2013-06-10 15:56:53

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በሕይወት ጎዳና ከኢየሱስ ጋር መገናኘት


RealAudioMP3 በኢጣሊያ ከማቸራታ ከተማ ተነስቶ እሰከ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ዘ ሎሬቶ የሚካሄደው በእግር ጉዞ የተሸኘ መንፈሳዊ ንግደት ዘንድሮ “Comunione Liberazione-ሱታፌና አርነት የተሰየመው ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ ባቀረበው ሃሳብ መሠረት “በእውነቱ የሰው ልጅ ፍላጎት የሚያረካው ምንድር ይሆን?” በሚል መርህ ቃል ተሸኝቶ መካሄዱ ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም. 35ኛው የእግር ጉዞ መንፈሳዊ ንግደት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኤማኑኤለ ሶሪከቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
በእግር ጉዞ የተሸኘው መንፈሳዊ ንግደት ማቸራታ እንደደረሰም ይኽ ከማቸራታ ሎሮቶ በየዓመቱ የሚካሄደው የእግር ጉዞ ባስጀመሩት የፋብሪያኖ ማተሊካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጃንካርሎ ቨቸሪካ ታጅበው በሎረቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ነጋዲያኑ በማሳተፍ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለት መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ የዚህ የ 35ኛው በእግር ጉዞ የተሸኘው መንፈሳዊ ንግደት መርህ ቃል ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በአንድ ወቅት ያሉት ሃሳብ ጠቀስ ሲሆን፣ ሃሳቡንም ያቀረቡት የሱታፌና አርነት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር አባ ኹሊያን ካሮን ሲሆኑ፣ የዚህ ጥያቄ መልስ ኢየሱስ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለነጋዲያኑ በስልክ ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው፣ ከኢየሱስ ጋር ከመገናኘት ከሚመነጨው እምነት የሚገኝ እንደሆነም ማብራራታቸው ልኡክ ጋዜጠኛ ሶሪከቲ ካስተላለፉት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ለዚህ ለተካሄደው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት የስልክ መልእክት፦ “መላ ሕይወት መንፈሳዊ ንግደት (ጉዞ) ነው፣ ሰው ነጋዲ ነው፣ የሚፈለገው በዚህ የሕይወት ጉዞ ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ነው። ከእርሱ ጋር መገናኘት እምነት ይለግሳል፣ ምክንያቱ እምነት የሚሰጠው እርሱ ነውና። እናንተ የዚህ መንፈሳዊ ንግደት የእግር ጉዞ ተሳታፊዎች በዚህ እጽብ ድንቅና ማራኪ ህላዌ በሆነው በኢየሱስ ላይ ትደገፉ ዘንድ አደራ። ድካም ሲሰማችሁ ለገዛ እራሳችሁና ገዛ እራሳችሁ ማእከል ያደረገ ጉዞ የማከናወን ፈተና ሲያጋጥማችሁ ከእናንተ ጋር የሚጓዘው ደጋፊያችሁ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን አስቡ አሜናችሁን አስታውሱ፣ የእናንተ ሰብአዊነት የተሰቃየውና የተጎሳቆለው አካለ ክርስቶስ የሚሻ መሆኑ አውቃችሁ ሁላችሁም ይኸንን ታውቁ ዘንድ በጸሎት ተሳሰቡ። ምክንያቱን የክርስቶስ ሰብአዊነት ብቻ ነው ለእውነተኛው የሰው ልጅ ፍላጎት ሙሉ መልስ” እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ሶሪከቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.