2013-04-15 15:38:44

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአንደኛው ወር ዝክረ ምርጫ



RealAudioMP3 ብፁዕ ካርዲናል ኾርገ ማሪዮ በርጎሊዮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው የተሸሙበት አንደኛው ወር ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. መዘከሩ ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸ ባላቸው ትህትና የአባትነት እንዲሁም የርኅራሄ መንፈስ ግልጽነታቸውም ለብዙ የምእመና እምነት መስህቦ ከመሆኑም ባሻገር ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አባላት እንድታድግ እያደረገ መሆኑ ከተለያዩ ሰበካዎች የሚሰጡት የምስክርነት ቃል ያረጋግጠዋል።
ርቆ የነበረው እምነት ከመቀበል እምቢ ያለው የሳበ ብቻ ሳይሆን በእውነቱ በቤተ ክርስቲያን ያለው ምእመን ጭምር እምነቱን በታደሰ መንፈስ እንዲኖር እያነቃቁ መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው በተመረጡባት ዕለት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ከውጭና ከውስጥ የመጡት አዲስ ር..ሊ.ጳ.ን ለማወቅ በብዙ ሺሕ የሚገመቱን ምእመናን ከሐዋርያዊ መስኮት ፊት ሆነው ሲተዋወቁ፣ እንደምን አመሻችሁ በሚለው ተራ ቃል በመተዋወቅ፦ “ሐዋርያዊ ቡራኬ ከመስጠቴ በፊት፣ የሮማ ጳጳስ ሕዝብን ከመባረኩ በፊት እግዚአብሔር ይባርከኝ ዘንድ እናንተ ስለ እኔ ጸልዩ በማለት እነገታቸን ዝቅ በማድረግ፣ ሕዝበ እግዚአብሔር ጳጳሱን እግዚአብሔር ይባርከውም ዘንድ ስለ እርሱ ጸልዩ” እንዳሉ የሚዘከር ነው።
እ.ኤ.አ. መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ስለ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “አለ መስቀል ስንጓዝ አለ መስቀል ስንገነባ ክርስቶስን አለ መስቀል ስንናዘዝ ስንመሰክር የጌታ ደቀ መዛሙርት ሳንሆን የዓልም እንሆናለ፣ አለ መስቀል ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ብፁዓን ካርዲናሎች ር.ሊ.ጳ.ሳትምን ልንሆን እንችላለን ነገር ግን የጌታ ደቀ መዝሙር አይደለንም” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ በመቀበል ባሰሙት ሥልጣናዊ ንግግር፦ “ጨለምተኛነት የክርስቲያን አይደለም፣ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ለአስፍሆተ ወንጌል የተዳሰ ስልት እንድትከተል የብርታት ጽናት ይሰጣል” እንዳሉ ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ባለ ሙያዎችና ሠራተኞችን በአገረ ቫቲካን ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው ባሰሙት ንግግር፣ ቅዱስነታቸው ለምን ፍራንቸስኮ የሚል መጠሪያ ስም እንደመረጡ ሲያብራሩ፦ “የብፁዓን ካርዲናሎች የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመምረጥ ባካሄደው ቅዱስ ዝግ ጉባኤ እንደመረጠኝ አጠገቤ ተቀምጠው የነበሩት ብራዚሊያዊ ብፁዕ ካርዲናል ሁመስ አደራህን ድኾችን እትርሳ ያሉኝን ቃል በቀጥታ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ ነው በውስጤ የቀሰቀሰው እኔም ይኸንን ሁነት በመከተል የአሲዚው ቅዱስ ስም ለመምረጥ ወሰንኹኝ፣ የሰላም መንፈስ የተሞላው ድኽነትን የመረጠው ቅዱስ በእውነቱ የተረጋጋው መንፈስ የተሞላው ቅዱስ ነው። ቤተ ክርስቲያን ድኻና ለድኾች ትሁን” እንዳሉ አስታውሰዋል።
መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተገኙት ምእመናን ፊት ባሰሙት የጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ፦ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው። እኛን ሊምረንና ይቅር ሊለን ፈጽሞ የማይደክም፣ እግዚአብሔር በምህረቱ የማይደክም የማይሰለች አምላክ ነው። ድካሙ ከእኛ ነው፣ ምህረት ከመጠየቅ መድከም ከእኛ ነን። አፍቃሪው አብ ዘወትር የሚምር ነው…ይቅር ማለትና ምህረትን መስጠት ከዚህ ፍጹም ምህረት እንማር’ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውሶ መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. በተከበረው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ጠባቂ በዓለ ቅዱስ ዮሴፍ ምክንያት እኚህ 226ኛ የቅዱስ ጴጥርስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተልእኮአቸውን በይፋ ለማስጅመር በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ልኡካነ መንግሥታት አርእስተ ብኄራት መራህያን መንግሥታት በብዙ ሺሕ የሚገመተው ተራ ምእመናን በተገኙበት ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “እውነተኛው ሥልጣን አገልግሎትና የአገልግሎት ኃላፊነት ነው። ስለዚህ እውነተኛው የአገልግሎት ሥልጣን ኃይል መስቀል፣ የመስቀል ብርሃን ነው” ሲሉ እ.ኤ.አ. መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታትን ተቀብለው ባሰሙት ሥልጣናዊ ንግግር፦ “በመካከላችን የሚጸናው ውይይት ሕዝቦችን የሚያገናኝ ድልድይ ነውና፣ ይኸንን አገናኝ ድልድይ በመወያየት እንገባ። በውይይት አንዱ በሌላው የእርስ በእርስ ጠላትነት ሳይሆን የእስር በእርስ ወዳጅነትና ወድማማችነት መንፈስ ሊገነዘብ ግምት ሊሰጥ ይገባዋል” እንዳሉ ያስታውሳል።
በላቲን ሥርዓት መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በዓለ ሆሳዕና ምክንያት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ዕለቱ ብሔራዊ የወጣቶች ቅን የሚከበርበት መሆኑ በማስታወስ፦ በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ የሚሰጠው ተስፋ እንዳይሰረቅባችሁ ተጠንቀቁ” እንዳሉና መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰሙነ ኅማማት ጸሎተ ሓሙስ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ፦ “ካህን መጋቤ ነውና ይኽ ደግሞ የእግዚአብሔር መንጋ እረኛ ማለት ነው። ስለዚህ የበጉ ጠረን ያለው በመንጋው መካከል የሚኖር ሰዎችን የሚያጠምድ መሆን አለበት” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
መጋቢት 31 ቀን 2013 ዓ.ም. ሮማዊና ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ቡራኬ ከመስጠታቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት ቃል፦ “በእግዚአብሔር ምህረት እንድንታደስ በእግዚአብሔር ፍቅር እንፈቀርም ዘንድ፣ የእርሱ ፍቅር ይለውጠንም ዘንድ እንፍቀድለት፣ የዚህ ምኅረት መሳሪዎች በመሆን ይኽም እግዚአብሔር ተፈጥሮን ለማቀብና ምድር ፍትህና ሰላም እንድታፈራ የሚሠሩ እንሁን” ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፣ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ባሰሙት የረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፦ “የትንሣኤ ቀደምት አብሳሪዎች ሴቶች ናቸው። ይኽ ደግሞ የሁሉም እናቶች በጠቅላላ የሴቶች ተልእኮ የሚገልጥ ነው። ይኽ ተልእኮ እንዴት ውብ ነው። ለልጆች ለልጅ ልጆች የኢየሱስ ሕያውነት መስካሪያን ናቸው። እናቶችና በጠቅላላ ሴቶች ይኸንን ሕይወት በመመስከር ኑሩ” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. የሮማ ጳጳስ እንደመሆናቸውም መጠን በቅዱስ ዮሓንስ ዘላተራኖ የሮማ ጳጳስ ርእሰ ባዚሊካ ሐዋርያዊ መንበራቸውን በይፋ ለመረከብ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ፦ “ሕዝብና ጳጳስ እጅ ለእጅ ተያይዘው በአንድ ላይ መጓዝ አለባቸው። እጅ ለእጅ ተያይዘንም ሞትን አሸንፎ በተነሣው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚስጠው ደስታ ዘወትር ተሞልተን ወደ ፊት እንራመድ። እርሱ ዘወትር ከጎናችን ነው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.