2013-06-21 15:57:35

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በልባችን ጠላት ያለን ከሆነ ወደ አባታችን መጸለይ አንችልን


RealAudioMP3 አባትችን ሆይ ብለን ለመጸለይ ከወንድሞቻችን ጋር በልባችን ሰላም ሊኖረን ይገባል” በማለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ጧት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ሕንፃ ባለው ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት ማረጋገጣቸው የቅዳሴውን ሥነ ሥርዓት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገልጠው፣ የምንጸልየው እግዚአብሔር አባት ለእኛ ቅርብ የሆነ እንጂ አንድ ያልታወቀ ሥመ ስውር ወይንም አንድ ቆስሞሳዊ አግዚአብሔር አይደለም” በማለት እግዚአብሔር አባትና ቅርብ መሆኑ ማብራራታቸው አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ ካቶሊካዊ ሕንጸት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዘኖኖ ግሮቾለቪዝክይ ታጅበው የዚህ ቅዱስ ማኅበር ተባባሪ ሠራተኞችና የቫቲካን ቤተ መዘክር ሠራተኞች ጭምር የተሳተፉበት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በእለቱ ምንባበ ወንጌል ተንተርሰው ባሰሙት ስብከት፦ ጸሎት መተት አይደለም በጸሎት ምትሃት አይሠራትም፣ ጠንቋይን ፈውስ መጠየቅ የአልቦ እምነት ተግባር ነው። ኢየሱስ የሚያስተምረን ቃላት መደጋገም ሳይሆን ስንጸልይ አባት የሚለውን ቃል እንድንደግም ነው። አባት የሚለው ቃል የጸሎት መሠረት ነው። አባት ከሚለው ቃል ውጭ የሚደገም ጸሎት ጸሎት ነው ለማለት አንችልም። ለማን ነው የምንጸልየው። ለከሃሌ ኩሉ እጅግ ሩቅ ለሆነው እግዚአብሔር? ይኽ ኢየሱስ የኖረው ስሜት አይደለም። ለቆስሞሳዊ አግዚአብሔር ነው የምጸልየው? ይኽ አይነት ጸሎት የዘመኑ ለስላሳው ባህል የሚከተለው በብዙኅነት-እግዚአብሔር ማመን ነው የሚሆነው። እኛ ስንጸልይ ግን አባት የሚለውን ቃል ነው የምደግመው። ለፈጠረን አምላክ ነው የምንጸልየው፣ ሕይወት ለሰጠን አምላክ ነው የምንጸልየው። ሕይወት ለሰጠኝ አምላክ ነው የምጸልየው። በመንገድህ ለሚመራህ መላ ሕይወትህን ጠንቅቆ ለሚያውቅ እግዚአብሔር ነው የምንጸልየው። ስለዚህ አባት የሚለው ቃል በከንፈር የሚነበነብ ቃል ሳይሆ ከልብ የሚመነጭ ግብረ ቃል መሆን አለበት” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቱ አክለው፦ ቅርባችን የሆነ በእቅፉ የሚያኖረን አባት አለን፣ የሚያውከን ሁሉ እርግፍ አድርገን ለአብ እንተውለት፣ የሚያስፍልገንን ሁሉ ያውቃልና። አባቴ ሳይሆን አባታችን ነው። ስለዚህ ማንም ብቸኛ አንድ ልጅ አይደለም፣ እኔ ወንድም ካልሆንኩ የዚህ አብ ልጅ ልሆን አልችልም። የእኔ አብ የወንድሞቼ አብ ነው። ስለዚህ ከውወንድሞቼ ጋር ሰላም ከሌለኝ አብን አባቴ ብየ ልጠራው አይቻለኝም” እንዳሉ ገልጠዋል።
“ብልባችን ጥላቻ ኑሮን መጸለይ ፈጽሞ የሚቻል አይደለም። ወንድሞችና ጠላቶች በልባችን ይዘን መጸለይ አንችልም፣ ልባችሁ የወንድምነት ሥፍራ ሊሆን ይገባዋል። እርግጥ ከባድ ነው። አባት ሆይ እኔ አባት ብየ መጸለይ አይቻለኝምና እርዳኝ፣ አባታችን ሆይ ብየ ለመጸለይ አልችልንም፣ ምክንያቱም ያ በድሎኛል እንዲህ እድርጎኛል … ወዘተ እንላለን፣ ገሃነም ግባ የእኔ ወገን አይደለም እንል ይሆናል፣ ኢየሱስ ግን መንፈስ ቅዱስን ቃል ገብቶልናል፣ እርሱ ነው በእኛ ውስጥ ሆኖ ብልባችን አባት ሆይ ለማለትና እንዴት አባታችን ሆይ ብለን ለመጸለይ የሚያስተምረን። ዛሬ መንፈስ ቅዱስ አባታችን ሆይ ለማለት የሚያበቃን ከሁልም ጋር የሚያስታርቀን ከጠላታችንም ጋር ሳይቀር የሚያስታርቀን አባት በልባችን ለመድገም እንድንችል ያስተምረም” በማለት ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኝ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.