2013-06-26 16:02:10

መካከለኛ አፍሪካ እርቅ እንዲወርድ የብጹዓን ጳጳሳታ ጥሪ


RealAudioMP3 የመካከለኛይቱ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከሰኔ 12 ቀን እስከ ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ያካሄደው ጠቅላይ ጉባኤ ፍጻሜ በአገሪቱ ተከስቶ ያለው የእርስ በእርስ ግጭት ተወግዶ ሰላም እንዲሰፍን እርቅ ወሳኝ መሆኑ በማብራራት የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ ሚሸል ድጆቶዲያ ስልጣን ላይ ያወጣው እ.ኤ.አ. መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሄደው የመንግሥት ግልበጣ ወዲህ ሰለካ የተሰየመው የአገሪቱ አማጽያን ታጣቂ ሃይል ያቀጣጠለው የትጥቅ ትልግ አይሎ ሲታይ፣ ተከስቶ ያለው አለ መረጋጋት እና ግጭት እጅግ አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን ፍጻሜው ምን መሆኑ የማይታወቅም ነው። በሰውና በንብረት በአገሪቱም ሁከትና አመጽ ከማስፋፋት አልፎ የሕዝብ ጥቅም የሚል ሳይሆን የግል ጥቅም ላይ ያነጣጠረ በአገሪቱ ንብረት ቤት መዝክር ቤተ መዝገብ የመሳሰሉትን በማወደም በጠቅላላ መካከለኛ አፍሪቅ አለ ታሪክ ትውስት ለማስቀረት ያለመ መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳቱ ባወጡት የጋራ መግለጫ በማብራራት፣ የትምህርት ዘመን ተቋርጦ መንግሥትም አለ ምንም ግብረ ገብና ሥነ ምግባር ሰብአዊነት ችላ የሚል ያሠማራው የመከላከያ ኃይል አባላት የጸጥታ ኃይል ከመሆን ይልቅ አማጽያን ኃይል አባላት የሚፈጽሙትን ጸያፍና አስከፊ ተግባር ሁሉ በሕዝብ ላይ በመፈጸም የጦር መሣሪያ ሕግ የሚያደርግ ሁኔታ በአገሪቱ አቁመዋል።
ያለው ሁከትና ውጥረት የኑሮ ውድነት ሕዝብ ሊወጣው የማይችለው እየሆነ ሁሉ ለከፋ ሰብአዊ ችግር እያጋለጠ መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት ባወጥት የጋራ መግለጫ በመጥቀስ ምእመናን እና አማኙ ህዝብ ሰላም እና ፍቅር በመመስከር ወንጌል ያበስሩ ዘንድ አደራ በማለት፣ አማኝ የፖለቲካ አካላት ሁሉ ባላቸው ኃልፊነት እማካኝነት እምነታቸው በመኖር የሰላም መሣሪያ ሆነው እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል።
የግል ጥቅም ማራወጥ ሳይሆን ብሔራው ከሰላምና ከእርቅ የሚመነጭ እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ሁሉም በየፊናው አስተዋጽዖ እንዲበረክት ጥሪ በማቅረብ፣ የአገር ጥቅም የሚያግድ ማነቆ ሁሉ ለመቅረፍ የሚበጅ ሁኔታ እንዲረጋገጥና ጎሳነት አድልዎ አመጽ ተወግዶ ሁሉም በመተሳሰብ የሕዝብና የአገር ጥቅም በማስቀደም ለተሳካ ዓላማ በተሳካ ተግባር በመጠመድ የተለያዩ ሃይማኖቶችም በጋራ ውይይት እምነት በሚሰዋ ፍቅር በመመስከር ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊ ውጥረት እንዲወገድ በማድረጉ ሚና ተቀዳሚ አስተዋጽዖ ያበረክቱ ዘንድ ብፁዓን ጳጳሳቱ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.