2013-03-15 14:45:14

የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አጭር የሕይወት ታሪክ


RealAudioMP3 በርጎሊያ ብፁዕ ካርዲናል ኾርገ ማሪዮ የአንዲት ቅድስት ካቶሊካዊት ሮማዊት ቤተ ክርስቲያን 266ኛ ር.ሊ.ጳ. እንዲሆኑ በተካሄደው የብፁዓን ካርዲናሎች ዝግ ጉባኤ መመረጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት። አንድ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባልና የላቲን አመሪካ ተወላጅ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ሲመረጡ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ያመለከተው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአርጀንቲና የቡዌኖስ አይረስ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት እንዲሁም በአርጀንቲና የምስራቅ ሥርዓት ለሚከተሉት የካቶሊክ ምእመናን ሥዩመ ጳጳስ መሆናቸውም ሲያስታውቅ፣ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 1936 ዓ.ም. ከኢጣሊያ የትውልድ ዘር ካላቸው ቤተሰብ ከባቡር ሃዲድ የመጓጓዣ ግብረ ሙያተኛና ከእናታቸው እመቤት ረጂና ሲቮሪ የተወለዱ አምስት ወንድሞች ያሉዋችው የበኽር ልጅ እንደሆኑና፣ የሥነ ቅመማ ሙያ ትምህራታቸውን እንዳጠናቀቁ በተሰማቸው የክህነት ጥሪ መሠረትም በቪላ ደቮቶ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤተ ገብተው እ.ኤ.አ. መጋቢት 11 ቀን 1958 ዓ.ም. የኢየሱሳውያን ማህበር ተመካሪ ሆነው ቀጥለውም በቺለ በሥነ ሰብአዊ የትምህርት ዘርፍ ተመርቀው እ.ኤ.አ. በ1963 ዓ.ም. ወደ ትውልድ አገራቸው አርጀንቲና ተመልሰው ሳን ሚገል ከተማ በሚገኘው ሳን ኾሴ የፍልስፍና መንበረ ጥበብ ገብተው በፍልስፍና ተመርቀው እንዳጠናቀቁም እ.ኤ.አ. ከ 1964 እስከ 1965 ዓ.ም. በ ሳን ሚገል በሚገኘው በሳን ፈ መንበረ ጥበብ የሥነ ጽሑፍና የሥነ ድረስት እንዲሆን የሥነ አዕምሮ አስተማሪ በመሆን አገልግለዋል። እ.ኤ.አ. በ 166 ዓ.ም. በቡዌኖስ አይረስ በሚገኘው ሳልቫቶረ መንበረ ጥበብ በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ አስተማሪ በመሆን ሲያገለግሉ፣ እ.ኤ.አ. ከ 1967 እስከ 1970 ዓ.ም. ሳን ሚገል በሚገኘው በሳን ኾሴ የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ የቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዳበቁ ከ 1970 ዓ.ም. እስከ 1971 ዓ.ም. የኢየሱሳውያን ሦስተኛ ደረጃ ተመክሮአቸውን በስፐይን ፈጽመው እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 22 ቀን 1973 ዓ.ም. እንደ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አቢይ መሓላ እንደፈጸሙም የቅድስት መንበር መግለጫ ይገልጣል።
እ.ኤ.አ. ከ 1972 እስከ 1973 ዓ.ም. በሳን ሚገል በሚገኘው በኢየሱሳውያን ማኅበር የቪላ ባሪላሪ ገዳምና የተመካርያን ቤት አለቃ እንዲሁም የቲዮሎጊያ መምህር በአርጀንቲና የኢየሱሳውያን ማኅበር ቅርንጫፍ የጠቅላይ አለቃ አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 31 ቀን 1973 ዓ.ም. የኢየሱሳውያን ማኅበር በአርጀንቲና ጠቅላይ አለቃ ሆነው ለስድስት ዓመት ካገለገሉ በኋላ ከ 1980 ዓ.ም. እስከ 1986 ዓ.ም. በቡዌኖስ አይረስ የቲዮሎጊያና የፍልስፍና መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪና በሳን ሚገል ሰበካ ለሚገኘው ፓትሪያርካዊ ሳን ኾሴ ቁምስና ቆሞስ በመሆ እንዳገለገሉ የጠቆመው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ እ.ኤ.አ. በ 1986 ዓ.ም. መጋቢት ወር ወደ ጀርመን ተልከው በቲዮሎጊያና ፍልስፍና ሊቅነት አስመስክረው በአርጀንቲና ኮርዶባ በማኅበረ ኢየሱሳውያን ወደ ሚተዳደረው ቤተ ክስቲያን ተዛውረው እዛው አበ ነፍስ ሆነው እንዳገለገሉም አስታውቋል።
