2013-03-29 16:24:12

ካህናት እንደ መልካሙ እረኛ የደከመችውን በግ በትከሻቸው መሸከም አለባቸው፣


በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ የተያዝነው ሳምንት ሶሙነ ሕማማተ እግዚእነ የሚዘከርበት በመሆኑ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሮማ ሃገረስብከት ጳጳስ በመሆናቸው ሁሉም ጳጳስ በሃገረ ስብከተ በዚሁ ሳምንት ማበርከት ያለበትን ተልእኮ ለመወጣት በዕለተ ሆሳዕና ከተከበረው ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ሃገረ ስብከታዊ ቀን ጀምረው በየዕለቱ እያስተማሩና በተለያዩ ቦታዎች በመሄድም ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮአቸውን እየፈጸሙ ናቸው፣
ትናንትና ሓሙስ ቤተ ክርስትያን ክምታከብራቸው ታላላቅ በዓሎች አንዱ በመሆኑ በዚህም ዕለት የሶስቱ ዓበይት ምሥራተ ቤተ ክርስትያን ምሥጢረ ጥቀ ቅ.ቍርባንና ምሥጢረ ክህነት የተመሠረተበት እንዲሁም ለምሥጢረ ጥምቀት ምሥጢረ ሜሮንና ምሥጢረ ቅብአ ሕሙማን የሚሆን ቅዱስ ዘይት የሚባረክበት በመጨረሻም ጌታ ለሐዋርያቱ ሲሰናበታቸው ያደረገው ታላቅ የትሕትናና የፍቅር ምልክት የሆነ ሕጽበተ እግር የሚፈጸምበት ዕለት ነው፣
ቅዱስነታቸው ከ1600 ካህናት በላይ በተሳተፉበት የዘይት ቡራኬ ቅዳሴ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ አሳርገዋል፣ የኁባሬ ቅዳሴ ካህናት እውነተኞች እረኞች በመሆን መለያቸው የሆነውን መንጋዎቹም በእርሱ የሚያውቅዋቸው የመንጋቸው ጠረን እንዲኖራቸው አሳስበዋል፣ እንደ ማንኛ ባለመዋል ወይም አገናኝ ሳይሆን እውነተኛ እረኞች ሆነው እስከ ሕይወታቸው መሥዋዕት ለማድረግ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውና ከመንጋው እንዳይለዩ፣ አደራ ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው ደጋግመው በዚሁ ሶሙነ ሕማማት ከገዛ ራሳችን መውጣት እንዳለብንና ኅብረተሰቡ ረስተዋቸው ተገለው እና ተረስተው ያሉ ድኅቶችና እርዳታ ወደ ሚያፈልጋቸው እንድንደርስ ሲሆን በትናንትናው ስብከታቸው በተለይ ለካህናት እንደ መልካም እረኞች እያንዳንዱ የቍምስናቸውን ም እመን ከቅዳሴ በኋላ ዓይን ዓይኑን በመምለክት በተፈጸመው ሥር ዓተ አምልኮ ልባቸው የተነካና አዲስ ነገር ያገኙ እንደሆነ ለሕይወታቸው የሚያሳድስ ነገር ያገኙ እንደሆነ ጠንቅቆ ማወቅ እንዳለባቸው በማመልከት በሥር ዓተ ቅዳሴው መሃከል እያንዳንዱ ካህን የሚያደርገውን የካህናት ማኅላ ማለትም በንጽሕና በድኅነትና በታዛዥነት ሕዝብን ለማገልገል የገቡትን ማሃላ ባሳደሱበት ወቅት “መልካሙ እረኛ የደከመችውን በግ በትከሻው ላይ ተሸክሞ እንደተመላለሰው ሁሉ የዛሬ ካህናት እያንዳንድዋ ነፍስ በዚህ ጊዜ የምታሳልፈውን ችግር ተሸክመን ምን እንደሚሰማቸው የልባቸውና የመንፈሳቸውን መጨነቅና ችግር መስማት እንደሚያስፈልግና ተስፋ እንድንሆን ያስፈልጋል” ሲሉ ተማጥነዋል፣ ይህ የፍቅር ተግባር በቅዱስ ዘይት መቀባትን እንደሚያመለክትና ይህም ቅባት ወደ ሕዝቡ መሸጋገር እንደለበት ለማመልከት ያህል የአሮን ካህን መዓዛ ከራሱ እስከ ጢሙ ይወርድ እንደነበረ መልካም እረኛ የሆነ ካህንም ሕዝቡን እንዴት በዚሁ ቅባት እንደሚነካ ምስክሩ ነው፣ ሕዝቡ በደስታ ዘይት የተቀባ እንደሆነ ይታወቃል፤ ለምሳሌ ያህል ከቅዳሴ በኋላ ቆሞሱ በቤተ ክርስትያን አፋፍ ላይ ቆም የእያንዳንዱ ም እመን ፊት በመመልከት ማን ይህንን መልካም ዜና እንደተቀበለ ማየት ይችላል፣ ም እመናን ወንጌል ሲሰበኩ በዕለታዊ ሕይወታቸው ጋር የሚገናኝና ሕይወቱን የሚያበራለት እንዲሆን ይገልጋል ከሁሉ በላይ ደግሞ ያለንን አጥርና ድንበር ሰብረን ለሁሉ መድረስና ለእያንዳንዱ አንድ የተስፋ ቃል በቂ ነው ይህም እምነታቸውን በማደን ያለውን ኑሮና ሕይወትን ለውጦ ወደ ጌታ ያቀርባቸዋል፣ ሕዝቡም የሚያስግነን ሁሉን አብረን ከጸለይንና ደስታቸውና ስቃያቸው ችግሮቻቸውና ተስፋቸውን ስንካፈል ነው፣ ይህ ማለትም የክርስቶስ ቅባትን በእኛ ለማየትና ለመስማት ይችላል፤ በዚህም ተበራትቶ አባ ስለ እኔ ጸልዩልኝ፤ አባ ይህ ችግር አለኝ፤ አባ ባርኩኝ ለማለት ይችላሉ፣ ሲሉ መታደስ መጀመርያ የክርስቶስ እንደራሴዎች በሆኑ ካህናቱ መጀመር እንዳለበት አስምረውበታል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.