2013-03-01 13:43:38

የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ


RealAudioMP3 “ቅዱሱነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና በኢጣሊያ ሰዓት አቆታጠር ከቀትር በኋላ ልክ 05 ሰዓት ሮማ አቅራቢያ ወዳለው ካስተል ጋንዶልፎ ከተማ ወደ ሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንጻ መዛወራቸው ትዊተር በተሰየመው የማኅበራዊ ድረ ገጽ በኩል ባለው የግል አድራሻቸው አማካኝነት እንዳሳወቁየቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክልፍ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ትላትና በቅዱስ መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ለተገኙት ከተለያዩ አገሮች ለተወጣጡ ልኡካን ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ በነደታ ካፐሊ አስታወቁ።
አባ ሎምባርዲ ጳጳሳዊ የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ቀደም በማድረግ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የትዊተር Pontifex በሚል ስያሜ የሚታወቀው አድራሻ አዲስ ር.ሊ.ጳ. እስከ ሚመረጡ ድረስ ባዶ እንደሚሆንና የሚመረጡት ር.ሊ.ጳ. ሊጠቀሙበት ወይንም እንዲቋረጥ የማድረጉ ውሳኔ የሳቸው እንደሚሆንና ለጊዜው ክፍት ሆኖ ይቀራል” በማለት የሰጡት መግለጫ በማስታወስ፣ ቅዱስነታቸው ትላትና በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ስምንት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መኖናቸው ሲዘከርም፣ “ልኂቅ ሮማዊ ጳጳስ ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ ካስተል ጋንዶልፎ በሚገኘው ሐዋርያዊ ሕንፃ የሁለት ወር ቆይታ በማድረግ አንዲት ቅድስት ሮማዊት ሐዋርያዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አዲስ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሲኖራት በአገረ ቫቲካን ወደ ሚገኘው ለመኖሪያ የመረጡት ገዳመ መናንያን ተመልሰው ገዳማዊ ሕይወታቸውን እንደሚጀምሩ ነው” እንዳሉ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ካፐሊ ቀጥለውም፣ አገረ ቫቲካን በሚገኘው ቀለመንጦስ ሐዋርያዊ አዳራሽ ቅዱስነታቸውን ለመሰናበት 144 ብፁዓን ካርዲናሎች መገኘታቸውና፣ ባሰሙትም ቃል ለሚመረጡት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሙሉ ታዣዥነታቸውንም ከወዲሁ በመግለጥ የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ምርጫ ለተሳታፊ ብፁዓን ካርዲናሎች ለመጀመሪያው የብፁዓን ካርዲናሎች ቅዱስ ጉባኤ የጥሪ መልእክት በማስተላለፍ የቅዱስ ጴጥሮስ ተክታይ ለመምረጥ ለሚደረገው የቅዱስ ዝግ ጉባኤ ሂደት በካፐላ ሲስቲና ያስጀምራሉ እንዳሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.