2013-06-10 16:17:55

የጣልያን ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ቫቲካንን ይፋ ጐበኙ ፡


የጣልያን ርእሰ ብሔር ጆጆ ናፖሊታኖ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በቫቲኣክን የጣልያን አምባሳደር እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናታ አስከትለው በቫቲካን ይፋዊ ጉብኝት አካሄደዋል።
ርእሰ ብሔሩ እና ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቫቲካን ውስጥ በሚገኘው ሐዋርያዊ ቤተ መጻሕፍት ተገናኝተው በቅድስት መንበር እና ጥልያን መንግስት መካከል ያለውን ግንኙነት የኤውሮጳ የዓለም ወቅታዊ ሁኔታ ትኩረት የሰጠ ውይይት ማካሄድቸው ቫቲካን ላይ የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል ።
ፓፓ ፍራንቸስኮ የዲሞክራሲ ተቋሞች እና የሃያምኖት ነፃነት የጠበቀ እንዲሆን የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ እንዲገታ ርእሰ ብሔሩን መጠየቃቸው በቅድስት መንበር እና በታልያን መነግስት መካከል ያለውን ግንኙነት መልካም መሆኑ የገለጡ ሲሆን ፡ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ በበኩላቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በታልያን ህዝብ በፍጥነት ተቀባይነት ማግኘታቸው ርእሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው መልካም ጅማሬ ማሳየቱ ከመግለጣቸው ባሻገር በቅድስት መንበር እና ጣልያን መካከል መልካም ግንኙነት መኖሩ ማረጋገጣቸው ተዘግበዋል።
በዛርዪቱ ዓለም የሃይማኖት ነፃንት ተረጋግጠዋል ቢባልም በነጻ ገቢራዊ እየሆነ ነው ለማለት አዳጋች መሆኑ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጠቅሰው የሃይማኖት ነፃነት መጠበቅ የክርስትያኖች ሁሉ ሐላፊነት እንደሆነ ቅድስነታቸው ማስገንዘባቸው ተገልጠዋል።ኤውሮጳ አቀፍ ለማለት በሚያስችል መልኩ የተከሰተው የኤኮኖም ቀውስ በተለይ በወጣቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳረፈ መሆኑ ያመልከቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ፍትሕ አልባነትን በመታገል እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።በመጨረሻም ቅድስነታቸው እና ርእሰ ብሔሩ ስጦታ መለዋወጣቸው ተመልክተዋል።
የጣልያን መንግስት ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ወደ ኲሪናለ ቤተ መንግስት ከመመለሳቸው በፊት ከየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ከብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ እና ከየውጭ ጉዳይ ዋና ተጠሪ ከሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበርቲ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.