Home Archivio
2013-02-27 14:45:33
የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዕድሜ መግፋትና እዲሁም ኃይል መድከም ምክንያት የቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ መወሰናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸ ጴጥሮሳዊ ሥልጣናቸው እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከምሽቱ ስምንት ሰዓት የሚያበቃለት መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት ትላትና በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ለተገኙት ከውጭና ከውስጥ ለመጡት ልኡካን ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውሰው፣ ቅዱስነታቸው ከተለያዩ የመንግሥታት እንዲሁም የፖለቲካ የሃይማኖት መሪዎች ቅርበታቸው የሚያረጋግጥ የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት እየደረሳቸው ሲሆን ዛሬ ዕለተ ረቡዕ እ.ኤ.አ. የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ያቀረቡት ይፋዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የመጨረሻ እንደሚሆንም አስታውሰው፣ ከቅዱስ አባታችን ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረትም
ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣንቸውን ከለቀቁ በኋላ ቅዱስ አባታችን በነዲክቶስ 16ኛ የሚለው መጠሪያ ይዘው የሚቀሩ ሲሆን፣ ልኂቅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወይንም ልኂቅ ሮማዊ ጳጳስ በሚል መለያ እንደሚታወቁ ነው
ካሉ በኋላ ጴጥሮሳዊ የአሳ አጥማጅ ምስል ያለበት ቀለበት እንደሚሰረዝና የሚያጠልቁት ጫማ ቀይ ቀለም ያለው መሆኑ ቀርቶ ቡናማ ቀለም እንደሚኖረው ገልጠው፣ ሆኖም በቅርቡ በሚክሲኮ ባካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ከሌዮን ዕደ ሙያተኞች ገጸ በረከት የተሰጣቸውን ቡና ጫማ እንደሚጠልቁ ይገመታ ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይፋዊው የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አቅርበው እንዳበቁም፣ በሐዋርያዊው መንበር በሚገኘው በቅዱስ ቀለመጦስ የጉባኤ አዳራሽ ከተለያዩ መንግሥታት መሪዎችና አበይት አካላት ጋር እንደሚገናኙ አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ ከስሎቫኪያ መንፈሳውያን ነጋዲያን ጋር በመሆን ሮማ ከሚገኙት ከስሎቫኪያ ርእሰ ብሔር፣ ከሳን ማሪኖ አገረ ገዥ ከባቪየራ ርእሰ ክፍለ ሃገር ከአንዶራ ልኡል ጋር መገናኘታቸው ገልጠው እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከቀትር በፊት 11 ሰዓት ሮማ ከሚገኙት ከተለያዩ አገሮች የመጡት ብፁዓን ካርዲናሎች ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ከቀትር በኋላ ልክ አራት ሰዓት ከ 55 ደቂቃ በብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ አሸኛኘት ተደርጎላቸው ከአገረ ቫቲካን ከሚገኘው ከሄሊኮፕተር ማረፊያ ሮማ አቅራቢያ ወደ ሚገኘው ጳጳሳዊ ሕንጻ በሄሊኮፕተር ተጉዘው እዛው በአገረ ቫቲካን መሥተዳዳር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጁሰፐ በርተሎ በአልባኖ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሰመራሮ በካስተል ጋንዶልፎ ከተማ ከንቲባ በጳጳሳዊው ሕንጻ በሚገኘው መናፍፈሻ አቀባበል ተደርጎላቸው ልክ አምስት ሰዓት ተኩል ላይ በጳጳሳዊው ሕንጻ በሚገኘው ሐዋርያዊ መስኮት ብቅ ብለው ከተለያዩ የውስጥና ከውጭ ለሚመጡት መንፈሳውያን ነጋዲያ የመጨረሻው ይፋዊ የስንበት ሰላምታን አቅርበው፣ ልክ ከምሽቱ ስምንት ሰዓት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣን ክፍት ከሆነ በኋላ ከጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ ኃይል ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚሰጠው ጥበቃ ተቋርጦ የካስተል ጋንደልፎ ጳጳሳዊ ሕንጻ በር ከተዘጋ በኋላ የአገረ ቫቲካ የጸጥታ ኃይል አባላት የጸጥታና ደህንነት ጥበቃ አገልግሎት ይቀጥሉበታል።
አባ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አክለውም፣ እ.ኤ.አ. ምናልባት መጋቢት 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ሊሆን ይችላል የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ምራጫ ተሳታፊ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን መላ ብፁዓን ካርዲናሎች ለብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ጥሪ ያስተላልፋሉ ከዚያ ቀን በፊት ለማስተላለፍ የሚቻል አይሆንም። ስለዚህ የሚካሄደው የብፁዓን ካርዲናሎች ቅዱስ ጉባኤ ከመጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. በፊት እንደማይከናወን ነው። ጉባኤው በአገረ ቫቲካን በሚገኘው የሲኖዶስ አዳራሽ የሚካሄድ መሆኑና፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመምረጥ የሚደረገው ዝግ ቅዱስ ጉባኤ ሲቃረብም ብፁዓን ካርዲናሎች ወደ ቅድስት ማርታ ሕንጻ ይዛወራሉ ብለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.