Home Archivio
2013-03-04 14:28:05
የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ
በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በጸሎት ዙሪያ የጠመረች ኃያው ቤተ ክርስቲያንን የሚያረጋግጥ በቅዱስ ቁርባን ፊት በዚህ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መንበር ክፍት በሆነበት ወቅት ስለ ቅዱስት ቤተ ክርስቲያንና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመምረጥ ብፁዓን ካርዲናሎች ለሚያደርጉት ዝግ ቅዱስ ጉባኤ ሃሳብ ያደረገ በቅዱስ ቁርባን ፊት ቀጣይ የአስተንትኖና የጸሎት ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ትላትና በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክልፍ ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ለተገኙት የውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኖች በሰጥት ጋዜጣው መግለጫ በማብራራት በቅዱስ ጴርጥሮስ ባሲሊካ ከቅትር በኋላ ከሚቀርበው መሥዋዕተ ቅዳሴ ቀጥሎ ልዩ ስለ ብፁዓን ካርዲናሎች ጸሎት እንደሚደረግና ይኽም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመምረጥ የሚያደረጉት ዝግ ቅዱስ ጉባኤ ላይ ያተኮረ መሆኑ አብራርተዋል።
ሁሉም ሰማንያ ዓመት ዕድሜ ያልሞላቸው ብፁዓን ካርዲናሎች ቅዱስ አባታችንን ለመረጥ እንደሚሰበሰቡና ዛሬ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው አዲስ የሲኖዶስ አዳራሽ የመጀመሪያው ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ምርጫ በሲስቲና ቤተ ጸሎት ለሚደረገው ዝግ ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ የጠሩት ጉባኤ መካሄዱ ተገልጠዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.