2013-06-17 19:18:55

የእግዚአብሔርን መንገድ መከተል ወደ ሕይወት: የጣዖቶቹን መከተል ግን ወደ ሞት ይመራል፣


በዚሁ የእምነት ዓመት ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.አ.አ በ1995 ኢቫንጀልዩም ቪተ የሕይወት ወንጌል በሚል ርእስ የጻፉት መልእክት ቀን ለማስታወስ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለመሳተፍ ከመላው ዓለም የተሰበሰቡ ከ200 ሺ በላይ የሚሆኑ ምእመናን ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተገኝተዋል፣ ስመጥር ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያኔ መል እክቱን የጻፉበት ምክንያት ለሕይወት ፈታኝ የሆኑ ነገሮች እንደ ጽንስ ማስወረድ ኤውታናዝያ ወይም ለመዳን ተስፋ የሌለውን የሕይወት ዘመን ማሳጠር የሞት ቅጣት የመሳሰሉትን ለማረም የጻፉት ነበር፣
ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና ባሰሙት ስብከት “የእግዚአብሔርን መንገድ መከተል ወደ ሕይወት ይመራል የጣዖቶቹን መከተል ግን ወደ ሞት ይመራል፣ ሆኖም ግን ሕዝብ ብዙ ጊዜ ሕይወትን አይመርጡም የወንጌል ሕይወትን አይመርጡም ሆኖም ግን ሕይወትን በሚያወግዱ ርእዮተ ዓለሞችና አስተሳሰቦች ይጓዛሉ፣” ሲሉ የወንጌል መል እክት አንኳር የሆነው በስመ ጥር ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የተጻፈው የሕይወት ወንጌልን እንድከተል አሳስበዋል፣
በእኩለ ቀን ላይ የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምሮ ፍጻሜ ላይም በ1944 ዓም አይሁዶችን ለመከላከል በናዚ የመታጐርያ ወህኒ ቤት ስለሞተውና ብፅ ዕናው ቅዳሜ የታወደው ኦድዋርዶ ፎከሪኒም አስታውሰዋል፣
ከዚህም ጋር በሮም ጉባኤ እያካሄዱ ያሉ 100 ሺ የሚሆኑ የሃርለይ ዳቪድሰን አባላት ሰላምታ አቅርበው 1.400 የሚሆኑ የድርጅቱ ፍሬ የሆኑ ሞቶር ሳይክሎችም ባርከዋል፣
ቅዱስነታቸው በቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ደጋግመው ያወሱት እግዚአብሔር በምሕረቱ ሕይወትን እንደሚፈልግና ሁል ጊዜ ይቅር እንደሚለን ነው፣
የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ትናንትና ከመላው ዓለም ከተሰበሰቡ ሕይወትን የሚደግፉ እና ማንኛውም የሕይወት አውዳሚ ነገር እንደ ጽንስ ማስወረድና ጸረ ጽንስ ነገሮች እንዲሁም የሞት ቅጣትና ርኅሩኅ መስሎ ሰዎችን ከመሰቃየት ሞት እያሉ ጸረ ሕይወት የሆነ ፕሮፓጋንዳን በመቃወም በቡድንና በተናጠል የሚንቀሳቀሱ ጸሎተ መቍጠርያ ካሳረጉ በኋላ ቅዱስነታቸው በጂፕ ማኪና ተዘዋውረው ሰላም ካልዋቸውና ከባረኩዋቸው በኋላ መሥዋተ ቅዳሴ በአደባባዩ አሳርገዋል፣
“ለፍቅር እሺ ለራስን ብቻ ወዳድነት እንቢ እንበል! ለሕይወት እሺ ለሞት እንቢ እንበል! ለነጻነት እሺ ለተለያዩ የዘመናችን ጣዖቶች ባርነት እንቢ እንበል! አጠር ባለ አነጋገር ፍቅር ሕይወትና ነጻነት ለሆነውና ኪዳኑን ለማይረሳ እግዚአብሔር እሺ እንበል፣ ሕይወቱን በሰጠን በኢየሱስ ክርስቶስና እንደ እውነተኞች የእግዚአብሔር ልጆች እንድንኖር በሚያደርገን በመንፈስ ቅዱስ በረዳን በእግዚብሔር ማመን ብቻ ነው የሚያደነን! ነጻና ደስተኞች አድርጎ የሚያኖረንም ይህ እምነት ብቻ ነው፣
“የሰው ልጅ ገዛ ራሱን ብቻ በመውደድ በገዛ ራሱ ብቻ ተዘግቶ በመኖርና በእግዚአብሔር ቦታ ራሱን በማስቀመጥ ለመኖር ከፈለገ ሞትን በመዝራት ላይ ተሰማራ ማለት ነው፣ ገዛ ራስን ብቻ መውደድ ገዛ ራስንና ጓደናን ለመሞኘት በመጣር ውሸትን ይወልዳል፣ ሆኖም ግን የሕያዋን አምላክ የሆነው አምላክ በሰው ልጆች ታሪክ ገብቶ መጀመርያ ከዚህ ባርነት ነጻ ያወጣናል ከዛ በኋላ ዓሠርቱ ቃላትን ይሰጠናል፤ አትዋቹ የሚል ት እዛዝም እዛ ይገኛል፣
