2013-03-08 15:14:03

የቫቲካን ማተሚያ ቤት ለቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ክብር


RealAudioMP3 የቅድሱነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው ከማስረከባቸው ጥቂት ቀናት ቀደም መማድረግ ያስደመጡት የለገሱት ሥልጣናዊ አስተምህሮና ስብከት ማእከል ያደረገ አዲስ መጽሐፍ የቫቲካን ማተሚያ ቤት ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያለው ታማኝነት የሚመሰክር በቫቲካን ማተሚያ ቤት ታትሞ ከትላትና ጀምሮ ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይኽ አዲስ መጽሐፍ ቅዱስነታቸው ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከየካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. በገዛ ፈቃዳቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣናቸውን እስከ ለቀቁበት እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ያለው የጊዜ ገደብ ያካተተ መጽሐፍ ሲሆን፣ እንደሚታወሰውም እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን ልክ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣናቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት ባሉት የጊዜ ገደብ ውስጥ ያሰሙት የለገሱት ሥልጣናዊ ትምህርት ያጠቃለለ መጽሐፊ መሆኑና፣ የቫቲካን ማተሚያ ቤት ቀዳሜ ዓላማውም የእግዚአብሔር ቃልና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣናዊ ትምህርት ማሰራጨት የሚል ሲሆን። የዚህ አዲስ መጽሐፍ ውጫዊው ሽፋን ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. እንዲሁኑ ወደ ሚያሸጋግረው የወሰኑት ሰዓት ከመድረሱ ቀደም በማድረግ በመጨረሻው የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እ.ኤ.አ. የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ሲያቀርቡ የሚያሳይ የቅዱስነታቸው ምስል የተኖረበት፣ የመጽሐር ርእስ በዚያኑ ዕለት “በቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይነት ሓዋርያዊ ሥልጣን ተልእኮ አገልግሎት ያለው ደስታና የሃላፊነቱንም ክብደት በመሸከሙ ረገድ ብቸኝነት ተሰምቶኝ ፈጽሞ አያውቅም” ያሉትን ሃሳብ የሚገልጥ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
ይኽ መጽሓፍ የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ እንደወሰኑ የገለጡበት ለብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ያስደመጡት መልእክት ሁለት ቀን በኋላ እ.ኤ.አ. የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ያቀረቡት የዕለተ ረቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. የሮማ ሰበካ ውሉደ ክህነት አባላትን ተቀብለው ያሰሙት ሥልጣናዊ መልእክት፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 17 ቀንና የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ያስደመጡዋቸው የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮዎች፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን አበይት የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ብፁዓን ካርዲናሎችን በመቀበል ያሰሙት መልእክት፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በሮማ ከተገኙት ከተለያዩ አገሮች የመጡትን ብፁዓን ካርዲናሎችን በመቀበል ያሰሙት የስንበት ቃል፣ በመጨረሻም እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቅትር በኋላ ወደ ካተል ጋንዶልፎ ሐዋርያዊ ሕንፃ ተዛውረው ከቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣናቸው እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከምሽቱ ስምንት ሰዓት አንድ ደቂቃ ከመድረሱ በፊት እዛው በካስተል ጋንዶልፎ ለተሰበሰቡት ከውጭና ከውስጥ ለመጡት መእመናን ያሰሙት የመጨረሻና የሰጡት የመጨረሻው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ቡራኬ ያካተተና ሁኔታውንም ጭምር የሚተርክና የሚተነትን እንዲሁም በመጨረሻ ፊርማቸውን በማኖር የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመምረጥ ላለው አንቀጽ የሚያሟላ የማይሻረው ያወጁት ታካይ ሐዋርያዊ ሕግ ጭምር ያካተተ መጽሓፍ መሆኑ ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.