2013-04-26 14:10:24

ክርስትያን ትሑት መሆን አለበት ሆኖም ግን ታላላቅ ነገሮች ለማድረግ መፍራት የለበትም፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅድስት ማርታ በሚገኘው ቤተ መቅደስ ባስረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የክርስትያን ስብከተ ወንጌል ትሑት ነው በሌላ በኩል ደግሞ ታላላቅ ነገሮች ለመፈጸም የማይፈራ ነው ሲሉ በላቲኒ ሥርዓተ አምልኮ በዕለቱ የተዘከረውን የቅዱስ ማርቆስ አስታውሰዋል፣
የዕለቱ ቃለ ወንጌል ከማርቆስ የተወሰዶ ሆኑ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከመጣቱ በፊት ለሐዋርያቱ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።” ብሎ እንድተናገራቸው ከዛም “ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ ሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።” (16፡15-20) የሚለው ክፍል ነበር፣ ቅዱስነታቸውም ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ የሚለውን ቃል በማስመር ወደ ኢየሩሳሌም ወይንም ገሊላ ብቻ ነው ወይ የላካቸው ብለው ጥያቄ አረበዋል፣“አይደለም! ወደ መላው ዓለም ነው፣ እጅግ ሰፊ የሆነ አመለካከት ነው! በዚህም የቤተ ክርስትያን ተልእኮአዊ ባህርይ ለረዳት ይቻላል፣ ቤተ ክርስትያን ይህንን ለፍጥረት ሁሉ ለመላው ዓለም ወንጌል ስብኩ ባለው ት እዛዝ መሠረት ትገሰግሳለች፣ ይህንን ግስጋሴ የምታደርገው ብቻዋ አይደለም ሁሌ ከኢየሱስ ጋር ነው የምታጓዘው፣ ጌታ ወንጌል ከሚሰብኩ ጋራ ሁሌ ይሰራል፣ ክርስትያን ሊኖራቸው የሚያስፈልገው ይህ ለጋስነት ነው፣ ደካማና ፈሪ ይየሆነ ክርስትያን ግን ሊረዳው አይችልም፣ ይህ ለጋስነት የክርስትያን ባህርይ ነው፤ ማንኛው ክርስትያን በዚህ ለጋስነት እያደገ ሁሌ ወደፊት መገስገስ አለበት፣ ሲሉ ስለተል እኮ ከተናገሩ በኋላ ከዕለቱ አንዱ በሆነው በ1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፤5 ላይ “ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት” በሚለው በማትኰርም ይህንን ብለዋል፣
“የወንጌል ስብከት ባህርይ በትሕትና መሆን አለበት ማለት በአገልግሎት እና በወንድማዊ ፍቅር መሆን አለበት፣ ሆኖም ግን በውስጣችን ጌታ ሆይ! መላውን ዓለም ለመያዝ እንፈልጋለን የሚል ስሜት ሊኖረን ይችላል፣ ሆኖም ግን ዓለምን መያዝ መግዛት የሚለው ቃል ከክርስትና አይስማማም፣ በዓለም ውስጥ ሆነን መስበቅ አለበን፣ ክርስትያን ውግ ያን ባሸነፉ ጊዜ ሁሉን እንደሚደመሥሱ ወታደሮች መሆን የለብንም፣ ክርስትያን ወንጌልን በቃል ሳይሆን በሕይወቱ በአኗኗሩ ምሳሌ በመሆን ነው መስበክ ያለበት፣ ቅዱስ ቶማስ እንደሚያመለክተው የክርስትያን ጉዞ በሁለት የተራራቁ ነገሮች ያጌጠ መሆን አለበት፣ ወደር የለሽ ታላላቅ የእግዚአብሔር ሥራዎች ባንድ በኩል በሊላው በኩል ደግሞ ትናንሽ ነገሮችን አይቶ ለመቻል ትሕትና ያስፈልጋል፣ የክርስትና ስብከተ ወንጌልም ሁሌ ይህንን መከተል አልበት፣ በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል አንዲት ደስ የምታሰኝ ሓረግ አለች፤ ሐዋርያት ወንጌል ሲሰብኩ “ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ ሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።”
“ስለዚህ እኛ ሁሌ በእነዚሁ ለጋስነትና ትሕትና የተጓዝን እንደሆነ፤ በትላላቅ ነገሮች ሳንደነግጥ በየዕለቱ በትሕትናና በፍቅር ትናንሽ ነገሮችን የምንመርጥ ከሆነ ጌታ ቃሉን በምልክቶች ያጸናል፣ በዚህም ወደፊት እንራመዳለን፣ የቤተ ክርስትያን ድል የኢየሱስ ትንሣኤ ነው፣ ሆኖም ግን መጀመርያ መስቀል አለ፣ ዛሬ ጌታን የቤተ ክርስትያን ልኡካን እንድንሆን በታላቅ ለጋስነትና በታላቅ ትሕትና መንፈስ እንድንፈጽመው እንዲያስቸልን እንለምነው ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.