወናያን፣ የእርሱ ብቻ ነው ዋነኛ ተወናያንንነት፣ ስለዚህ ደስታችን በእርሱ ዋነኛ ተወናያንነት ላይ የጸናን የእርሱ ደቀ መዛሙርት መሆን፣ የእርሱ ጓደኞች መሆን ነው። መልካም የወንጌል አብሳሪዎች እንድንሆን ቅድስት ድንግል ማርያም ትርዳን። ደስታ ሊያስፈራችሁ አይገባም ደስታና ብርታት፣ ደስተኞችና ብርቱዎች ሁኑ” ካሉ በኋላ ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ደግመው እንዳበቁም፣ የእግዚአብሔር ብርሃን የተሰየመው በቅዱስነታቸው ሊኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተጀምሮ በቅዱስታቸው ለፍጻሜ የበቃው አዋዲ መልእክት ለማርያም ጥበቃ አቅርበው፦ “ዓዋዲ መልእክቱን በደስታ ለሕዝበ እግዚአብሔር አቀርበዋለሁኝ፣ ለሁሉም በተለይ በዚህ በአሁኑ ወቅት ወደ መሠረተ እምነት መቅረብ ያለውን መሠረታዊ አስፈላጊነቱን መገንዘብ በጥልቀት ለመረዳት ከወቅታዊው ሁነት ጋር ተነጻጽሮ መኖር አጅግ አንገብጋቢ ነው። ውድ ወጣቶች እኔም የእምነትን ዓመት ለማክበር እየተዘጋጀሁኝ ነኝ፣ አብረን እንጓዝ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ የእምነ ጉዞ ትርዳን” በማለት ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.