2013-03-18 13:45:23

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዚህ የተገባው ሳምንት መርኃ ግብር


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ቅዳሜ መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ከአገረ ቫቲካን ከሚገኘው ከሄሊኮፕተር ማረፊያ እኩለ ቀን ተነስተው ጋስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ ሕንጻ በመሄድ እዛው ከሚገኙት ከቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጋር እንደሚገናኙ አዛው አብረው የምሳ ግብዥ እንደሚቋደሱና መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ለበዓለ ሆሳዕና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው እኩለ ቀን ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር እንደሚመሩ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስነታቸው ዛሬ ከአርጀቲና ርእሰ ብሔር ክርስቲና ፈርናንደስ ደ ኪርኽነር ጋር መገናኘታቸውና እንዲሁም እ.ኤ.አ. መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተልእኮአቸውን በይፋ ለመጀመር በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጥዋቱ 9 ሰዓት ተኩል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ ረቡዕ መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 11 ሰዓት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ቀለመንጦስ የጉባኤ አዳራሽ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ልኡካንን ተቀብለው እንደሚያነጋግሩና በመርህ የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተውም በቅድስት መንበር ከተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት ጋር እንደሚገናኙ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.