2013-03-18 17:43:29

እግዚአብሔር መሐሪ ነው፤ ቸርነቱም ወደር የለውም፤ ምሕረት ለመስጠት አይደክምም እኛ ብቻ ምሕረት ለመጠየቅ አንሰለች፣


በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ትናንትና የተነበበው የዕለቱ ቃለ ወንጌል ከወንጌለ ዮውሐንስ ሆኖ በዝሙት ስለተኘችው ሴት ልጅ የኢየሱስ ፍርድ የሚመለክት ነበር፣ °ጻሐፊዎችና ፈሪሳውያን በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው። መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። እርስዋም። ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም። እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት። (8:3-11)
ቅዱስነታቸውን ትናንትና እንደ ማንኛው ቆሞስ በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው የቅድስት ሃና ቤተ ክርስትያን ቍምስና ከቍምስናው ም እመናንና ቆሞስ ጋር አብረው ቅዳሴ ባሳረጉበት ወቅት እላይ የተጠቀሰውን ታሪክ የእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ምሕረትና የመሓሪነት ባህርዩ ላይ በማትኰር፤ ወደ መጨርሻ የሌለው የእግዚብሔር ምሕረት መቅረብ ቀላል እንዳልሆነ እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“በእግዚአብሔር ምሕረት መተማመንና ወድ እርሱ መቅረብ ቀላል አይደለም፤ ምክንያቱም በመሀካላችን ልንረዳው የማንችል እንደ ታላቅ ገደል አለና፤ ያም ሆኖ ይህ ግን ልናደርገው ይገባል፣ ካሉ በሕይወታችን በሚያጋጥሙን ችግሮችና የእረኞች ሁኔታን አስመልክተውም ወደ ንስሓ ሲጠሩና ከም እመናን ጋር የሚያደርጉትን ውይይት እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“አይ አባ! ሕይወቴን ቢያውቁ ኖሮ ንስሓ ግባ እያሉ እንዲህ ባልጨቀጨቁኝ ነበር? ብሎ ም እመኑ ሲያጕረመርም ቆመሱ ምን ጥፋት ሰርተሃልና ብሎ ይመልሳል! ቆመሱም እጅግ በጣም ጥሩ ወደ ኢየሱስ ሂድ! ምክንያቱም ለእርሱ እንዲህ ብለህ ስትናዘዝ ደስ ይለዋል! እርሱ ሁሉን ይረሳል! ታላቅ የመርሳት ችሎታ አለው! ያቅፈሃል ይስመሃል በመጨርሻም የሚልህ ነገር ካለው እኔም አልፈርድብህም፤ ሂጅ ከአሁንም ጀምሮ ደግመህ ኃጢአት አትሥራ ነው” ይህንን ምክር ብቻ ነው የሚሰጥህ፤ ሆኖም ግን ከአንድ ወር በኋላ ወደ ነበርንበት እንመለሳለን! ችግር የለም ወደ ጌታ መመለስ ነው ምክንያቱም ጌታ ለመማር ፈጽሞ አይታክትም በፍጹም አይደክምም” ሲሉ ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ሁሉም ሊረዳው በሚችለው የእረኛችና ቆማሳት ቋንቋ ገለጠዋል፣
ቅዱስነታቸው አያይዘውም ይህንን የኢየሱስ የምሕረት ሥራ ከዕለት ተዕለት ሕይወታችን ጋር በማያያዝ እኛም እንደ ፈረሳውያኑና ጸሓፊዎቹ ኢየሱስ የሚለውን ለመስማት እንፈልግ ይሆናል፣
“እኛም የዚህ ሕዝብ አካል ነን! ባንድ በኩል ኢየሱስ የሚለውን ለመስማት እንሻለን! በሌላው በኩል ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ሌሎችን ለመግረፍና ለመፍረድ ደስ ይለናል፤ የኢየሱስ መል እክት ግን የምሕረት መል እክት ነው፤ እንደሚመስለኝ ለኔ ከጌታ ኃይለኛ መል እክቶች አንደኛው ይህ ነው፣ ምሕረት! ሲሉ እኛም መሓሪዎች መሆን እንዳለብን አሳስበዋል፣
የቅድስት ሃና ቆሞስ አባ ብሩኖ ከቍምስናው ም እመናን ጋር በዚሁ ባልታሰበው የር.ሊ.ጳ ጉብኝት የተሰማቸውን ደስታን ከገለጡና ካመሰገኑ በኋላ የቍምስናው ም እመናን ሁላቸው ልባቸው እንዳቀረቡላቸው ለመግለጥ ቍልፎች እንዲህ ሲሉ ለቅዱስነታቸው አቅርበዋል፣
“ቍምስናው የሁላችን የልቦቻችን ቍልፎች ያበርክታችኋል የመላዋ ቍምስናና የመላው ዓለም የልብ ቍልፎች ናቸው” ብለዋል፣
የቫቲካን ከተማ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ኮማስትሪም በሁኔታው እጅግ ተደንቀውና ከመመረጣቸው ዕለት እስከ ዛሬ ገና በመግረም እንዳለው ሁኔታውን እንዲህ ሲሉ ገልጠውታል፣
“ባለፈው ዕለተ ሮብ ቅዱስነታችሁ ፍራቸስኮስ ብየ እጠራለሁ ስትሉ የካርዲኖልች የተመለከታችሁ እንደሆነ ቤተ ክርስትያን ከተመሠረተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ፍራንቸስኮስ የሚል የር.ሊ.ጳ ስም የለም፣ አጠገቤ ከነበሩ ካርዲናሎች አንዱ “ምን አሉ” ብለው ጠየቀኝ፣ሁሌቴ ደግሞ በጥያቄ ቃና ፍራንቸስኮስ ፍራንቸስኮስ ብለዋል፣ ሁላቸውም እንደዛ፣ በመጨረሻም ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ አለን ብለናል፣ ሲሉ መገረማቸውን ከገለጡ በኋላ፤ቅዱስ አባታችን መላው ዓለም የቤተ ልሔም ግርግም ጠረንን የወንጌል ጠረንን ይጠባበቃል፣ እባክዎን ቤተ ክርስትያንን በወንጌለን ጠረን ይምልዋት፣ ይህም የኢየሱስ ምዑዝ ሽቱ ነው፤ እኛም እንከተላችኋለን፣ ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጠዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.