“እነኚህን ትእዛዞች መጠበቅ እውነተኛ ነጻነት ወደ ተላበሰ እና ሙላት ወዳለው ሕይወት የሚወስደውን ጐዳና መከተል ማለት ነው፣ ምንም እንኳ አትግደል አታመንዝር አትስረቅ በውሸት አትመስክር እያሉ በአሉታዊ ቃላት ቢዘረዘሩ የእግዚአብሔር ፍቅርንና ሕይወትን የሚያመልክቱ ናቸው፣ ሕይወታችን በእግዚአብሔር ብቻ ነው ሙላት የምታገኘው ምክንያቱም ሕያው የሆነው እርሱ ብቻ ነውና! መጽሓፍ ቅዱስ ባጠቃላይ የሚያስተምረንም ይህንን ነው፣ እግዚአብሔርን ሕይወት የሚሰጥ እና የተትረፈረፈ ሕይወት ጐዳና የሚያሳይ ብሎ ይጠራዋል፣
“ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚብሔር ምሥጢረ ሥጋዌ ነው፣ ይህም በብዙ የሞት ሥራዎች ኃጢአቶች ራስን ብቻ መውደድና በገዛ ራስ ብቻ መዘጋትን በመቃወም ሕይወትን ይሰጣል፣ ኢየሱስ ሁሉን ይቀበላል ያፈቅራል ይረዳል ያበራታታል ይቅር ይላል እንዲሁም እንደገና ጉዞ ለመጀመር ኃይልንና ሕይወትን ይሰጣል፣ ሁሌ ይቅር የሚለን የእግዚአብሔር ምሕረት ታላቅ ነው፣
“እግዚአብሔር ሕያውና መሓሪ ነው!! ትስማማላችሁ ወይ? አብረን እንዲህ እንበል! እግዚአብሔር ሕያውና መሓሪ ነው! ሁላችሁ! ሕያው የሆነው እግዚአብሔር መሓሪ ነው! እስቲ ድገሙት! እግዚአብሔር ሕያው መሓሪ ነው! እንደ እውነተኞች የእግዚአብሔር ልጆች በመለኮታዊ ሕይወት ውስጥ የሚያገባን ከሙታን ተለይቶ የተነሣው ክርስቶስ ልዩ ሥጦታ የሆነ መንፈስ ቅዱስ ነው፣
“ክርስትያን መፈሳዊ ሰው ነው! ይህ ማለት ግን ከእውነተኛ ኑሮ ርቆ በደመና የሚኖር መንፈስ ማለት አይደለም፣ ክርስትያን በየዕለቱ እግዚአብሔር እንደሚያዘው ስለሕይወት የሚያስብና ስለሕይወት የሚሰራ ነው፤ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ እንድትመራና እንድትገሰግስ የሚፈቅድ ነው፤ በዚህም እንደ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ ሕይወቱ የተትረፈረፈ ይሆናል፣ እውነተኛነትና ፍርያምነት ማለት ደግሞ ይህ ነው፣ በመንፈስ ቅዱስ እንዲመራ የሚፈቅድ እውነተኛ ነው፤ ነገሮችን መምዘንና ዋጋ መስጠት ይችላል! ፍርያማም ነው ሕይወቱ በአከባቢው ሕይወት ይወልዳል፣ ሆኖም ግን የሰው ልጅ አብዛኛውን ጊዜ ሕይወትን አይመርጥም፤ የወንጌል ሕይወትን አይቀበልም፣ ከራስ ወዳድነት ከጥቅም ከትርፍ ማግኘት ከሥልጣን መጨበጥ እና ከደስታ ማግኘት የሚፈልቁ ርእዮተ አለሞችና አስተሳሰቦች እንዲመራ ይፈቅዳል፣ እነኚህ ግን ከፍቅርና የጓደኞች በጎ ነገር መሻት የሚፈልቁ አይደሉም፣
“በተደጋጋሚ የሚታየው የዘመናችን ቅዥት እግዚአብሔር የሌለበት ከተማ መቆርቆር ነው! ማለት ሕይወትና የእግዚአብሔር ፍቅር የሌለው አዲስ የባቢሎን ግንብ ማነጽ ነው፣ ይህም እግዚአብሔርና የሕይወት ወንጌል የሆነውን የክርስቶስ መልእክትን ማውገድ ነጻነት ሙሉ ሰብአውነት ያለብሳል ብሎ ማሰብ ነው፣ የዚህ ውጤት ደግሞ ሕያው እግዚአብሔር በሰው ሰራሽ ጣዖቶችና አላፊ በሆኑ ነገሮች ይተካል፣ እነኚህም የግዝያዊ ነጻነት ጣዕም ይሰጣሉ ነገር ግን በመጨረሻ ላይ የባርነትና የሞት ምንጭ ይሆናሉ፣ ስለዚህ ሊያድነን የሚችለው በሕያው እግዚአብሔር ማመን ብቻ ነው፣ ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ ቅዱስነታቸው ዘወትር አጠቃላይ አስተምህሮ ካቀረቡ በኋላ አጫጭር መልእክቶች ትዊተር በተባለው ዘመናዊ የብዙሓን መገናኛ በማስተላለፍ ትናንትናም ቤተ ክርስትያን የተፈቀርን ሆነን የምንሰማባት የምሕረት ቦታ መሆን አለባት ሲሉ አሳስበዋል፣ የመልእክቱ ሙሉ ይዘት “ቤተ ክርስትያን ዘወትር እያንዳንዱ ተቀባይነት ያገኘበት የተፈቀረበትና ይቅርታ ያገኘበት ሆኖ የሚሰማበት የምሕረትና የተስፋ ቦታ ትሁን፤” ይላል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.