2013-03-01 13:54:24

የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር የምስጋና ቃል ለቅዱስነታቸው


RealAudioMP3 ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን በእድሜ መግፋት ምክንያት ለመልቀቅ ወስነው ወደ ካተል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንፃ ከመዛወራቸው ቀደም በማድረግ የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ባለፉት ስምንት ዓመት ቅዱስነታቸው ለኢጣሊያና ሕዝቧ ያሳዩት ቅርበትና ፍቅር ጠቀስ ባስተላለፉት መልእክት ለቅዱስነታቸው ያላቸው አድናቆት በመግለጥ፣ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ የወሰዱት ቁርጥ ውሳኔ ለመላ ዓለም አብነት ነው ክሉ በኋላ መቼም ቢሆን በኢጣሊያ ሕዝብ ልብ የሚታወሱ አባት ናቸው እንዳሉ የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አመለከተ።
ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ በሳቸውና በኢጣሊያ ሕዝብ ስም ባስተላለፉት መልእክት መላ ኢጣሊያ ለቅዱስነታቸው ቅርበትና ፍቅር እንዳሳየም መስክረው፣ ከቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳትሆን በተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ጭምር የተደነቁ በሃገራት መሪዎች የሚመሰገኑ ጥልቅ አሳቢ ናቸው፣ በኢጣሊያና በቅድስት መንበር መካከል ያለው ግኑኝነት በሳቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ወቅት እጅግ የተዋጣለነት መሆኑ እንዳሰመሩበትም የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።
ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ባስተላለፉት መልእክት እ.ኤ.አ. የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቅዱስነታቸው ጋር ያካሄዱት የመጨረሻው ይፋዊ ግኑኝነት ጠቅሰው፣ በተካሄደው ግኑኝነት በሁለቱ አካላት አንዳዊ ስሜት መታየቱና በቤተ ክርስቲያንና በዓለም የተከስተቱት አሳሳቢ ሁኔታዎች ምንኛ ልባቸው እንደነካውና ይኸንን ከባድ የቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ ሥልጣን በመኖር በጽናትና በቆራጥነት በመምራት በእውነት የተመራ መፍትሔና ሃሳብም በመለገስ ላሳዩት አሳቢነት እንዳመሰገኑና ቅዱስነታቸው የቅዱስ ጴጥርስ ተከታይነት ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን ቢለቁም ሮማን እንደማይለቁ ከኢጣሊያ እንደማይርቁ የገለጡላቸው ቅርበት ሁሉ ናፖሊታኖ በማስታወስ ቅርበቱ ኅያው ሆኖ ይቀራል እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.