2013-04-24 15:18:55

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አለ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ማመን አይቻልም


RealAudioMP3 ትላትና በላቲን ሥርዓት የቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል መከበሩ ሲገለጥ፣ በዚሁ ዕለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዕለተ ስማቸው ማክበራቸውም ለማወቅ ሲቻል። ዕለቱ ምክንያት በማድረግ ቅዱስነታቸው በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ጸሎት በሮማ ከሚገኙት ብፁዓን ካርዲናሎች ጋር በመሆን መሥዋዕተ ቅድሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፦ አለ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ማመን አይቻልም። አለ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ክርስቲያን የኢየስስ መንጋ ለመሆን አይቻለውም። ስለዚህ አለ ቤተ ክርስትያን የማኅበረ ክርስቲያን እምነት የወተትና የውኃ ቅልቅል ሆኖ ጣእም የሌለው ሆኖ ይቀራል። ይኽ ደግሞ የዛሬ 2 ሺሕ ዓመት በአንጽዮኪያ አንድ በማለት ቅዋሜው ካረጋገጠው እውነት ጋር አያያዘውም፣ ቀደምት ክርስቲያን አለ ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ አምናለሁ ለማለት የሚቻል እንዳልሆነ በቃልና በተግባር መስክረውልናል። ማኅበረ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም ባጋጠማቸው ስደትና መከራ ምክንያት ወደ ተለያዩ አገሮች ተሰደው ወንጌል እንዲመሰክሩ አድርገዋል። ስለዚህ ስደትና መከራ ለአስፍሆተ ወንጌል ማነቃቂያ ኃይል ነው። ቤተ ክርስቲያን እናት ነች፣ በዚህ ሁነት የመጀመሪያው ቲዮሎጊያዊ አንቀጸ እምነት ጅማሬ ተረጋገጧል ለማለት ይቻላል” እንዳሉ ቅዳሴውን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።
“ክርስቲያናዊ መለያ የቤተ ክርስቲያን አባልነት የሚል ክፍለ ቤተ ክርስቲያን ማለት ነው። ምክንያቱን የሁሉም እናት ለሆነቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ናቸውና። ስለዚህ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ኢየሱስን ማግኘት ፈጽሞ የሚቻል አይደለም። ኢየሱስ መለያችን የምናገኝበት እናታችን የሆነቸው ቤተ ክርስቲያን ይሰጠናል። ስለዚህ ምልክታችን የሚታተምበት ብቻ ሳይሆን የእርሷ ክፍል መሆናችን የሚረጋገጥበት እውነት ነው። መለያችን የቤተ ክርስቲያን አባል መሆናቻን ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
“ከዓለም ጋር በመደራደር በዓለም መንገድ ለመራመድ የምንፈልግ ከሆን መቼም ቢሆን የጌታ መጽናናት አይኖረንም። ስለዚህ መጽናናትን ብቻ የምፈልግ ከሆን መጽናናቱ መሠረት የሌለው ይሆናል፣ ምክንያቱም ከኢየሱስ የሚገኝ መጽናናት ሊሆን የማይችል ሰብአዊ መጽናናት ሆኖ ስለ ሚቀር ነውና። ቤተ ክርስቲያን በመስቀልና በትንሣኤ በስደትና በጌታ መጽናናት የምትራመድ ነች፣ ይኽ ልንጓዝበት የሚገባን መንገድ ነው። በዚህ መንገድ የሚራመድ አቅጣጫውን አይስትም አይሳሳትምም” ካሉ በኋላ፦ “የኢየሱስ በጎች ካልሆን እምነት አይኖረንም። ስለዚህ የኢየሱስ በጎች ካለ መሆን የምንኖረው እምነት አልባ መሠረት፣ ቋሚ ነገር የሌለው እምነት ይሆናል። ስለዚህ በዚህች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት እናት ውስጥ የኢየሱስ ስም አንግበን ወደ ፊት እንበል፣ ቅዱስ ኢግናዚዮስ እንደሚለውም ይህች ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ቅድመ ተከተል ሥልጣንና ኵላዊነት ባህርይ አላት በማለት የገለጣት ቤተ ክስቲያን የሚያስታውስ ነው” በማለት ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አመለከቱ።
ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዕለተ ስማቸው ባሚያከብሩበት በትላንትናው የጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል ምክንያት ከተለያዩ አበይት አካላት የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት መተላለፉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.