እ.ኤ.አ. ግንቦት 20 ቀን 1992 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ውሳኔ አማካኝነት በአርጀንቲና የአውካ ሰበካ ጳጳስና የቡዌኖስ አይረስ ሰበካ ረዳት ሊቀ ጳጳሳት እንዲሆኑ ተሹመው እ.ኤ.አ. ሰኔ 27 ቀን 1992 ዓ.ም. በብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ኵዋርቺኖ በአርጀንቲና የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ኡባልዶ ካላብረዘ በመርሰደስ ሊኻን ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤሚሊዮ ኤግኜኖቪች ሢሜተ ጵጵስና እንደተቀበሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ እ.ኤ.አ. ሰኔ 3 ቀን 1997 ዓ.ም. የቡዌኖስ አይረስ ሰበካ ተጠባባቂ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው በማገልገል ላይ እያሉ በሰበካው ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካዲናል ኵዋርቺኖ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ምክንያት እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 1998 ዓ.ም. የቡዌኖስ አይረስ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው እ.ኤ.አ. ህዳር 6 ቀን 1998 ዓ.ም. በአርጀንቲና ለሚኖሩት የምስራቅ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ሥዩመ ጳጳስ ሆተው መሾማቸውም ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 21 ቀን 2001 ዓ.ም. በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ውሳኔ መሠረት ለካርዲናልነት ማዕርግ ከተመረጡት ብፁዓን ሊቀ ጳጳሳት ውስጥ አንዱ በመሆን የካርዲናል ማዕርግ ተቀብለው በሮማ የቅዱስ ሮበርቶ በላርሚኖ ቤተ ክርስቲያን ሥዩመ ጳጳስ እንደሆኑና እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2001 ዓ.ም. ብፁዕ ካርዲናል እንደመሆናቸውም መጠን የብፁዓን ጳጳሳት አሥረኛው ይፋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ጠቅላይ አለቃ በመሆን እንዳገለገሉ ሲገለጥ፣ እ.ኤ.አ. ከ ሚያዝያ 18 ቀን እሰከ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመረጠው የቅዱስ ጴጥርስ ተከታይ መራጭ ዝግ ቅዱስ ጉባኤ የተሳተፉም ሲሆን እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 2 ቀን እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም. ለተካሄደው የመላ ብፁዓን ጳጳት 11ኛው ልዩ ሲኖዶስ ምክር ቤት አባል ሆነው እንዳገለገሉና፣ እንዲሁም የሥርዓተ አምልኮና ቅዱሳት ሚሥጢራት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበ፣ የካህናት የመናንያንና የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበራት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር፣ የቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት የድኅረ ሲኖዶስ ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት አባል እንደሆኑም የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ በአርጀንቲና የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጥበብ ዓቢይ አለቃ፣ በአርጀንቲና የጳጳሳዊ መናብርተ ጥበብ የሚከታተለው ምክር ቤት ሊቀ መንበር እንዲሁም በአገሪቱ የአንዲት ቅድስት ካቶሊካዊት ሮማዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ ፍርድ ቤት ዋና ዳኛ በመሆን፣ እ.ኤ.አ. ከህዳር 2005 ዓ.ም. እስከ ህዳር 2011 ዓ.ም. የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር በመሆን እንዳገለገሉ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.