2013-03-04 14:32:16

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ
ተስፈኛ ስንበት


RealAudioMP3 በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመምረጥ ለሚደረገው ቅዱስ ዝግ ጉባኤ ሃሳብ ያደረገ ጸሎት በመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እየተካሄደ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማገባደጃ የሚያቀርቡት በቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመግለጥ፣ ልኂቅ የሮማ ጳጳስ ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ ካስተል ጋንደልፎ በሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንጻ እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደደረሱ እዛው ለተገኙት በብዙ ሺሕ ለሚገመቱት ምእመናን ይፋው ባሰሙት የመጨረሻው ንግግራቸው “ተራ መንፈሳዊ ነጋዲ በሚል መጠሪያ ገዛ ራሳቸውን በመግለጥ የቤተ ክርስቲያን የበላዩ እራስ የህነው መጋቤ ክርስቶስ ነው። ቤተ ክርስቲያን የእርሱ ነች፣ የሚመራትም እርሱ ነው” እንዳሉ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ጠቅሰው፣ ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ በይፋ ከዚህ የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይነት ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው ለመሰናበት እሳቸው ያሰሙት ንግግር በጠቅላላ በሁሉም ልብ ታትሞ የሚቀር የብዙ ሰው ልጅ ልብ የነካ መሆኑ ያስታወሱት አባ ሎምባርዲ አክለውም፣ የላቀው ሰብአዊነታቸውና ጥልቅ መንፈሳዊነታቸው ትህትና የተሞላው ጸላይና በእምነት ላይ የጸናው ሕይወታቸው ሊቅነታቸው ሁሉም በቅርብ ለይቶ የተገነዘበው መሆኑ ገልጠዋል።
ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣናቸው በስቃይ በህመም የገለጡት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየት በተፈጸመው ሐዋርያዊ ተልእኮአቸው የሚደነቅ ጽናት ያሳዩ ናቸው፣ ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛም ለየት ባለ መልኩ ጽናት የተሞላው የእግዚአብሔርን ፍቃድ እሺ ብሎ በመቀበል የተገለጠ ነው። ስለዚህ አንዱ ካንዱ ይበልጣን ሳይሆን ቆራጥና ጽኑ የሚያሰኘው የእግዚአብሔር ፈቃድ ለይቶ እሺ ብሎ በመታዘዝ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ተቀብሎ የመኖር ምስክርነት ነው ብለዋል። ሁለቱ ር.ሊ.ጳ. በሥልጣናዊ አስተምህሮአቸውና በደረሱዋቸው አዋዲ መልእክቶቻቸው በተለይ ደግሞ በሕይወታቸው ዕለት በዕለት የእግዚአብሔር ፈቃድ መኖር ያለው አስፈላጊነትና መላ ኅልውናቸው የዚህ ፈቃድ ተገዥ አድርገው መኖራቸው መስክረውልናል ብለዋል።
በገዛ ፈቃዳቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው የመልቀቁ ውሳኔ ባስደመጡበት ወቅት እንዳመለከቱት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው የመልቀቁ ውሳኔ ከኃላፊነት ከተቀበሉት ሐዋርያዊ ተልእኮ መሸሽ ማለት ሳይሆን፣ በውሳኔው መሠረት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመፈጸም የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በተረጋገጠ ተስፋ የሚመራት እርሱ መሆኑ በማመን ለእግዚአብሔር ማቅረብ የሚል ነው። በትህትናና በተረጋጋ መንፈስ ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ የእግዚአብሔርን ቤተ ክስቲያን እርሱን በመታዘዝ ያገለገሉ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው ጭምር በገዛ ፈቃድ ሲለቁም የእርሱ ፈቃድ ነው የፈጸሙት፣ ይኽንን ፈቃድ በመፈጸምም ቤተ ክርስቲያንን ነው ያገለገሉት።
የልኂቅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ ቅዱስ ውርሻና አደራ ለቤተ ክርስቲያን ጸልዩ የሚልና ስለ ቤተ ክርስቲያን መጸለይ የሁሉም ኃላፊነትና ተልእኮ ነው የሚል እማኔ ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ብፁዓን ካርዲናሎች በዚህ ጸሎት የመጠመዱ ኃላፊነት የተቀበሉት የሐርያዊነት የተልእኮ ባህርይ ነው። ስለዚህ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመምረጥ ለሚያደረጉት ቅዱስ ጉባኤ መጸለይና ለሚመረጡት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በጸሎት የመሸኘትና አለ ምንም ቅድመ ሁኔት በመታዘዝ የሚኖሩት ሐዋርያዊ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለመላ ሰው ዘር ጥቅምና መልካምነት ነው ሲሉ አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ አብራርተው፣ በዚህ የቤተ ክርስቲያን ጸሎት ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ እንደሚሸኙንና በፍቅር በልብ በጸሎት በአስተንትኖ እሳቸው እንዳሉት ከእኛ ጋር ናቸው በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.